ልጥፎች

የግራ ፖለቲካ ምራቅ ወይንም የሳሙና አረፋ ነው።

ምስል
  ማህበረ ቅንነት ለኢትዮጵያ ውራጅ ፖለቲካ ብላችሁ አጋ ለይታችሁ አትለያዩ፨ የግራ ፖለቲካ ምራቅ ወይንም የሳሙና አረፋ ነው። አድሮ የማይገኝ፥ ቂም ያረገዘ በቀል የሚቀፈቅፍ ጃርት፨ ሥርጉትሻ   አገልጋይ፨ 2024.04.22

እስኪ፨

ምስል
    እ ስኪ ፨ "በእግዚአብሄር ሕግ ጸንተህ ብትኖር ለዘላዓለም፦ በተድላ በደስታ በኖርክ ነበር።" (መጽሐፈ ባሮክ ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፪)   (አብይ እንኳን አገር ወረዳ መምራት አይችልም። ወሮ ፈትለወርቅ) እንፈትሸው። ዶር አብይን " ማን ፈጠረው? ማንን ይመስላል? ማን ዕድሉን ፈጠረለት? ማን ኮትኩቶ አሳደገው? ተጠያቂው አሳዳጊው ወይንስ ታዳጊው? ትንሽ በስሱ ልፈትሸው። የተለሞጠ ስለሆነብኝ።    #እፍታ ።   ህወሃት ፈቅዶ ስልጣኑን ከለቀቀ በኋላ ጽፌበት አላውቅም። አብዝቼ እሞግተው የነበረ የዞግ የፖለቲካ ድርጅት ነበር። ይህን እኔን የሚውቁ ሁሉ ጠንቅቀው ያውቃሉ። ወዲያው ሥልጣኑን ሲለቅ በወጀብ ያላጉት የነበሩትን ሁሉ ሞግቻለሁ። ስለምን? ፈቅዶ እና ወዶ መንበረ ሥልጣንን በሰላማዊ መንገድ መልቀቅ ሥልጣኔ መሆኑን አምኜ ስለተቀበልኩት። ህወሃት ሥልጣን የለቀቀበት መሠረታዊ ምክንያትም ሚዲያ ላይ እንደሚነገረው አለመሆኑን ጠንቅቄ አውቅም ስለነበር።   ህወሃትን ከልጅነቴ ጀምሮ ነበር እማውቀው። ያ የካቲትን ተንተርሶ የጎንደር ገበሬን አዝመራ ለመዝረፍ ባለዓዋጁ፤ በዘመቻው የሲዊዲን ተራድዖ ድርጅት በገጠር የሠራቸውን፤ የአውራጃ እና የወረዳ ከተሞችን እዬዘረፈ፤ ፈንጅ እዬቀበረ ወገኖቹን ይጨርስ የነበረ ድርጅት በለስ ቀንቶት 27 ዓመት ፀጥ ለጥ አድርጎ መግዛቱን ሳስተውል ይገርመኝ ነበር በእጅጉ። በፌድራሉ እና በህወሃት ጦርነት በአፋር እና በአማራ ክልል እራሱ በዘመኑ ያለማውን የደከመበትን ሲያነድ፤ ሲያወድም፤ ሲዘርፍ አልደነቅም ነበር። ለምን? ተፈጥሮውን ስለማውቅ።    አመጣጡን በህይወት ስለምረዳ። ስለሆነም በሁለቱ ጦርነት ጉዳቱን የግራ ቀኙን ከመዘገብ ውጪ ጦርነቱ ሲጀመር፤ ሲዋገድ፤ ሲጠናቀ...