ልጥፎች
#አሜን። ዓለም የሰላም አንባ ትሆን ዘንድ የአሜሪካን ግሎባል ምርጫ እግዚአብሄር በሰላም ያስፈጽመው። አሜን።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
#አሜን ። ዓለም የሰላም አንባ ትሆን ዘንድ የአሜሪካን ግሎባል ምርጫ እግዚአብሄር በሰላም ያስፈጽመው። አሜን። "አድርገህልኛል እና ለዘላለም አመሰግንኃለሁ፦ በቅዱሳንህም ዘንድ፦ መልካም ነውና ስምህን ተስፋ አደርጋለሁ " (መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፶፩ ቁጥር፱ ) 1) እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ መልዕክት ይዞ ይወለዳል። 2) እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ ጥሪ ይዞ ይወለዳል። 3) እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ መክሊት ወይንም ስጦታ ይዞ ይወለዳል። የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ወ/ ሮ ካሚላ ሃሪስ ( ኮሞላ ሃሪስም) ይህን አጣምረው ተወልደዋል ብዬ አምናለሁኝ። በእኛ አገር አባባል "ልጅ እና ጢስ መውጫው አይታወቅም" እንዲሉ። ጤና ይስጥልኝ የማከብራችሁ ውድ ቤተሰቦቼ? እንዴት ሰነበታችሁልኝ? በበዛ #አርምሞ እና በሰከነ #ጥሞና ልንከታተለው የሚገባው ለእኔ ዓለም ዓቀፋ የኢትዮጵያ፤ የአፍሪካ ቀንድ፤ የመካከለኛው ምስራቅ አፍሪካ፤ የእስያ፥ የቻይና እና የታይዋን፤ የአህጉራችን የአፍሪካ፤ የእስራኤል- የጋዛ፤ የሊባኖስ - የኢራን፤ የራሽያ - የዩክሬን፤ የአውሮፓ ህብረት፤ የአፍሪካ ህብረት ጉዳይ፦ የአሜሪካዊው የ2024 የምርጫ ሂደት ጋር ህሊና ላለው የሰው ልጅ ሁሉ መንፈስን አንቅቶ ሊከታተለው የሚገባ ጉልላታዊ #ፒላር ጉዳይ ይመስለኛል። የአሜሪካ ጠቅላላ የታች እስከ ላይ የሚካሄደው ሥልጡን፤ የተደራጀ፤ በቅጡ ኮኦርድኔት የተደረገው የምርጫ ሂደት ጉዳዩ ለእኔ #ቅንጦት አይደለም። ብዙ ግሎባል የህይወት፤ የተፈጥሮ መስኮች ላይ ተጽዕኖም አሳዳሪ ነው። ጉዳዩ #የጫጉላ የሙሽርነት ሽርሽር አይደለም። ኢትዮጵያ በዴሞክራሲ እጦት ሙሉ 50 ዓመታት እንደምን ትውልዷ እዬታጨደ እንዳለ፤ ምን ያህል የኢትዮጵያ እናቶች ...
Lualawi ሉዓላዊ-የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እና የምርጫ ሥርዓት -ከፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ ጋር
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
የፍቅር ተፈጥሮ ሙያ ሊሆን ይገባል። Die Natur der Liebe sollte ein Beruf sein. Aber wie?
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድን "በብልጽግና" መንደር የሆነ ነገር #ቢፈጠር ማን ይተካቸዋል? ለሚለው #ጠቅላዩ መልስ ሰጥተዋል ብዬ አስባለሁኝ።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድን "በብልጽግና" መንደር የሆነ ነገር #ቢፈጠር ማን ይተካቸዋል? ለሚለው #ጠቅላዩ መልስ ሰጥተዋል ብዬ አስባለሁኝ። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" የህወሃት ህገ - መንግሥት ተጥሶ ከምል #ተጠቅጥቆ ፦ የፓርላማው ጉባኤ ኃላፊነት እና ተጠያቂነት #ጭብጥብጥ ተደርጎ በራሳቸው ፈቃድ በአናርኪዝም መርኽ ሚኒስተሮቹን ሿሿሙ ---:ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ። ለሚያረገርገው ካቤኒያቸው በዬጊዜው ሲያነሱ፤ ሚኒስተሮቻቸውን ሲያሽቀነጥሩ፤ በዲሞሽን ሲያንበሸብሹ ባሊህ ባይ የላትም ኢትዮጵያ። #ሃግ የሚልም የለም። በስንት ሽልንግ #ጦቢያን ዶር አብይ አህመድ አሊ እንደ ሸመቷት አይታወቅም። እንዲያ ወፍ የቀናው ዕለት በሥርዓተ አልበኝነት ህግ ጥሰው የሹመት ዓዋጁን ያስነኩታል። በሳቸው #የተጨባበጠው ፓርላማም ባሰኛቸው ቀን #ይሁንታ ይሰጥላቸዋል። መታደል ይባል መገደል አላውቅም። ኢንጂነር አንሻን የመከላከያ ሚር አደረጓቸው። ወዲያው በዲሞሽን ከሆነ ቦታ ወስደው ሸጎጧቸው። በዛ ሰሞን ደግሞ ቀኑ ላልታወቀ ጊዜ ተልዕኮው ለምን እንደሆን ባናውቅም ዶር አብርኃም በላይ ተነስተው ኢንጂነር አንሻ የመከላከያ ሚር ሆነው ተሹመው አይተናል። የሚባንን ጉድ። ወደ ቀደመው ጉዳዬ ስመለስ በዚህኛው የሹመት ሂደት እንዲያው በመፈንቅል ይሁን፦ በተፈጥሮ ሁኔታ አንድ ነገር ቢፈጠር ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድን ማን በብልጽግና ሠፈር ይተካል ለሚለው የዲፕሎማሲው ማህበረሰብ ስጋት፦ እራሳቸው ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ መልስ ሰጥተዋል። ቀዳማዊ እመቤትነቱም በፍትህ ሚኒስተርነት ቀድመው ቁብ አድርገዋል። የህግ ባለሙያው ዶር ገዲወን ጢሞቲወስ ከዲፕሎማሲው ማህበረሰብ ጋር ይተዋወቁ ዘንድ ሁለተኛ ዕድል ...
የጃርት ጉባኤ ርደት። Poesie By Sergute Selassie Der Mensch wurde zum Guten gesc...
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
የጃርት ጉባኤ ርደት *** ባድም በጃርት ተሰቅዛ ... በአረማሞ አራሙቻ ናውዛ። እህህን ሰንቃ ደንዝዛ ... ሰቀቀን ታጥቃ አርግዛ። በ’ሬት ጨጎጎት ተደልዛ ... መቀነት በእሾህ ተገንዛ ... ቁም ስቅሏን አዬች - ይህው በልዛ። ጃርተ - ምርት፣ እሾህ ... ፍጥረተ - ነገሯ፣ ውጋት። ... በበቀል ተዋቅራ በደም ተቋድሳ በደጋን ታምሳ ተደቁሳ። እሾህ አዘራች መልሳ .. የጃርት ገላ መላልሳ። ህልም ራዕዩ ምልግልግ የላንቁሶ ውሃ ዝልግልግ። ጃርተ- ልብ፣ የእሾህ ልግ የአሜኬላ የቋሳ ድግዳግ። ጃርትስ አሰኛት የበቀል ብቅል የአብሾ ጠላ ዝልል። ቋቱ የማያውቅ ግልግል የጃርት ህሊና የውጋት ግልገል ... ... ሰባራ ገል። እሾህስ አልቦ የለም ጃርት ከዘረ እሾህ የለም ምርት። የጠቀራ ናስ ሃሞት ዙሪያ - ገባው፣ ማት ... ... ህልፈት የሐገር ቅብረት። አንተ አለህ እና በቤትህ ትሰማለህም ታያለህም የጃርተን-ትእቢት፤... የቀን ጥሰትን የበቀል አምላክ አትለፋት የሕዝብን ዕንባ ህማማት ... እ!-እ!-እ!-እ!-እ!-እ!-እ!-እ-! እም-እ-እ-እእ ግንቦት 20 ቀን 2000 ዓ.ም አንደልፊንገን-ሲዊዘርላንድ