ህሊና።
ህሊና። ከሥርጉተ - ሥላሴ ( Sergute © Sselassie ) 10.01.2018 (ከጭምቷ - ሲዊዘርላንድ።) „ትሁት ልብ የሥጋ ሕይወት ነው፤ ቅንዓት ግን አጥንትን ያነቅዛል።“ (መጸሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፲፬ ቁጥር ፴) · እ ንደ መነሻ https://www.youtube.com/watch?v=lzMC2C1x0Qw ESAT Efeta 5 Jan 2107 (2018 ) http://www.satenaw.com/amharic/archives/44372 „ ይድረስ ለአቢይ አህመድ ( ዶ / ር ( ለኦህዴድ ፅህፈት ቤት ሀላፊ በኤርሚያስ ለገሰ) ቆንጽሎ ማዬት የጭንቀት በሽታ ነው። ዛሬ ትንሽ ከፖለቲካ ተንታኙ ጋዜጠኛ ኤርምያስ ስጋትን ማነሳሳት እንዲህ አሰኘኝ። ይሳሳ - ይባዘት - ይቀንደብ፤ የማከብርህ ወንድሜ ጋዜጠኛ ኤርምያስ ለገሰ እንዴት ሰነበትክ? ምነው እንዲህ ብትክትክ አደረገህ? አንድ ጊዜ ከእነከሌ ጋር ጎን ለጎን መቀመጥ የለባቸውም ትላልህ፤ ከተጨባጭ ውጪ የሆነ ነገር። አሁን ደግሞ ኦፌኮን ምህረት ይጠይቁ ትላለህ? ግራው ገባህ። እንደዚህ ከሆነ አትደራጁም ብላችሁ ጦር የሰበቃችሁባቸውን የአማራ ድርጅቶችን ይቅርታ ጠይቁ - እናንተም። የአማራን ተጋድሎ „የነፃነት ሃይል እያላችሁ“ ሥነ - ልቦናችን ባልተወለደ አንጀታችሁ ያረሳችሁትን ሁሉ ቁስሉ እንዲሽር ይቅርታ ጠይቁ። ከገ...