ልጥፎች

"እንዳያማም ጥራው፤ እንዳይበላም ግፋው።" ለሰብ ትርታ #መደንገጣችሁን እስከ ምን ይጠበቅ?

  "እንዳያማም ጥራው፤ እንዳይበላም ግፋው።" ለሰብ ትርታ #መደንገጣችሁን እስከ ምን ይጠበቅ?   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   • ቅኒትን፤ የልቅና ባለቤቷን፤ የዊዝደም ጉልላቷን ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ደረጃዋ ይህ ነውን?   https://www.youtube.com/watch?v=uBHU_VSzGhQ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተሰጠ መግለጫ    #ምዕራፍ ፲፱።   ከኢትዮጵያ መንግሥት የተሰጠውን መግለጫ አዳመጥኩት። አገርን - በቅንነቷ፤ በዊዝደሟ - ልዕልና፤ በመንፈስ #ንጽህናዋ ልክ መሠረት ያስያዘች ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ #ዕንባ በምን መልኩ እንደሚታይ ሙሉ ፰ ዓመት አይቻለሁ። አድምጫለሁኝ። ለእኔ ምንም አዲስ ነገር የለውም። ምን አልባት "እንዳያማም ጥራው …"የመግለጫው ዓይነት ይሆናል አዲሱ።   በሌላ በኩል ብሄራዊት፤ ዓለም ዓቀፋዊት የሆነችው ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶም ሊቃናት፤ ሊሂቃን፤ የተደራጄ መዋቅር፤ ቀኖና እና ዶግማ ያላት ተቋማዊ ሃይማኖት ናት።   የቅድስቷ #ነቁጧ ብቻ የሚስጢር ዲካዋ ሊሠፈርም ሊለካም አይችልም። ፈተናዋም የዚያኑ ያህል ዲካ የለሽ ነው። እራሷን የቻለች፤ ሁሉ ያላት፤ የምትችል ሆና ግን የዝምታዋ #መንገሥ ልጆቿ የየለት ሰማዕትነት፤ የተቋማቷ ስደት፤ የሁለመናዋ ተከላካይ አልባ መደፈር በበዛ ትዕግሥት መያዟ ፈተናዋ መቋጫ አጣ። የእኛ የታናናሾቿ ዝምታም ልኳ፤ ልዕልናዋ፤ አቅሟ፤ ልቅናዋ የማይደረስበት በመሆኑ በደል ሲጠናባት ዕንባችን አፍስሰን ተማጥኗችን ለላይኛው እንልካለን።   አጽናኟ፤ አይዞሽ ባዮዋ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ፤ እንዲህ ለራሷ መሆን ሲሳናት ማዬት እጅግ ያሳዝናል። በማናቸውም ብ...

#ሙሉዑነትን መናፈቅ ጤነኝነት ነው። የእቴጌ ትግራይ ንጥረ - ነገር #ሲጎድልስ? ኢትዮጵያም፤ ኢትዮጵያዊነትም #የወል ሥም ነው። ባለቤቱም አንድ የፖለቲካ ድርጅት ሳይሆን #ህዝብ ነው።

  • #ሙሉዑነትን መናፈቅ ጤነኝነት ነው። የእቴጌ ትግራይ ንጥረ - ነገር #ሲጎድልስ ?   ኢትዮጵያም፤ ኢትዮጵያዊነትም #የወል ሥም ነው። ባለቤቱም አንድ የፖለቲካ ድርጅት ሳይሆን #ህዝብ ነው።   "አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።"   #ምዕራፍ ፲፱።   https://www.youtube.com/watch?v=evR6jYDJ7B4 «ኢትዮጵያ መርጣለች!» https://www.youtube.com/watch?v=lTQ5Q-CPcxk «ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው !» https://www.youtube.com/watch?v=EXtFzg7msAQ «ኢትዮጵያ መርጣለች፣ ጸንታለች፣ አሸንፋለችVETV | EBC | EBCDOTSTREAM»   #ነገረ ዕርዕስ እንደ በር።    ዕርስ ጥምን ያረካል። ግን ዕውነት ከሆነ ----- ብቻ። ዕርዕስ ይክሳል። ግን ዕውነትን የማያቆስል ወይንም ዕዳ የማያስከፈል -------ከሆነ። ዕርዕስ ተስፋ ይሰጣል። ግን ዕውነትን የማይፋለም -------ከሆነ። ዕርዕስ ማግስትን ያበስራል። ግን ዕውነትን ባለአንጣ ------ካላደረገ።   * ኢትዮጵያ መረጠች።" *** ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው።" ****ኢትዮጵያ መርጣለች፤ ጸንታለች፤ አሸንፋለች።" እነኝህ ዕርዕሶች በተደጋጋሚ አየኋቸው። ሙሉነትን መናፈቅ ጤነኝነት ነው። ደስ ይላልም። ግን የመሻት ላዕላይ እና ታህታይ መዋቅሩ ማረግረግ እንዳይኖርበት ጥንቃቄን ይጠይቃል።   ተችሎ ምርጫ በተካሄደባቸው ቦታወች ሁሉ ዘመኑ ጥሩ ነው ተከታትየዋለሁኝ። ምርጫው ተካሂዷል። በተጨማሪነት ዘመናይ የሆኑ መሻቶችን ተመልክቻለሁኝ። "ፍትኃዊ፤ ነፃ፤ አሳታፊ፤ በጣም ቄንጤኛው ዴሞክራሲያዊ" ይላል። ዴሞክራሲ ወጫችሁን ችዬ ያለእናንተ ድካም በእኔው ጊዜ አንቱ ላሰኛችሁ ብሎ ...

#ኡራኖስ ላይ የሚኖረው የኢትዮጵያ ሴቶች ፌድሬሽን መግለጫ?

ምስል
  #ኡራኖስ ላይ የሚኖረው የኢትዮጵያ ሴቶች ፌድሬሽን መግለጫ?   https://www.youtube.com/watch?v=Wz_GsvGSA6I የፌዴሬሽኑ መግለጫ ሕዝብ ያሳየው ታማኝነትና ቁርጠኝነት   "አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።"   #እንዲህ የሚባል ተቋም #ኢትዮጵያ አላትን?   የምር ነው በትህትና የምጠይቀው? የት የነበረ ይሆን ይህ ተቋም የሚኖረው ጁቢተር ወይንስ ኡራኖስ ማርስ ወይንስ ሜርኩሪ ላይ? የኢትዮጵያ እናቶች ሲከፋቸው፤ ሲያለቅሱ፤ በተፈጥሮ ይሁን በሰው ሠራሽ ችግር ሲገረፋ የት ነበሩ? በግፍ ሲታገቱ፤ አራስ ቤት ህይወታቸው ሲያልፍ፤ ተፈናቅለው ሲንከራተቱ? ሲርባቸው - ሲጠማቸው፤ ሲታረዙ እራፊ ሲያጡ ተቋሙ የት ነበር? ዛሬ ለሠርግ እንደምን ብቅ አለ ደፍሮ?    ኢትዮጵያ ለዚህ በምንም ደረጃ ላለ ተቋም #በጀት መድባለችን? በውነት እምዬ በጣም ደልቷቷል ማለት ነው። የእናቶች ዕንባ እኮ የቧንቧ ውሃ አይደለም። በዓለም ውዱ የዕንባ ጠብታ ነው።    ከኢትዮጵያ እናቶች ዕንባ መከፋት ጎን ቆሞ ፊት ለፊት ወጥቶ ያልሞገተ፤ የግንባር ስጋ መሆን ያልፈቀደ ያልተገባ ሥያሜን ይዞ ሚዲያ ላይ የሚወጣ ምን ይባል ይሆን? የወጣቶችን አይቻለሁኝ። የእነሱ ዕድሜያዊ ጉዳይ ስላለበት ዘልየዋለሁኝ። ሴቶች ግን በጥቂቱ ………   1) የአገር ኃላፊነት፤ 2) የትውልድ ኃላፊነት፤ 3) የአደራ ኃላፊነት፤ 4) የታሪክ ኃላፊነት፤ 5) #የሰላም ኃላፊነት፤ 6) #የፍቅር ኃላፊነት፤ 7) የእናታዊነት ሁለገብ ኃላፊነት፤ እናታዊነት ከፖለቲካ ርዕዮት በላይ ነው።  ስምንተኛ) የተፈጥሯዊነት ኃላፊነት ያለባቸው ናቸው።   ለእኛ ለሴቶች የተሰጠን ሰማያዊ ኃላፊነት #የሰብዐዊ መብት ተሟጋች...

"ጽድቁስ ቀርቶ በወጉ በኮነነኝ።" ተናፋቂው ባህርዳር በብልጽግና ምን አገኜ???

ምስል
  "ጽድቁስ ቀርቶ በወጉ በኮነነኝ።" ተናፋቂው ባህርዳር በብልጽግና ምን አገኜ???   "ባሕር ዳር ከተማ ዐይን ገላጭ ፕሮጀክቶች የተሠሩላት በብልጽግና ፓርቲ ነው" ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ" መሃከነ፤ እግዚዖ ተሳህለነ። አሜን።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   ምዕራፍ ፲፱።       #እፍታ ።   https://www.youtube.com/watch?v=LGPQf4ShXaA "ባሕር ዳር ከተማ ዐይን ገላጭ ፕሮጀክቶች የተሠሩላት በብልጽግና ፓርቲ ነው" ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ"   እንዴት ነን? ጭምት ናቸው ሲባል እሰማለሁኝ። የዛሬን አያድርገውና መስኪ ይህን ጽፋው ነበር የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት ሳሉ። ዛሬ ዘለግ ያለ ሙግት "ብልጽግናን መምረጥ ነገን መምረጥ ነው" ሲሉም ሙግት ቢጤ ነበረኝ ከምክትል ጠቅላይ ሚሩ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ጋራ። ተጥፏልም።    የዘገየሁት ለምርጫው ሳንክ መሆን ባለመፈለጌ ነው። አስክኖ እና አስተውሎ ማየት የብትን አፈር ለማኝነትን ይታደጋል። የዘመኑ የዓለም ዓቀፍ የፖለቲካ ባህሪንም በቅጡ ማድመጥ ይገባል። አገር ሊኖር ይገባል ለማሄስ፤ ለመሞገት።    ለእኔ ቁጥር ፩ የኢትዮጵያ መኖር እንደ አንድ አፍሪካዊት አገር ወሳኝ ጉዳይ ነው። ለዚህም ነው ሰላማዊ ተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶችን በምርጫ ተሳትፎ ያደርጉ ዘንድ በትህትና ያሳሰብኩት። ኢትዮጵያ እንደ አገር አናርኪያዊ ሁነት ገጥሟት ስለማያውቅ ላታውቀው ትችል ይሆናል።    #አናርኪዝም ከፋመ ጦርነት የባሳ አሰቃቂ ክስተት ነው። ለአገሬ ለኢትዮጵያ ከዚህ ፈጣሪዬ እንዲሰውራት ምኞቴ ነው። የመጸለይ አቅሜ አናሳ ቢሆንም - ሁልጊዜ አገሬን...