ልጥፎች

• #ትህትናዊ ዓለም ለመፍጠር የተጉ የዘመናችን ጀግና! #ጀግንነትን #በጀግንነት #ቀደሱት ፓለቲከኛዋ ክብርት ማሪያ ኩሪያ ማቻዶ! ብሩክ! # ዓለማችን ከኖቤል የሽልማት ተቋም ጋር የሚለካካ፤ ሚዛን አስጠባቂ፤ ከፖለቲካ ነፃ የሆነ #አዲስ የሽልማት ተቋም ልትፈጥር ይገባል።

  • #ትህትናዊ ዓለም ለመፍጠር የተጉ የዘመናችን ጀግና! #ጀግንነትን #በጀግንነት #ቀደሱት ፓለቲከኛዋ ክብርት ማሪያ ኩሪያ ማቻዶ! ብሩክ! # ዓለማችን ከኖቤል የሽልማት ተቋም ጋር የሚለካካ፤ ሚዛን አስጠባቂ፤ ከፖለቲካ ነፃ የሆነ #አዲስ የሽልማት ተቋም ልትፈጥር ይገባል።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   #ምዕራፍ ፲፯     #መቅድም ።   ህውከትም፤ ጩኽትም፤ ዕልቂትም፤ ውድመትም ባባከናት ዓለማችን እረፍት የሚሰጥ #ትህትናዊ ጉዞ እያዬሁ ነው። የትራንፒዝም ብርቱ ደጋፊ የነበሩ የአንድ ወጣት አሜሪካዊ ሰማዕት ህልፈትን አስመልክቶ ክብርት ባለቤታቸው፤ በመግደል ወንጀል ለተጠረጠረው ወገናቸው #የምህረት ቃል ያሰሙት በቅርቡ ነበር። ዛሬ ደግሞ ሌላ ትሁት፤ ፍጹም ቅን የሆነ ውስኔ ከቬንዞላዊቷ የፖለቲካ መሪ ክብርት ማሪያ ኮሪና ማቻዶ ተደመጠ።    ክብርቷ ከዘንድሮ የኖቤል ተሸላሚ ለመሆን ከታጩት ውስጥ አንዷ ነበሩ። አሸነፋ። ማሸነፋቸውን፤ ከደስታ በላይ ሐሤታቸውን፤ ግርማቸውን፤ ሞገሳቸውን፤ ተቀባይነታቸውን ለቬንዞላ ህዝብ እና ለተከበሩ ፕሬዚዳንት ዶናል ትራንፕ እንዲሆን ወሰኑ፤ ፈቀዱ። መሪነት ይሄ ነው። ከራስ ጥቅም፤ ከራስ ክብር የሚበልጠውን መዝኖ ጸጋውን ለሚበልጥ ሰብዕና ወይንም ዓላማ፤ ወይንም ግብ ፈቅዶ መስጠት። ታምራት እና ታላቅ ግሎባል የምሥራችም ነው ለቤተ ሰላም ቤተኞች።   #በምልሰት ስሜቴን ሳጋራ።   ወደ ኋላ ተመልሼ የአርጀንቲናዋን ቀዳማዊት እመቤትን ኢፋ / ኢቢታ ፔሩን አሰብኩኝ። በሳቸው ሁልጊዜ እንደተመሰጥኩ ነው። ከጋብቻ ውጪ በመወለዳቸው ነውር በነበረበት በዛን ወቅት ከአንድ ዝቅተኛ ቤተሰብ ነበር የተወለዱት። እናታቸው ተሳቀው ነበር ያሳደጓቸ...

#ሰላም #ይመረቅልን። አሜን። #ይቅናን። አሜን።

  #ሰላም #ይመረቅልን ። አሜን። # ይቅናን። አሜን።   የዛሬ ሁለት ዓመት ለእኛ የፆመ ጽጌ በር ዕለት መስከረም 26፣ በአውሮፓውያኑ #ጥቅምት ፯ ቀን ማት እስራኤል ላይ በጋዛ አጥቂወች ተፈጸመ።    ያን ዕለት ተከትሎ በግራ ቀኙ ስንት ህይወት፣ ስንት መኖር፣ ስንት ተስፋ #አረረ ? መፈጠር ተኮማተረ። ደም ፈሰሰ። ዕንባ ፈሰሰ። ዛሬ በዚህች #ቅጽበት ሁለቱ በአገረ ግብጽ በተከበሩ ፕሬዚዳንት ትራፕ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት አነሳሽነት ድርድር ላይ ናቸው። ይቅናቸው። አሜን።   ጦርነት ትውልድ ሊረከብ አይገባም። ጦርነት ትውፊት ሊሆን አይገባም። ስጋት የትውልድ መኖርን ሊያሰቃየው አይገባም። ፍልስጤማውያን #አገር #ይገባቸዋል ።    የእስራኤልን አገርነትንም ፍልስጤማውያን እና አጋሮቻቸው #ሊቀበሉት ይገባል። በመጨረሻም፣ ስምምነቱ ያለ #እንከን ይፈጸም ዘንድ ምኞቴ ነው።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፈጠርልኝ።" አሜን።   ይህ የጭስ ፎቶ አንድ ልጅ ሰላምን እየለመነ ይመስለኛል። በወቅቱ ዜና እያዳመጥኩ የቀረጽኩት ነው። እግዚአብሄር አምላክ፣ አላህ ለዓለማችን #ሰላም #ይመርቅልን ።   ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 07/10/2025 በቃ ጦርነት። በቃ መገዳደል። ጊዜ ራዲዮሎጂ ነ ው

እግዚአብሄር ደስ አለው። ሐሤትም አደረገ። ተስፋን አፋፋ። አዲስ #የሰላም #ግሎባል #ካሪክለም ተነደፈ!

ምስል
  እግዚአብሄር ደስ አለው። ሐሤትም አደረገ። ተስፋን አፋፋ። አዲስ #የሰላም #ግሎባል #ካሪክለም ተነደፈ!   "አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁኝ።" "የሰው ልጅ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።" (ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱)       #ቀን ሲመረቅ ……… አዲስ #ቅን ምዕራፍ -- ይታወጃል! አዲስ ብሩህ #ዘመን --- ያጫል! አዲስ #ቀና ጎዳና ---ይቀይሳል! አዲስ የህይወት በር ከፋች #ድንቅነትን ያጎናጽፋል። ተመስገን። አሜን ተመስገን።   የተከበሩ ፕሬዚዳንት ዶናል ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዕፁብ የሆነ ንድፋቸው በግራ ቀኙ ተደራዳሪወች የመጀመሪያው ምዕራፍ ይሁንታን ተቀዳጄ። ተመስገን። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት በሰላም ዙሪያ ሊቀ - ትጉኃን ተግባር ተባረኩ። ተመረቁ! የጋዛ እና የእስራኤል ውጊያ ፍጥጫን መልክ ሊያስዝ የሚችል የመጀመሪያ ምዕራፍ ስምምነት በሁለቱ ተደራዳሪወች ዘንድ ተፈረመ። እግዚአብሄርም #ደስ አለው። እኛም ሐሤት አደረግን። ለሰው ልጅ ሰላም ኦክስጅኑ ነው። ሰላም ትንፋሽ ነው። ሰላም ትርታ ነው። ሰላም ለሰው ልጅ ለተፈጥሮ የመኖራቸው ሚስጢር ነው።    አይደለም አንድ ድርብርብ #ኖቤል ቢሸለሙ የተከበሩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ፕሬዚዳንት ትራንፕ #ይገባቸዋል ! ፕሬዚዳንቱ #ከተደጋጋሚ ሞት የተረፋበት #ሚስጢር #አዲስ #መጸሐፍ ነው ይህ ድንቅ፥ ፍጹም ድንቅ #የምሥራች #ቀን ።    ዕንባ ይቆማል! የሰው ልጅ ደም መፍሰስ ይቆማል! የፍርኃት ዘመን ያከትማል! ልጆች ያለ ሥጋት እየሳቁ ያድጋሉ። መፈናቀል ቀጥ ይላል። ልጆች በሳቅ በቀያቸው ይቧርቃሉ። ራህብ፤ ቸነፈር፤ መሰደድ፤ አገር አልባነት፤ መከላተም ይቀንሳል። አትኩሮት ወደ ቀደ...

"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። "#ግጭት" ወይንስ "#ጦርነት"

ምስል
  #ችግር ዕውቅና ካላገኜ #መፍትሄው ሩቅ #በጣም እሩቅ፤ #እጅግም እሩቅ ነው - ለእርቅም ይገነግናል።    "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።     " #ግጭት " ወይንስ " #ጦርነት "    ኢትዮጵያ ከዝምተኛው ማህበረሰብ #የህግ ባለሙያወችን፤ የሰብዓዊ መብት ዕውነተኛ #ቅን ሞጋቾችን፤ #በፖለቲካ ሳይንስ የተማሩ የተመራመሩትን ሊቃናትን አክላ፤ ተገለው ያሉትን #ሊሂቃንንም ጨምራ፤ አሁን በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ከብልጽግና አገዛዝ አሻፈረኝ ካሉት ከኦላም ጋር ይሁን ከፋኖ ጋር፤ በቤንሻንጉል ጉምዝ፤ በጋንቤላም ካሉ ትናንሽ ቲሞችም ጋር ቢሆን የሚደረገውን የአፈሙዝ ግጥሚያ ይህን በኽረ ጉዳይ አጥንተው በአጭር ጊዜ #ሊዳኙት የሚገባ ይመስለኛል። ጦርነት ነው ወይንስ ግጭት? መፍትሄው በልኩ ሊታሰብለት ሲገባ። እራሴን ከበረደኝ ኮፍያ ብቻ አደርጋለሁኝ። ሙሉ ሰውነቴን ከበረደኝ ግን ጃኬቱ፤ ጓንቱ፤ ድርብ ካሊሲው፤ ሻሉ፤ ካፖርቱ፤ ሱሪ እና ሹራቡ ሁሉም ይጠራሉ። ችግርን በልኩ ማድመጥ ይገባል። መፍትሄውን በልኩ ለማደራጀት። በኽረ ጉዳዩ #ቢገፋ ፦ #ቢገለል ፤ #ቢቃለል ፤ ዕውቅና ቢነሳ፤ #ቢሽሟጠጥ ፤ ቢጣጣል፤ የሚያስከፋ ሥያሜ ቢሰጠውም " #ሸኔ #ጃዊሳው " ችግሩ ቀጥሏል። መቀጠል ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ #ቀንድ ዓይነተኛ ችግር ለመሆን እያኮበኮበ ነው። ሴም እና ኩሻዊነትም እያጠቀሱ ነው። እህ። ይህም ብቻ አይደለም የቀንዱ አፍሪካዊ ፖለቲካ ከጦፈ ነጩን ቤተ - መንግሥት ሰተት አድርጎ የማስገባት ጥሪኝ ያለው የፖለቲካ ቃና ነው። ከዚህ ላይ ህወሃት የቀደመው ኢትዮጵያን የመረከብ የመሻት ናፍቆት በነጩ ቤተ- መንግስት አይሆኑ ሆኋል። ለዚህ ነው በአዲስ ቅርጽ አይድኔው ህወሃት እያነኳኮረ ያለው...