#አይበገሬው ወጣት Yonas Mequanint በጥሪው ውስጥ። የትውልዱ ነገር ይገደኛል - እኔን። ይመለከተኛልም - እኔኑ።

 

#አይበገሬው ወጣት በጥሪው ውስጥ። የትውልዱ ነገር ይገደኛል - እኔን። ይመለከተኛልም - እኔኑ።
"አድርገህልኛል እና አመሰግንሃለሁኝ።"
 
እንዴት ናችሁ የእኔወቹ??? 
 
ያልተጠበቀ፤ የማይጠበቅ፤ የማይታሰብ፤ ግን ፈጣሪ አስቦ የጀመረው የዕውነተኛ ታሪክ ፍሰት። ኪኖ ይመስላል። ነጮቹ ቢያገኙት ፊልም ይሠሩታል። በተመስጦ፤ በተደሞ፤ በአትኩሮት፤ #በፍጹም ትዕግስት የተከታተልኩት ዕውነተኛ ታሪክ። ጓድ አበበ በዳዳ የሚባል አለቃ ነበረኝ። ከእለታት በአንዱ ቀን ጋሼ አቤ ከጎንደር ወደ ደቡብ ኦሞ ክፍለ አገር ፩ኛ የኢሠፓ ጸሐፊነት ተዛወረ። 
 
በሌላኛው ቀን ደግሞ ለማዕከላዊ ኮሜቴ ስብሰባ ጸሐፊወች ፬ኪሎ ተገናኙ። ወደ ፭ የሚሆኑ ፩ኛ ፀሐፊወች ያውቁኙ ነበር በአካል። በኮርሰኝነት ወይንም በሥራ። ሞገደኛ ነበርኩኝ። ደፋር ነበርኩኝ። ትጉህ ነበርኩኝ ዲስፕሊንድ ነበርኩ። ከቤት ወደ ሥራ፤ ከሥራ ወደቤት። በቃ። እና የመሪወቼ #አጀንዳ እኔ ሆንኩኝ። የጋራ ሊንክ።
 
ጋሼ አቤ እረፍት ወጥተው ቡና በጣም ይወዳሉ ሁሎችም፤ ቡና እየጠጣ ደብዳቤ እዛው ላይ ሆኖ ፃፈልኝ። ስዳር ጎንደር ተመልሶ መጥቶ እንደሚያጅበኝ እና ሌሎችንም ጉዳዮች አክሎ ፃፈልኝ። ከፃፈልኝ ውስጥ ከብረት ቁርጥራጭ የተሠራ ጥንካሬሽ …… ይል ነበር። በልጅ ዮናስ ያዬሁት ጥንካሬ፤ ብርታት፤ #የውሳኔ አቅም፤ #ሁለገብነት ጋሼ አቤ ለእኔ የሰጠውን ከብረት ቁርጥራጭ የተሠራሽ ያለውን ለዮኒ ለመስጠት ወሰንኩኝ። 
 
አወን ልጅ ዮናስ መኳንንት ከብረት #ቁርጥራጭ የተሠራ ማንነትን የገነባ #ጀግና ልጅ ነው። "ከተሠራንበት ርቀናል፤ ያልሞተ ሰው ሃሳብ ይቀይራል፤ ከጎርጎራ ውጪ ለ?የት አለ ምድር ለእኔ? የምንጀምረውን እንጂ የምንጨርስበትን ማን ያውቀዋል? ደስታን ለማጣት አርት ውስጥ አይገባም፤ የቀደመ ዓይን ከሌለው ምን አርት ውስጥ አለ ያሰኛል? ለአርት ሰብዕና #መሳቅ ይከብደዋል፤ እምወዳትን ባጣ፤ ለማግባት ብዬ #እማልወዳትን አላገባም፤ ጎርጎራ ለእኔ ሙሉዑ ናት፤ #መጠላላት #ያደክማል …… "እኛን" የሚል ቃል ፖሊስ ስልጠና ላይ አይፈልጉም " ጥቂቶቹ በስተመጨረሻ የኮለምኳቸው በኽረ ጉዳዮች ናቸው። 
 
ሆድ ሲብሰኝ፤ ሲከፋኝ፤ ዓውደ ዓመት ሲመጣ ሲመጣ፤ ልፋቴ ፈሶ ሲቀር ወይንም በጎነቴ ዕሴት አልባ ሲሆን፤ ሆዴን ባርባር ሲለው እንዲህ ዓይነት ጥንካሬ #ይጠግነኛል። ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ፍዝ ቀኖችን የምጋፈጥበት #ፌርማታዬ ይሆናል። ይህ ቃለ ምልልስ። በውነቱ አልጠገብኩትም። ነገረ አስትሮኖሚም ዝንባሌ ስላለኝ የጁቢተር ልጅ ይመስለኛል ልጅ ዮናስ። ግልጽ፤ ቀጥተኛ፤ አዛኝ፤ ተፈጥሮ ወዳጅ፤ እንሰሳትን የሚወድ፤ ለእንሰሳት ልዩ አክብሮት ያለው ኢትዮጵያም ያልከበደችው ዕውነት የሆነ ወጣት። ብዙ አስተምሮኛል። ይባረክ።
 አሜን። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
 
 
 https://www.youtube.com/watch?v=2A7DtG7iMIM
 
 

"ዮናስ መኳንንት ፡ የአያቶቼን ርስት ላቀና ነው የሄድኩት" Yonas Mequanint

ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
 
 
ሥርጉትሻ 14/02/2926
ዮናስ መኳንንት ፡ የአያቶቼን ርስት ላቀና ነው የሄድኩት | Yonas Mequanint

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።