ለስሜን ጎንደር በአለፋ ጣቁሳ #ፋኖ አገልግሎት መስጫወችን ማቃጠል የድል እርከን ከሆነ እንኳን ደስ አላችሁ¡¡¡¡
ለስሜን ጎንደር በአለፋ ጣቁሳ #ፋኖ አገልግሎት መስጫወችን ማቃጠል የድል እርከን ከሆነ እንኳን ደስ አላችሁ¡¡¡¡ የአለፋ ጥቁሳን መንደድ ከአቶ ዳንኤል በቀለ ፔጅ ላይ ነው ያገኜሁት። ህወሃት የተነሳበት ዓላማ እየተሳካለት ነው። "አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።" አሜን። #ምዕራፍ ፲፰። #በምልሰት የጣና ወርቅ ትዝታን። ጭልጋ አውራጃ ጭልጋ ወረዳ፤ ማጠቢያ ወረዳ፤ ቋራ ወረዳ ውስጥ አንዱ አለፋ ጣቁሳ ነበር። አለፋ ጣቁሳ የቅቤ፤ የማር፤ የእህል ዘር ብቻ ሳይሆን ማንኛውም #የቅመማቅመም ዓይነት የሚመረትበት፤ በእንሰሳት ተዋፆ ከአሳ ጀምሮ ዕምቅ ሃብት ያለው፤ በዕት ነው። እራሱ ደልጊ ከመድረሳችሁ በፊት የመኪና መስኮቱን ስትከፍቱት የደንቢያን ለጥ ያለ የሽንብራ አዝመራ ሲዘናጠፍ እያያችሁ የደልጊ የቅመማቅመም ህብር ጠረን አቀባበል ያደርግላችቿል። ሆቴል ይዛችሁ ምሳ ስታዙ #ዓሳ በዓይነት ይቀርባል። እኔ ጎርጎራ እና ደልጊ የበላሁት የዓሳ ጥብስ ጣዕሙ አብሮኝ ይኖራል። ጎንደር ከተማ ክርምትን ተከትሎ የዓሳ ገብያ የደራ ነው። የዓሳ መሰናዶም በየቤታችን ልዩ ነው። ያው በልጅነት እሾ ቢያስቸግረንም። የሆነ ሆኖ ወዛችሁን እርፍ አድርጋችሁ ሥራ እስክትጀምሩ ድረስ #ሰላምለኪ ጣና ለማለት ወደ ወደቡ ጎራ ትላላችሁ። ጣና እራሱ #አገር ነው። ዲካ የለውም። በሁሉም አቅጣጫ ብትዘዋወሩ ጣናን የዓይኔ ጥግ እስከዚህ ድረስ አይቶታል ብላችሁ መወሰን አትችሉም። የእቴጌ ጎንደር ዝክረ - ማንነትም ከዚህ መሰል እዮራዊ #ትንግርት የተቀዳ ነው። እንዴት ዋልክ ጣናሻ/ እንዴት ሰነበትክ ጣናወርቅ? እንደምን ባጀህ የእኔ ጣና ብላችሁ የቤተ - ዘመዱን፤ የዘመዳ ዘመዱን ወግ ካደረሳችሁ በኋላ ወደ...