ልጥፎች

ድምጽ አልባዋ። {የወግ ገበታ}

ምስል

ድምጽ አልባዋ።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ  ድምጽ አልባዋ የኢትዮጵያ እናት ለፖለቲካ አክተሮች የሊኳንዳ ቤት   ማዘጋጀት አይታክታትም … ዛሬም። „ብልህ ሰው መጽሐፍን መስማት ይወዳል። የሚጠራጠር በመጽሐፉ የማያምን ሰው ግን   በጥልቅ ነፋስ መካከል እንደምትጉላላ   መርከብ ይሆናል።“ መጽሐፈ ሲራክ ምእራፍ ፴፮ ቁጥር ፪ የኢትዮጵያ አዬሩ ስትራፓ ያዘው። ጓጐለ። ውዶቼ እንዴት ሰነበታችሁልኝ? ደህና ናችሁ ወይ? እስቲ ድብርታሙን ዛሬን እንዲህ አብረን እንቃኛው … ስክነት የት ይሆን የሚሸመተው? ውስጥሰ ከእርቃንነት መቼ ይሆን ለእራፊ የሚበቃው? ከቶ በቃን ህውሃት መባልን ትናንት በአኽትዮሽ መንፈስ በወል ማዕዶት የታለፈው ማዕደኝነትንም ጎበኘውን? የትውልዱ የሃሳብ ብክነትስ ማቆሚያ ለመቼ ተቀጠረ? መቼም አዘኔታ የለም ትውልዱን በዬዘመኑ ለቋያ ለመማገድ። ሥልጣኔ የለለን መሆኑን ሳስበው አይሆኑ ሆኖ ነገ ጠቆረብኝ። እንደዚህ ሰሞናት ባዶነት ተሰምቶኝ አያውቅም። እንዳሻኝ እምቀምረው ስፈለግ ግጥሙን፤ ስፈልግ ሀተታውን፤ ስፈልግ ልዩ ሪፖርቱን ስፈልግ ወጉን እንዳሻኝ በብራና ወክ እንዲህ ያላልኩበትን ያህል ሰሞናቱን ግን አልቻልኩም። ድብርት ቤቴ፤ ድብርት በብራናዬ ላይ ተዛናከተባቸው እንዳሻቸው … ክብረቶቼ የቀንበጥ ሚዲያ ታዳሚዎቼ እኔ መጻፍ ሥራ ሆኖብኝ አያውቅም። በህይወቴ ቀላሉ ሥራ መጻፍ ነው። ሰሞናቱን ግን   በዬአቅጣጫው ያለውን እብለቱን፤ ፌኩን፤ ንደቱን፤ ቦክሱን፤ ውስጥን ከፍቶ እንዳሻህ መባሉን፤ ቁጥበንት መሸጥ መለወጡን፤ መታቀብ መቀበሩን ሳስተውለው ግን ያ ሁሉ ድካም ለምን ስለምን አስፈለ ገን ይሆን? ብዕሬም ብራናዬም ሱባኤ ላይ ነበሩ … ዛሬ የሙት ሙቴን ተሟግቼ...

ተስፋ {የወግ ገበታ}

ምስል

ተስፋ {የወግ ገበታ}

ምስል
 እንኳን ወደ ቀንበጥ በሰላም መጡልኝ  ተስፋ። „መዳህኒቴ እና ክብሬ በእግዚብሄር ነው። የረድኤቴ አምለክ ተስፋዬም እግዚአብሄር ነው።“ መዝሙር ምዕራፍ ፷፪ ቁጥር ፯ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ v      ተስፋ ጸጋ v      ተስፋ ምህረት v      ተስፋ መድህን ነው።     ምን ያህል እንደተጓዝኩኝ አላውቀውም? ምን ያህል እንደሚቀረኝም አላውቀውም? አለማዋቄን ስጠይቀው አለማወቁን ገለጸልኝ። ተስፋን እጠብቃለሁኝ። እ.አ.አ 2010 ተስፋ መጸሐፌ ላይ የጀርባው ሽፋን ላይ ያልኩት ነበር አሁንም እምለው ይኸው ነው ...  ·          እ ፍታ እንደ መግቢያ …   የኢትዮጵያ ቅኔዎች የእኔም የኔታዎች የቀንበጥ ብሎግ ክቡር ታዳሚዎቼ እንደምን አላችሁልኝ? ዕለቱን ከተሰፋ ፈላጊና ተስፋ ፈጻሚ ጋር ያለው ድልድይ አስመልክቶ አንድ ወግ ቢጤ ለማቅረብ ተሰናዳሁኝ እንሆ … የተስፋ ጥገት ለአላዛሯ ኢትዮጵያ በእጅጉ ያስፈልጋታል። ይህ ማለት የተሰፋ ጥገት ያለው ያው የፈረንጅ ላሞች ዝርያ ስለሆነ በገፍ ወደ ኢትዮጵያ እንዲገባ እዮር ቢፈቅድላት ለእምዬዋ እንደማለት። የፈረንጅ ላሞች ወተተታም ናቸውና። ምኞት ...  ግን እኛ ለማይነጥፍ ጥገት ግሬራውን ወይንም ቆሬውን በገፍ ማሰናዳት ይጠበቅብናል። ታዲያ ምርቃታችን ሳንረጋግጥ ጥንቃቄ ከኖረን ነው። በስተቀር ምርቃትን የፈጠረም የሰጠም ኤልሻዳይ አምላክ ከከፋው ያነሳዋል … ምርቃቱን። አምላካችን ሲከፋው ምርቃቱን ...

ግድግዳ እና እኔ {ሥነ ግጥም።}

ምስል

ምንድነው የተፈለገው? ዙፋኑ እስከ እልፍኝ አሰከልካዩ ከቢኦኤ አማርኛው ዝግጅት ጋር ጥድፊያ በግራ ቀኝ የያዘው።

ምስል

ምንድነው የተፈለገው? ዙፋኑ እስከ እልፍኝ አሰከልካዩ ከቢኦኤ አማርኛው ዝግጅት ጋር ጥድፊያ በግራ ቀኝ የያዘው።

ምስል
 እንኳንም ወደ ቀንበጥ ብሎ በሰላም መጡልኝ።  ምንድን ይሆን የተፈለገው? ሦስት ጣማራ ቅዬጣ …   ዝንጣ ይባል ፍጠጣ ወይንም ፍለጣ ወይንም ሽምጠጣ አይታወቅም …?   „ስለ ደናግልም የጌታ ትእዛዝ የለኝም፣ ነገር ግን የታመንሁ እሆን ዘንድ ከጌታ ምህረትን እመክራለሁ። የሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ምልዕክት ወደ ቆርንቶስ ምዕራፍ ፯ ቁጥር ፮“ ከሥርጉተ ሥላሴ Sergute Selassie 29.05.2019 ከ እመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። ·       መነሻዬ። https://www.youtube.com/watch?v=sYeDO_87484&t=2s #Ethiopia   #Mereja ልንወርድ ከነበረበት አዘቅት የማገገም ሁኔታ አለ - ጠ / ሚ አብይ ከቪኦኤ ጋር ያደረጉት የአንድ ለአንድ ቃለመጠይቅ | Ethiopia Mereja TV Published on May 28, 2019 https://www.satenaw.com/amharic/archives/68090 የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ _ ከአቶ ንጉሱ ጥላሁን እና ከሆኑት አቶ ነቢያት ጌታቸው ጋር አጭር ቆይታ May 27, 2019 https://www.satenaw.com/amharic/archives/68082 “ የለውጡ አካሄድ ወደ ትክክለኛው መድረሻችን ሊያደርሰን የሚችል ነው። ” ስዩም ተሾመ – SBS Amharic May 27, 2019 በግርምታ ሰሞኑን ታደምኩበት። ግን እንዴት ናችሁ የኔዎቹ? ደህና ናችሁ ወይ? ሦስት ጣምራነት ብቻ ሳይሆን አራተኛውም አለ ዲሲ ላይ የተጠመደ አዲስ ትዕይንት። ተከድኖ ለጊዜው ይቀመጥ። ሌላ ጊዜ ፈታ በል...