እኔ ሥርጉተ©ሥላሴ ብልፄውን ስለምሞግት የደፂን ህወሃት ልደግፍ #አልችልም። ፈፅሞ! መቼውንም! ለምንግዜም!
እኔ ሥርጉተ©ሥላሴ ብልፄውን ስለምሞግት የደፂን ህወሃት ልደግፍ #አልችልም ። ፈፅሞ! መቼውንም! ለምንግዜም! "እግዚአብሄርን መፍራት ክብር ነው፤ የሚያስመካ ተድላም፤ ደስታም ነው፤ ተድላ ደስታ ይሰጣል፤ ደስም ያሰኛል፤ በሕይወት የሚኖሩበትን ዘመን ያበዛል።" #ምዕራፍ ፲፱። #ጠብታ ። ህወሃት የሚለው የዞግ የፖለቲካ ድርጅት ስለተከፋፈለ፤ አንደኛውን ክንፍ #የደፂ ህወሃት ወይንም #ደፂዝም ማለት ይገባል። አሁን ባለው ፖለቲካዊ ጭብጥ በቀደመው ሥም መጥራት የተገባ አይመስለኝም። ህወሃት ሆነው ግን የህወሃትን አሁናዊ #ትወና ሊጋሩ የማይፈልጉ ወገኖች ስላሉ። ወጣትነቴን አላውቀውም። ስለእኔ አስቤ አላውቅም። እኔን "የእኔ" አጀንዳ አድርጌም አላውቅም። በማገኛት አጋጣሚ ሙሉ መንፈሴን ከእኔ ውጭ ላሉ ሰብዕናወች አስባለሁ፤ እጨነቃለሁ፤ የምችለውን አደርጋለሁኝ። ዘመኔን ቅርጥም አድርጎ የበላው ደግሞ አውራው ህወሃት እና #ጨካኙ ጉዞው ነበር። ብዙ በጣም ብዙ አቅሜን ያለ ገደብ በጸረ - ህወሃት ትግል ሰጥቻለሁኝ። በቤተሰብ ይሁን በማህበራዊ ጉዳይም "ለእኔ" የሚል ሁነት ቀድሞብኝ አያውቅም። ስለሆነም የድምጽ አልባወቹ የኢትዮጵያ እናቶች #ዕንባ መሪዬ፤ መስመሬ መርሆዬ ነው። ፈጣሪ እረድቶን በራሱ በአምላካችን ጥበብ ፈቅዶ ህወሃት እራሱን ከመንበረ መንግሥቱ ሸኜ። ይህ ትንግርት፤ ታምር ስለነበረ ከዚህ በኋላ በህወሃት ላይ የሚነሱ ወቀሳወች መበርከት የለባቸውም ባይም ነበርኩኝ። ህወሃት የአማራ ክልል እና አፋርን እስከ ወረረባት ቅጽበት ድረስ፤ የኢትዮጵያ ዜጎችን ቁስለት ከዓለም ዓቀፍ ሚዲያ የማገኘውን መረጃ #በእኩልነት ዘገብኩኝ። ...