ልጥፎች

ቀን ሲሰጠው

  ዕውነት ሸሸውም፣ ቅበረውም፣ ተሸሸገውም፣ ሸውደውም ያው እሱነቱን ለብጦት፣ በአርቲፊሻል ቀሽሮት አያውቅም ቀን ሲሰጠው ይበራል፣ ያበራል። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 01/06/2021

ዕውነት ቋንቋ አለው። ዕውነት ግሥ አለው ይገስሳል፣

 ዕውነት ቋንቋ አለው። ዕውነት ግሥ አለው ይገስሳል፣ ዕውነት ስዋሰው አለው ድንጋጌ ችሎትም። ስትስተው የአደባባይ ቄጤማ ያደርግኃል። ያራግፍኃል። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 01/06/2021

#ሦስቱ ሰኔወች #ሦስቱ ጥቅምቶች የአዋሳው 11/11 የምርጫ ሸፍጥ ምህንድስና ነው።

ምስል
  #ሦስቱ ሰኔወች #ሦስቱ ጥቅምቶች የአዋሳው 11/11 የምርጫ ሸፍጥ ምህንድስና ነው።    ዕለተ ማክሰኞ ማዕዶተ ይግቡ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። "ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።" (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯) #ዕፍታ ለትውስታ። #ሦስት ሰኔወች፣ #ሦስት ጥቅምቶች፣ 11/11 ነገረ አዋሳ ለምርጫ ምህንድስና የተሰሩ የሞገድ መጽሐፍ፣ እና የ90 ደቂቃ በኢንተቤ ትወና የተከወነባቸው የገዳ ምርጫ ቦርድን ህጋዊ ዕውቅና ለማሰጠት የተሰናዱ ኦፕሬሽን ናቸው ብዬ በድምፅም በፁሑፍም በተደጋጋሚ ሠርቻለሁኝ። ይህን ሊቀ ትጉኃን አቶ ሰለሞን ኃይሌ የማይወዛወዙ ዶፋን ችለው ከእኔ ብራና ጋር የዘለቁት ቅኑ የብራናዬ ታዳሚዬ ያውቁታል። ግን ሰሚ አልነበረም። እስከዚህ ድረስ በጥልቀት ሄዶ የምርጫ መሰናዶ ስለመደረጉ የተነተነ ተንታኝ አላውቅም። #ሙሉ መሰናዶ እና ሂደቱ። ምርጫን አስበው በሱማሌ ማፈናቀል የሠሩትም ለዴሞግራፊው ስኬት ስለምርጫው ስለመሆኑ ኦህዴድ ስልጣን ከመያዙ በፊት ስለመሆኑም በአፅህኖት ፅፌያለሁ። ከዛም በኋላ "እንሞታታለን እንጂ ቤተ - መንግሥት አንለቅም" የጠቅላይ ሚር አብይ አልነበረም። በጨፌ ስብሰባ ለተነሳው ጥያቄ ዶር ለማ መገርሳ ሲመልሱ ቃሉን ተጠቅመውበታል። የቁም ሰማዕቱ ዶር አብርኃም ዓለሙ ተርጉመውት በርዮት ሚዲያም፣ ዘሃበሻ ላይም ለህትምት በቅቶ ስላነበቤኩ ያም ለምርጫ መሰናዶው ጥጉ እስከምን እንደሆነ ፅፌበታለሁ፣ በድምፅም ሠርቸበታለሁ። ግን አልተስተዋለም። ይህም ብቻ አይደለም እሳት ለብሰው ነፍሳቸውን ስተው እንደ አንድ ወጠጤ ጎረምሳ ጅማታቸው ተገታትሮ እሳት ጎርሰው እሳት ለብሰው ዶር አብይ አህመድ "ጦርነት ውስጥ...

Navigation. Über der Schimmel Führer. Dr. Kereis (PM Abiy Ahmed Ali)

ምስል
  Navigation. Über der Schimmel Führer. • Dr. Kereis (PM Abiy Ahmed Ali) • Thema Notfall News Maker.   Ihre Persönlichkeit ist wie ein Gel. Die Eilmeldungen Schöpfer sind Premierminister Abiy Ahmed. Es ist Ihr Brand. Ihre Leitung ist Schimmel. Lassen Sie mich Ihnen etwas sagen, was Sie nicht wissen. Während der vierjährigen Amtszeit von Premierminister Abiy Ahmed gab es keine offiziellen Neuigkeiten Nachrichten. Es sind vier Jahre voller Eilmeldungen. Eilmeldung: Bis zu fünf pro Tag. Dr. Krise oder Connell Krise Abiy Ahmed haben eine Haushaltskrise. Sie organisieren Krisen; Sie führen eine Krise an und sie machen die Eilmeldungen. Vier Jahren, es gibt keine offiziellen Nachrichten in Äthiopien. Tut weh. Sie sind die Natur der Presse getötet. Sie haben den Mediennatur in Eis verwandelt. Die Nachricht ist nur Tod und Trauer oder Brände oder die Zerstörung von Städten oder Kriege. Der Kapitän ist der Premierminister. Sie führen Äthiopien auf unbekannte Weise. Das äthiopische Volk...

ሰማዕቱ ደብረ ኤልያስ። ግፍ የተፈፀመበት ፃድቁ እና ሐዋርያው ቅዱስ ባዕት።

ምስል
  ሰማዕቱ ደብረ ኤልያስ። ግፍ የተፈፀመበት ፃድቁ እና ሐዋርያው ቅዱስ ባዕት።   "ዬቤትህቅናት በላኝ።" እንዴት ነን? አይዞን። ይህ ክፋ ዘመን ያልፋል። ከሊቀ ትጉኃን ከአቶ ኪሩቤል ዘላዓለም ዬተገኜ ነው። "ደብረ ኤልያስ" "የሐዲስ ዓለማየሁ ፣የዮፍታሔ ንጉሤ፣የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ሃገርየነመልካሙ በጎሰው፣የነዶ/ር ኢሳይያስ የትውልድ ከተማ። ዛሬ በቅዱስ ኤልያስ በዓል ዋዜማ ላይ በሥፍራው ተገኘሁ። አካሄዴ በደብረ ኤልያስ የተሠራውን ሆስፒታል ለደገፉ ምስጋና ለማቅረብ በተደረገው ፕሮግራም ለመሳተፍ ነበር። ይህንን በቀጣይ እመለስበታለሁ። ነገ ታሕሳስ 1 ቀን 2015 የሚከበረውን የቅዱስ ኤልያስን በዓለ ልደት ዋዜማ ለማየት ከታደሉት አንዷ በመሆኔ ከሥራ ባልደረቦቼ ጋር ሆነን ወደ ገዳሙ ተጓዝን። ከየገጠሩ መንደሮች ከሩቅም ከቅርብም ለጠበል ጣዲቅ የሚሆን ምግብ የተያዘበት መሶብና ገምቦ እየያዙ ወደ ቤተክርስቲያን የሚጓዙትን እያየን በአቧራማው መንገድ ወደዚያው አቀናን። እነሆ ታላቁ ገዳም ከነሙሉ ግርማው በኢትዮጵያ ባንዲራ አሸብርቆ በምእመናኑ ደምቆ ጉብ ብሏል። ቅዱስ ኤልያስ በእሳት ሠረገላ በእሳት ፈረሶች ተነጥቆ ወደ ሰማየሰማያት ሲወሰድ የሚያሳየው ውብ ሥዕል በአፀደ ቤተክርስቲያኑ መሐል ጉልህ ሥፍራ ይዟል። " "በመጽሐፍ ቅዱስ የተፃፈው ገድሉ እንደሚያስረዳው "ከደቀ መዝሙሩ ከኤልሳዕ ጋር እየተነጋገሩ ሲሔዱ የእሳት ሠረገላ፣ የእሳት ፈረሶች በመካከላቸው ገቡና ለያዩዋቸው፡፡ ኤልያስም በእሳት ሠረገላ ዐረገ፡፡ ኤልሳዕም የኤልያስን ወደ ሰማይ መወሰድ አይቶ ጮኸ፤ ኤልያስም ልብሱን ከሁለት ከፈለው፡፡ መጠምጠሚያውንም ለኤልሳዕ ጣለለት፡፡ የኤልያስ ጸጋና በረከትም በኤልሳዕ ላይ አደረ" ይላል።...

1% በኢትዮጵያ የፖለቲካ ውክልና የሌለው የገበሬው ምጣት ዘመን 32 ዓመት አስቆጠረ

ምስል
  1% በኢትዮጵያ የፖለቲካ ውክልና የሌለው የገበሬው ምጣት ዘመን 32 ዓመት አስቆጠረ ።    ብዙ በጣም ብዙ ጊዜ ጽፌበታለሁ። ለጠቅላይ ሚር አብይ አህመድም እንደ ሰው ቁጠሩኝ ባሉበት ዘመን ግንቦት 5/2010 መቶ ቀናታቸውን ሳያጠናቅቁ ነበር ወሳኝ ብሄራዊ ጉዳዮችን ነጥብ በነጥብ ዘግቤ ያሳሰብኳቸው። ካሳሰብኳቸው በኽረ ጉዳዮች አንደኛው የገበሬው ጉዳይ ሲሆን ሁለተኛው ደቡብ ሱዳንእና ጋንቤላም ነበሩበት። በጣም በስፋት ነበር የፃፍኩት። የቁቤ ትውል መልሶ በብሄራዊ ስሜት ማነጽም ይገኝበት ነበር። ኢትዮጵያ ዬገበሬወች አገር ሆና ግን ዬኢትዮጵያ ገበሬ የፖለቲካ ውክልና የለውም ሰፊው ማህበረሰብ። ሁለገብ በሆነው የኦነግ ጆኖሳይድ ተጠቂ ከሆነው የአማራ ማህበረሰብም ገበሬው ግንባር ቀደም ነው። ልጆቹን በማገት፤ በጅምላ በመጨፍጨፍ፤ የቤት እንሰሳቱ ላይ ጆኖሳይድ በመፈጸም ሰፊ የሆነ ፀረ መኖር ዘመቻ ሲካሄድ እንሆ 50 ተቆጥሯል። አገር ተደፈረች፤ ሉዓላዊነት ተነካ ሲባልም በገፍ የሚያልቀው የአማራ ገበሬ ነው። ያኮረፈ ሁሉ የሚተመው ምሽግ የሚያደርገውም አማራ ገበሬን ነው። የኢሊባቡር፤ የጋሞ፤ የባሌ፤ የጅማ፤ የአርባምንጭ፤ የአሰላ ወዘተ ጫካወች በሰላም ውለው ሲያድሩ የአማራ ቀዬ ግን ዕድሜ ልክ ስቃይ ብቻ። በዚህ በአምስት አመቱ የሌኮ አብይ አህመድ የቤርሙዳ ትርያንግል ዘመን ጭካኔን፤ አረማዊነትን፤ በዓይነት አይተናል። ዬአማራ ገበሬ ልጆቹን ወደ ትምህርት ቤት እንዳይሄዱ፤ ከቀደመው ከዘመነ ህወሃት እንዳይወልዱ እንዳይከብዱ የማምከን ተግባር ተፈጽሞበታል። በዚህ መከራ ውስጥ ያለፈው ትውልድ ነው አሁን ለንብርብር መከራ እዬተዳረገ ዬሚገኜው። ዬአማራ ገበሬ ምርቱን ተዘዋውሮ እንዳይሸጥ ማዕቀብ ተጥሎበታል። ይህን ሁሉ የቻለ የአማራ ገበሬ አሁን ደግሞ #ማ...

በጎርፍ ውኃ ጠጅ አይጣልም።

ምስል
  " ስምምነትን መቃወም ፍትኃዊ አይደለም።" በትውስት አቅም መፍትሄ አይገኝም። በጎርፍ ውኃ ጠጅ አይጣልም።    አዲስ ዋልታ ሊቃናቱን ያወያዬበት ርዕሰ ጉዳይ ነው። ግን ፍትህ ለዶር አብይ መንግሥት ምንድን ነው? ህግ አውጥቶ ከንቲባ መሾም? ወይንስ በህዝብ የተመረጡ የፓርላማ፤ የምክር ቤት አባላትን ተዳፍሮ ከምክር ቤቱ፤ ከፓርላማው ፈቃድ ውጪ ማሰር እና በበቀል መበቀል ነው? ይህ ይሆን ፍትኃዊነት? እሳቸውን ለስልጣን ያበቃውን የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ መልስ ሳይሰጥ በጭነት 3 አዳዲስ ክልሎችን ፈጥሮ በባጀት እጥረት እያገላበጡ ማሸት? ወይስ ከፋኝ ያለን ማህበረሰብ በማሽን መፍጀት ማሸማቀቅ? ወይንስ አማራ የተባለን ህዝብ አልይህ ብሎ ለብቻው ከልሎ በህግ አውጣ ቀንዳም የበቀል ሾተላይ ሙሉ ዘጠኝ ወር የበቀል ግጥግጠኛ መሆን??? የአማራ እናት እትብትን እና ማህፀንን በጭካኔ መጨፍጨፍ፤ ማሰር ማንገላታት? መቼ ነው የምክክር ኮሚሽኑን እዬነጣጠሉ ጥቃት የሚፈፅሙበት። የሳቸው የጠቅላይ ሚሩ ማለቴ ነው #አስፈንጥሮ መፈጥፈጥ ልማዳቸው ነውና። ከሄሮ ወደ ዜሮ። ግን አዲስ ዋልታ የት ላይ ይሆን ቢሮው??? ጁቢተር ወይንስ ኡራኖስ? አገራዊ ምክክሩ ምን አስቀረ? እሱ እያለ እኮ ነው ደብረ ኤልያስ፤ መራዌ መአት የሚዘንበው? አቅም አልባ አቅም ነን ፋንታዚ ይመስለኛል። በጎርፍ ውኃ ጠጅ አይጣልም። የገረመኝ የደህንነት ዋስትና እንሰጣችኋለን መባሉ ነው። የእናንተ ደህንነት ዋስትና ካገኜ በቂ ነው። መንግሥታዊው ሥውር አካል ዕውቅና ተሰጥቶት በጠራራ ፀሐይ ያሻውን በሚያደርግባት ኢትዮጵያ? "እኛ ዋስትና እንሰጣለን"??? የቅንጡ ጥያቄ ነው በሞት በዓት ኢትዮጵያ። ለመሆኑ ሚዛን ካለ መቼ ነው ፋኖ ኦፊሻል ጥያቄ የቀረበለት። "ተራ ...

#ድርድር እና የሰው ልጅ። ሕይወት #አናጋሪም #ተናጋሪም፤ #አናባቢ #ተነባቢም ናት።

ምስል
  #ድርድር እና የሰው ልጅ። ሕይወት #አናጋሪም #ተናጋሪም ፤ #አናባቢ #ተነባቢም ናት።    (ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱) "የሰው ልጅ መንገድ ያዘጋጃል እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያዘጋጃል።" እጽዋት ቅኖች ናቸው። ቅን ባይሆኑ ፍሬ ሳይሆን ትል ያፈሩ ነበር። እኛስ???? ድርድር የፈጣሪ ሥጦታ ነው። ፈጣሪ ሠራሽም ነው ለእኔ። የመኖር ጥበብ ነው። ከቀስት እንድን ዘንድ የመዳንም ምልክት ነው ለእኔ።። ህይወት ድርድር ናት። የድርድርም ውጤት ናት። የሰው ልጅ እና ድርድር አብረው የተፈጠሩ ናቸው። ድርድሩን ስታፈርሰው ቅጣት ይኖራል። አዳም ከፈጣሪ አምላክ ጋር የነበረውን ድርድር አፍርሶ ነው የሃጢያት መርገም የወረደው። አባ አባት ነውና በፍጥሮቹ ስቃይ ደስተኛ አልነበረምና ስቃዩን እንደ ሰው ሆኖ አይቶ ስቅለትን መረጠ። ስቅለቱ የኃጢያትን ግድግዳ ሰብሮ የእርቅ ድልድዩን ትንሳኤን ሰጠን። የዚህ ትርጉም ማመሳጠር የኔ ፀጋ አይደለም። በቁሙ ንባቡ የሰማያዊ ግርማ ሞገስ ድርድር ሂደቱ ከተሰጠን ስጦታወች የመኖር ጥበብ ውስጥ አንዱ ነው። ለድርድር ልኩ ማስተዋል፤ ጥሞና፤ ፀሎት እና ፈቃደኝነት ነው። ሦስተኛው የግጥም መዐሐፌ "ውል" ነው እርዕሱ። #ውል ። የድርድር አስኳል ነው። ውል ላልቶ ሲነበብ ትዝታ፦ ሽውታ ይሆናል። ሽውታም በራሱ ጠብቆ እና ላልቶ ሲነበብ የራሱ ትርጉም አለው። ሽውታ ቅፅበታዊነትንም ያመለክታል እንደማለት። ውል ዘመኑ በትርፍ ስሌት የተመሰጠረ ነው። ወይንም ሰጥቶ በቀበል የእኩልዮሽ መርህ። እናት እና ልጅ ውል አላቸው። እንቁላሉ ሰው ለመን ጽንሱ ሀሌት ካለበት ጀምሮ። በመኖር ውስጥ ውል - ድርድር - ስምምነት የሌለበት፤ ክርክር - ሙግት የሌለበት የመኖር ዘይቤ አይገኝም። ዕብን የሚባሉት እንሰሳት ውሻ፤ ደሮ፤ ፈረስ ...