የኤርትራን ልኡካን ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ተቀበሏቸው።
የቤተሰባዊው የመንትዮሹ ዕሴት በምን እና በምን ቀልመው ባጁ? ልግመኛው ጥላቻ ዛሬ ተቀጣ! ከሥርጉተ © ሥላሴ። 26.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ) „ምህረትና እውነት ከ አንተ አይራቁ፣ በአንገትህ እሰራቸው፤ በልብህ ጽላት እሰራቸው።“ (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፫) የሰው ልጅ ላካ ከማያውቀውም ስሜት ጋር ነው አብሮ የሚኖረው ማለት ነውን? ከእኔ ቁጥጥር ውጭ ከሆነ ስሜት ጋር መኖሬን ዛሬ አረጋገጥኩኝ። በፍጹም ሁኔታ ፈጽሞም ያልጠበቅኩት ነገር ነው አሁን የገጠመኝ። የኔወቹ ግን ልታምኑኝ ትፈቅዳለችሁን? እባካችሁ እመኑኝ። ዛሬ የኤርትራ የልዑክ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ በፍጹም ሁኔታ ጭራሽም ያልጠበቅኩት ነገር ነው የገጠመኝ። እያዬሁኝ ከእኔ ቁጥጥር ውጬ በሆነ ሁኔታ የገፄ መስኮቶች ለካናስ ዝናቡን ከፈቃዴ ውጪ ለቀውታል። ምን ነካኝ ብዬ ራሴን እስክታዘብ ድረስ። ለካንስ እንዲህ እኛ ሳናውቀው ውስጣችን የተጎዳበት መለዬትን ያለመፍቀድ ሰቆቃ ነበረብን። ለካንስ ይህን ያህል ውስጤ አዝኗል። ዘጋቢው 18 ዓመት ይላል ዘመን አይለካውም፤ በመሃል የነበረውን የታሪክ ስንጥቅጥ። ግን ለምን ሆነ? እኮ ስለምን? ለዚህ መራር የሀዘን ስሜት ፈቀደንለት? ክፉነት ግን እንዴት ክፉ ነው። ክፉነት እሱ ከፍቶበት እኛንም አስከፋን። እኛንም ክፉነቱን ለክፉነት አዋረሰን። ወንድሞቻችን የገበርንበት የመከራ ዘመን ይህን መሰል የውስጥ እረመጥ ተሸክመን እንድንኖር ተገደድንበት። መለዬት ለካንስ ሰው ከሰው ብቻ ሳይሆን የአገር ሆኖ ሲሆን ደግሞ እንዲህ ግዙፍ ነው። እንደ ገና ደግሞ በምልሰት መለዬት በቃኝ ብሎ ወደ እኛ...