የምዕት ፈርጧን አርቲስት ኢፋ /ኢቢታ/ ፔሩን "በተባረከች አገር ለተባረከ ትወልድ" ተስፋ ውስጥ።
እንኳን ደህና መጡልኝ። ለውጡ እንደ ዝናሽ ንዑድ መንፈስ የእኩልነት ማህደር ቢሆንልን። „እግዚአብሄር ለሰው ልጆች ይደክሙበት ዘንድ የሰጣቸውን ጥረት አይቻለሁ።“ መጽሐፈ መክብብ ፫ ቁጥር ፲ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 18.02.2019 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። ጥሞና መልካምነቱ ብዙ ነገርን ከውስጥ ለማዬት ይረዳል። ሳተናው ድህረ ገጽ ስገባ የማነባቸው፤ ዩቱብ ስከፍት የማደምጣቸው ነገሮች መከፋቴን አሳየሉበት። ስለምን ብትሉኝ በ2008 ላይ የነበረው ድቅድቅ ጨለማ እና „ሰከን በል“ የአርቲስት ይሁኔ በላይ የህሊና ተቋም እኔን ያልተለመዱ እርምጃዎች ያስወሰዱኝ የጭንቅ ወቅት ነበሩና። እነዛ ያልተለመዱ እርምጃዎቼ ጥቋቁር ሰለነበሩ ያን መልክ ለማሳያዝ ደግሞ የግድ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ወደ እጩ ጠ/ሚር ሲመጡ ማቃናት ነበረብኝ። እናም በድፍረት ያን ቁስለቴን የሚሸር ቀን ፊት ለፊት ዋዜማ ላይ ነው ብዬ የቀደመውን የጭንቀት መንፈስ የሚረገብ ጹሑፍ ጻፍኩኝ እና ለኩኝ። ኢህአዴግ ውስጥ የነበረው የለወጥ አዬር በጤናዳምነት በቅንነት ነው የተመለከትኩትና። ያተስፋዬ በ ኢህዴግ ውስጥ ከተሳካ ያን የመሰለ ምሬት ከእንግዲህ ለመላክ አላማሰቤን ስስበው እራሱ ጤናዬን መለሰለኝ። የዛሬውም የቀድሞዎችም ኢህአዴግ ላይ የነበረው ጠባሳ መሻሪያው የተስፋ ዘመን መጣ በሚል በትልቁ ሰፋ አድርጌ መንፈሴን እርጋ አልኩት። በዛ የውስጥ ቁስለት ውስጥ የታደሙ መንፈሶች እንደ እኔው ተስፋ ያደርጉ ዘንድ ደግሜ መማጸን ስለነበረብኝ ነው የማቃኛ ሌላ ደብዳቤ የጻፍኩት ለሚያደምጡኝ። አሁን የምሰማው የማዬው የማዳምጠው ደግሞ ለዬት እያለብኝ ነው። ዛሬ ጥዋት ከቀደመት አንጋፋ ጋዜጠኞች ውስጥ አቶ ...