ልጥፎች

መጥኒ ለእናታዊነት።

ምስል
  መጥኒ ለእናታዊነት።   • ዘገባው የBBC ነው።   "በትግራይ ከሥራ ቦታ፣ ከመንገድ እና ከመኖሪያ ቤት እየተካሄደው ያለው አፈሳ የፈጠረው ስጋት"   https://www.bbc.com/amharic/articles/c3vywvgnv2qo «የትግራይ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ በትግራይ "የተመለመሉ" ወጣቶችን ለሠራዊት እያሰለጠነ መሆኑን ለቢቢሲ ትግርኛ ገልጾ የምልመላው ሂደት ግን "በክልሉ መንግሥት እንደሚፈፀም" ተናግሯል።   ቢቢሲ ያነጋገራቸው በክልሉ የተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ወጣቶች ከሥራ ቦታቸው፣ ከመዝናኛ ስፍራ እንዲሁም ከሕዝብ ትራንስፖርት ላይ በግዳጅ ተወስደው ወደ ተለያዩ ካምፖች መላካቸውን ተናግረዋል።   ቅድሚያ ለሰብዓዊ መብቶች ኢትዮጵያ በበኩሉ የትግራይ ፀጥታ ኃይሎች በክልሉ መጠነ ሠፊ አፈሳ እና የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ እያካሄደ መሆናቸውን በመጥቀስ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል።   የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ድርጊቶቹ ይፈጸምባቸዋል በሚል ከዘረዘራቸው አካባቢዎች መካከል፣ ሰሜን ምሥራቅ ዞን፣ ማዕከላዊ ዞን እና ምሥራቃዊ ዞን ይገኙበታል።   ለሁለት ዓመታት የተካሄደውን ጦርነት ባስቆመው የፕሪቶሪያ ስምምነት መሠረት የተቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር በማፍረስ ከጦርነቱ በፊት የነበረው የክልሉ ምክር ቤት ሥልጣን ከያዘ በኋላ በህወሓት መሪዎች እና በፌደራል መንግሥቱ መካከል ውጥረት ተፈጥሯል።   ተመልሶ ሥራ የጀመረው ፈርሶ የነበረው የትግራይ ክልል ምክር ቤት ሕጋዊ የፓርቲ ዕውቅናው የተሰረዘበትን የህወሓት ሊቀመንበር ደብረፂዮን ገብረ ሚካኤልን የክልሉ ፕሬዝዳንት አድርጎ የሾመ ሲሆን፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ያሉበት ሁኔታ አስካሁን በይፋ አይታወቅም።   በዚህም የተነሳ በክልሉ ሌላ ...

፲ #ኤርትራ፤ ፳ ሰሜን ሱዳን፤ ፴ ግብጽ አያስደነግጡኝም - እኔኑ። #ለምን? #ይልቁንስ እኮ ……… #ምን???

ምስል
  ፲ #ኤርትራ ፤ ፳ ሰሜን ሱዳን፤ ፴ ግብጽ አያስደነግጡኝም - እኔኑ። #ለምን ? #ይልቁንስ እኮ ……… #ምን ???   "አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።"     #ምዕራፍ ፲፱።   ፲ #ኤርትራ ፤ ፳ ሰሜን ሱዳን፤ ፴ ግብጽ አያስደነግጡኝም - እኔኑ። ለምን?    ፈላስፊት ኢትዮጵያ ------አትለካም። ሳይንቲስቷ ኢትዮጵያ -------አትሰፈርም። ዩንቨርሷ ኢትዮጵያ --------አትመዘንም። ህጊት ኢትዮጵያ ---------አትገመትም። ቤተ - ይሉንታዊቷ ኢትዮጵያ ------------- #አትከነዳም ።   ሱዳንም በቀደመው ጊዜ ወራ በመተማ በኩል፤ ግብጽ ዕድሜ ልኳን ታግላ፤ በዞግ አደራጅታ ባህር በር ይሁን ወደብ አሳጥታ፤ የአፍሪካ ቁልፍ ቀንድነቷን ፈትና፤ ኢትዮጵያ ግን አለች የአፍሪካው ህብረት #ዋና ጽህፈት ቤት ሆና፤ የዓለም ፬ኛ #የዲፕሎማሲ ዓይንም ሆና ቀጥላለች።   ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያኒዝም እንደ አሻው በሆነ አካል የሚኮሰምን፤ #ቃ የሚል፤ #ዳ የሚፈትነው፤ ስብራት የሚጎበኜው ማንነት አይደለም። ብዙ ያለው፤ ያለውን ልቅና በልዕልና መስጥሮ የተቀመጠ አንቱ ማንነት ነው ኢትዮጵያዊነት። የሰይጣን ጆሮ ይደፈንና " #በደራሽ ሱናሜ፤ በምኞት ፈረስ ፍርስርሱ ይሁን ብትንትኑ የሚወጣ" ማንነት አይደለም ተፈሪው ኢትዮጵያዊነት።   በብልጽግና ዘመን እራሱ እኮ ብዙ ፈተናን አስተናግዷል። ተቋማቱ ሁሉ ፈተና ላይ ነው የባጁት። የኢትዮጵያኒዝም አማንያን ያላዩት የአሳር፤ የፍዳ ዓይነት የለም። ሎጎወች ኢትዮጵያን ከሚገልጹ ንጥረ ነገሮች ሁሉ በእጅጉ ከድንቁ የኢትዮጵያዊነት ማንነት የራቁ ናቸው። አንድ ቀን ለራሳቸው ለጠቅላይ አብይ አህመድ ሰባስቤ አቀርብላቸዋለሁኝ። በዚህው በቤተ ሥርጉትሻ።...

#ሁለት ወዶ አይሆንም።

  #ሁለት ወዶ አይሆንም።    "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።"   ምዕራፍ ፲፰።   #ብልፄው ሁለት ወዶ አይሆንም። ሥልጣኔ #ይጽና በደልም #ይቀጥል አያዋጣም።   የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች #ካቴና ሊነካቸው አይገባም። ምክንያት ከፖለቲካ #ውክልና ፤ ከመኖር አንባ ውስጥ #ተገለዋል ።   ምን #አደረጉ ? መገደላቸውን፤ ለቅሷቸውን፤ መገፋታቸውን፤ መቃለላቸውን ሁሉ ቻል አድርገው በተቀመጡ ለምን #ካቴና ይታዘዝባቸዋል?   አንድ ጊዜ አይደለም፤ ሁለት ጊዜ አይደለም በተደጋጋሚ ብልፄው ተኝቶ ሊያስበው የሚገባው ቁምነገር በቅድስት ኦርቶዶክስ ላይ በግልጽም በስውርም የከፈተው ዘመቻ ሊቆም ይገባል።   ቅድስቷ ይቅርታ ልትጠየቅ ይገባል። በይፋ። ላዘኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች ብቻ ሳይሆን፤ ለወዳጆቿም ጭምር አጽናኝ ብሄራዊ መልዕክት በእጅጉ ያስፈልጋል። #ይቅርታ መጠየቅ #እርቅን ፤ መተማመንን ቢያጸድቅ እንጂ ማንንም አይጎዳም። የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የጸጥታ ህማማት ሊያመጣ የሚችለው እርግማን ሊታሰብ ይገባል።   ለትውልድም ለአገርም #ስለማይጠቅም ። ውዶች ክብሮች ቤተ ሥርጉትሻ እንዴት አላችሁልኝ። .   ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን። ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።   ኑሩልኝ። አሜን። ሥርጉተ©ሥላሴ። Sergute©Selassie. 15/06/026.   #ፍቅር ሲያልቅ #ትዕግሥት #ይሰደዳል ።

ከዚህ በኋላስ? "በዋግ ኽምራ ዞን ታጣቂዎች ሁለት ወረዳዎችን በመቆጣጠራቸው በርካታ ነዋሪዎች መፈናቀላቸው ተነገረ" BBC.".

  "በዋግ ኽምራ ዞን ታጣቂዎች ሁለት ወረዳዎችን በመቆጣጠራቸው በርካታ ነዋሪዎች መፈናቀላቸው ተነገረ" BBC.   https://www.bbc.com/amharic/articles/cjeg35z91ywo 10 ሰኔ 2026 የንባብ ጊዜ: 5 ደቂቃ   "በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን 'የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ' (አዴን) ታጣቂዎች አበርገሌ እና ፃግብጂ ወረዳዎችን "ሙሉ ለሙሉ" መቆጣጠራቸውን እና ማኅበረሰቡ በስጋት ሸሽቶ መፈናቀሉን የአካባቢው አስተዳደር እና ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ።   ከሁለት ዓመት በፊት ከመንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት ፈርመው የነበሩት የአገው ታጣቂዎች ካለፈው ሚያዝያ ወር ጀምረው ሁለት ወረዳዎችን እንደተቆጣጠሩ አምስት የአካባቢው ነዋሪዎች እና የዞኑ ፀጥታ መምሪያ ተናግረዋል።   የአዴን ኃላፊዎች ወረዳዎቹን እንደተቆጣጠሩ ለቢበሲ አረጋግጠው፤ ነዋሪዎች ግን አልተፈናቀሉም በማለት አስተባብለዋል። በአበርገሌ ወረዳ ሚያዚያ 12/2018 ዓ.ም. በአካባቢው ሚሊሻዎች እና በታጣቂዎች መካከል "በከባድ መሣሪያ" የታገዘ ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ የአዴን ኃይሎች በከፊል ተቆጣጥረውት የነበረውን ወረዳ ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠራቸው ተነግሯል።   ቀኑን ሙሉ ውሏል በተባለው ውጊያ የአዴን ኃይሎች ከ"ህውሓት ታጣቂዎች" ጋር "ተቀናጅተው" እንደተሳተፉ ነዋሪዎች እና የዞኑ አስተዳደር ለቢቢሲ አመልክተዋል።   የአዴን የሚዲያ እና ኮምዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ካሴ ከህውሓት ኃይሎች ጋር ተጣምረው መዋጋታቸውን አስተባብለው፤ "አመራሮቻችንን አፍነው ለመውሰድ ሲሞክሩ" ግጭቱ ተቀስቅሷል በማለት "ተገፍተን ነው [ወደ ግጭት] የገባነው" ...

"የአሜሪካዋ ግዛት ምክር ቤት ለአድዋ ድል መታሰቢያ ቀን ሰየመ BBC."

ምስል
  "የአሜሪካዋ ግዛት ምክር ቤት ለአድዋ ድል መታሰቢያ ቀን ሰየመ BBC." https://www.bbc.com/amharic/articles/cn94gp15zx7o   ከ 5 ሰአት በፊት የንባብ ጊዜ: 3 ደቂቃ   "በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት 2' በግዛቱ የአድዋ ድል መታሰቢያ ቀን እንዲሆን የቀረበን የውሳኔ ሐሳብ በከፍተኛ ድምጽ አፀደቀ።   ይህ 'ኤችአር 441' የተሰኘው የውሳኔ ሐሳብ የፀደቀው ባለፈው ሳምንት በግዛቲቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተደረገ የድምጽ አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት ነው።   በአሜሪካ የግዛቶች ምክር ቤት አሠራር መሠረት፣ ይህ ውሳኔ በግዛቲቱ የሕግ መዝገብ ላይ የአድዋ ድል በይፋ ዕውቅና ያገኘበት ታሪካዊ ሰነድ ሆኖ በቋሚነት ይቀመጣል።   ይህ የውሳኔ ሐሳብ ረቂቅ፣ የአውሮፓውያኑ 'ማርች 2 ቀን 2026' የ130ኛ 'የአድዋ ድል ቀን' ሆኖ በፔንሲልቬኒያ ግዛት ዕውቅና እንዲሰጠው የሚደነግግ ነው።   ውሳኔው በሪፐብሊካን እና በዲሞክራቲክ ፓርቲ እንደራሴዎች በተሰጠ 195 ከፍተኛ የድጋፍ ድምጽ እና በ6 ተቃውሞ ብቻ ነው የፀደቀው።   ረቂቁ የቀረበው ከወራት በፊት ቢሆንም የምክር ቤቱን የውስጥ አሠራሮችን አልፎ፣ ውይይቶች ተደርገውበት ከቆየ በኋላ የውሳኔ ድምጽ የተሰጠበት ግን ባለፈው ሳምንት ነው።   ''ኤችአር 441'' ረቂቅ የውሳኔ ሐሳቡን ለፔንሴልቬኒያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረቡት የሰሜን ፊላደልፊያ ሜንገመሪ ካውንቲ፣ የሕዝብ ተወካይ የሆኑት ሴናተር ቤንጃሚን ሳንቼዝ ናቸው።   ቢቢሲ የፀደቀውን የውሳኔ ሐሳብ አስመልክቶ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጡት ሴናተሩን በኢሜይል ጥያቄ አቅርቦላቸው ...

«ስዊትዘርላንድ የሕዝብ ቁጥሯ ከ10 ሚሊዮን እንዳይበልጥ በቀረበው ዕቅድ ላይ ድምጽ ልትሰጥ ነው» BBC.

  «ስዊትዘርላንድ የሕዝብ ቁጥሯ ከ 10 ሚሊዮን እንዳይበልጥ በቀረበው ዕቅድ ላይ ድምጽ ልትሰጥ ነው» BBC. https://www.bbc.com/amharic/articles/c6216ggwxryo   ከ 5 ሰአት በፊት የንባብ ጊዜ : 3 ደቂቃ "አንድ አገር የሕዝብ ቁጥሩ እንዳያድግ ቁጥሮችን ማስቀመጥ እና መወሰን ይቻላል ?" "ይህንን ለመመለስ ስዊትዘርላንድ የአገሪቱን ሕዝብ ቁጥር ከ 10 ሚሊዮን እንዳይበለጥ የቀረበው ዕቅድ ላይ እሁድ ድምጽ ትሰጣለች። ዕቅዱን ቀኝ ዘመሙ የስዊስ ሕዝብ ፓርቲ ( ኤስቪፒ ) ደግፎታል። ፓርቲው ዕቅዱ በመኖሪያ ቤት፣ በሕዝብ አገልግሎቶች እንዲሁም በአካባቢ ላይ ያለውን ጫና ይቀንሳል " የዘላቂነት " ጥያቄ ነው ሲል ደግፎታል። ወደ ስዊትዘርላንድ የሚመጡ ስደተኞችን ቁጥር የመቀነስ ዓላማ ያለው ይህ የፓርቲው ሃሳብ ሕዝቡን እና አንዳንድ ተቋማትን ለሁለት ጎራ ከፍሏቸዋል። የስዊስ መንግሥት እንዲሁም ሁሉም ትልልቅ ፓርቲዎች፣ የንግድ ድርጅት ኃላፊዎች እና የንግድ ማኅበራት በበኩላቸው " ቀውስን የሚጋብዝ " ዕቅድ ነው ሲሉ ተቃውመውታል። ሆቴሎች እና ሆስፒታሎችን የመሳሰሉ አገልግሎት መስጫ ተቋማት አስፈላጊ የሆነ የሰው ኃይል እጥረት እንዲገጥማቸው ያደርጋል ሲሉ ተከራክረዋል። አክለውም አገሪቱ ከአውሮፓ ኅበረት ጋር ያላትን ግንኙነት አደጋ ላይ እንደሚጥለው እና ከኅብረቱ መውጣት ደግሞ በዚህ አደጋ በሞላበት ዓለም ስዊዘርላንድን እንድትገለል እንደሚያደርግ አስረ...