የቧልት ብልት!
የቧልት ብልት! „እውቀትን ለማን ያስተምረዋል? ወይስ ወሬ ማስተዋልን ለማን ይሰጣል? ወተትን ለተው ወይስ ጡት ለጣሉ ነውን?“ ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፳፰ ቁጥር ፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ 17.08.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። መፈራረጃ እንደ በር፤ ይግርሙኛል የሰሞኗቱ ጉዳዮቹ ዶር ገዱ አንዳርጋቸው ለውጡ እንዳይቅለበስ ምንትሶ ቅብጥርሶ ይሉናል … የተፎካካሪ ፓርቲዎች ደግሞ ለውጡን ስለማስቀጠል ይነግሩናል፤ የለውጡ መሪ መንፈሱ የት አለና ለውጡ የሚቀጥለውስ የሚቀድመውስ? ቁልጭ ያለው ዕውነት እኮ አንጃው እና ወያኔ ሃርነት ትግራይ ቀልብሶ በምስል እየተፍነሸነሸ ነው። ለወያኔ ቧልት ደግሞ እጅ ነሺዎች ሆናናል። ደጅ ጠኚዎችም። አሁን እውነት ጠፍቷቸው ነው ዶር ገዱ አንዳርጋቸው ለውጡ እንዳይቀለበስ ምንትሱ ቅብጥሮሶ የሚለኑ? እንዴት ነው ማተብ የሚባል፤ ኪዳን የሚባል የለምን? ቅደስት ተዋህዶም ቤተክርስትያኔ ስቃይ ውስጥ ናት እና የህግ ጥበቃ አልተደረገለኝም እያለች ነው። ያው ያተራመሰው ወያኔው ስለሆነ ለወያኔ ሃርነት ትግራይ አቤቱታው ወደ መቀሌ ቢላክ መልካም ነው። ወይ ደግሞ ለእነ ሳጅን በርከት ስምዖን ጁንታዎች፤ እዛው ቤተ መንግሥት አዲስ ሴራ ላይ ለተጠመዱት ለእነሱ ቢሆን ይሻላል። አባ ቅንዬማ ካቴና ውስጥ ናቸው፤ ወዱቼ አዱኛዎቼ ጥቂት በምልስት እና በቅኝት አብረን እንሁን እላለሁኝ ... ቧልቱን በብልት በብልቱ ለማየት እነዚህ ሊንኮች በሚመለከት የቤት ሥራ ልስጣችሁ እና እዩዋቸው - ጥያቄ ግን በትሁት መንፈስ ነው። ነፃነት የተቀማው አንበሳ...