እ። ምን ልል ነበር አያ? ኧረ አወን ልበለው። "የታስራችሁ #የተሰውታችሁ እንይ" ምኞት። "በሞኝ ክንድ ዘንዶ ይለካበታል።"
እ። ምን ልል ነበር አያ? ኧረ አወን ልበለው። "የታስራችሁ #የተሰውታችሁ እንይ" ምኞት። "በሞኝ ክንድ ዘንዶ ይለካበታል።"
"እግዚአብሄር እዮብን ልቡ ከኃጢያት፤
እንደነፃች ባየው ጊዜ፤ በብዙ ክብር
ተቀበለው።" (መቃብያን ም ፰ ቁ ፪)
ምዕራፍ ፲፱።
ጤና ይስጥልኝ ክብርት ኢትዮጵያ እናት አገሬ፤
ጤና ይስጥልኝ እምዬ ሲዊዝሻ ርህርህተ - አገር፤
ጤና ይስጥልኝ ኮሽ አይሏ ደጓ፤ እየኖርኩብሽ እማልጠግብሽ ቢንተርቱር ከተማ (Winti)
ጤና ይስጥልኝ አዱኛወቼ ቤተ - ሥርጉትሻ እንዴት አድራችሁ? እንደምንስ አረፈዳችሁልኝ?
"በአገራዊ" የምክክር ኮሜሽን ቅሬታ ያላቸው ተቋማት፤ የተከፋ ተሳታፊወች "ጉባኤውን ረግጣችሁ
ውጡ፤ ምን ትጠብቃላችሁ፤ ሞትም እስራትም ቢመጣ ተጋፈጡት፤ የሚል ጨካኝ ሃሳብ አዳመጥኩኝ።
"ያልተነካ ግልግል ያውቃል" እንዳልል ሃሳብ አራማጁ በዘመነ - ህወሃት፤ በዘመነ - ብልፄው
ታስሮ የተንገላታ፤ የተሰደደም ነው።
በተለይ የአማራ ተወያዮች "በነውረኛ ቃል ዘለፋ፤ በክፋ ዓይን መገረፍ፤ በተሳትፎ ላይ ዕድል
መነፈግ፤ ግልምጫ፤ ማሳደድ ተካሂዶብናል" ብለው ቅሬታቸውን ለምክክር ኮሚሽኑ አቅርበው
አድማጭ ማጣታቸው ነው "ጥለው ይውጡ ምን ይሠራሉ? ይውጡ እና የሚመጣውን ይጋፈጡ"
የሚል ሃሳብ ተሰጣቸው።
ወጣትነት ትዕግሥትን የሚፈትን ስለሚሆን ይሆናል። ወጥተው የት ይሂዱ እነኝህ ቅሬታ
አቅራቢወች? ሰማዩም ምድሩም እኮ #በብልፄው መንግሥት ሥር ነው። ምንድን ነው ወጥተው
የሚያተርፋት? ማንስ አላቸው???? መቼም ከ፵ ሚሊዮን ህዝብ በላይ ስደት ሊያስብ ይቻል ይሆን
ሎጅኩ? ልሰደድ ቢልስ ይችላልን???
የአማራ ተሳታፊወች ጉባኤውን ረግጠው ቢወጡ አትራፊ አይደለም። ቅራኔውን ያፍመዋል፤ ተጠቂነታቸውንም
የበለጠ በእጥፍ #ያፋጥነዋል። በተለይ የተማሩ እና በፆታቸው፤ ተባዕት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ከሆኑ። ለእነሱ
ቅንጣት ርህራሄ የለም። ለ፰ ዓመታት የታዘብኩት ይህን ነው።
ሰላማዊ ትግል ጠንቃቃ መንፈስ ይጠይቃል። ሰላማዊ ትግል ወጀብን የመቋቋም አቅም ብቻ ሳይሆን
ክህሎትን ይሻል። ክህሎት የዳበረ የሰከነ የተግባር ልምድን ይጠይቃል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ የሦስቱ ወጣት ሰማዕታት ውሳኔ እኮ #እኔን ያዬህ ተቀጣ እርምጃ ነው። አዲስ አበባ
እንዳይፈጽሙት ዓለም በንቃት እና በትጋት የሚከታተለው ጉባኤ ነው። ጉባኤው የሚካሄድበት በኢትዮጵያ
#ዋና መዲና፤ በአፍሪካ ትንፋሽ፤ በዓለም ዲፕሎማሲ መቀመጫ ነው። ለዓለም ሚዲያ የመጋለጥ ዕድሉን
ለማሸሽ ይሆናል ይህ የተፈጸመው።
እርምጃው ሙግት ላይ ላሉ ባለ አቅሞች #ስማ ነው።ሌላ እስር ስለምንስ ይናፈቃል? እስር ላይ ያሉ ወገኖቻችን
ማን አስታውሷቸው ያውቃል? ለዓላማቸው ሰማዕትነትን የተቀበሉ እነ ወጣት ናሆሰናይ፤ ወጣት አባኔዘር
የሚያስታውሳቸው ዛሬ አለን? ቤተሰቦቻቸውን የሚያቋጥር አለን? "በሞኝ ክንድ ዘንዶ ይለካበታል።"
ስለ ታሰሩት ወገኖቻችን ሲፃፍ ሼር የሚያደርግ እንኳን የለም። ለዓላማቸው ሰማዕት የሆኑትን ቤተሰቦች እንዲህ
ዓውደ- ዓመት ሲመጣ ማን ጠይቋቸው ያውቃል? ማገዶነት ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ተጣይ ነው። በየወቅቱ ገኖ
ይወጣል። ከዛ እንደ ሳሙና አረፋ ተኩረፍርፎ #ረብ ይላል። ይረሳልም። ጠበቃ ሳሙኤል ዓወቀ ታስቦ ያውቃልን?
"ታስራችሁ እንያችሁ፤ ተሰውታችሁ" እንያችሁ ብሎ ነገረ "የራስ ወንድም፤ የራስ እህት፤ የራስ እናት የራስ
አባት፤ የራስ ልጅ፤ የራስ ቤተ- ዘመድ ቢኮን" ቃሉ እንዲህ #ይደፈራልን? ለራስ ጉዳይ ልዩ ጥበቃ፤ ልዩ ከለላ
ይፈቀዳል፤ የማህጸን ቄራነት ከሌላው ይጠበቃል።
እራስን አድኖ ስደት ላይ ተሁኖ "ተማግዳችሁ፤ #ጭሳችሁ፤ ነዳችሁ የእንያችሁ" ምኞት አትራፊ የፖለቲካ ስልት ፈጽሞ
አይደለም። በግራ በቀኝ ወዮ! ብትሳተፋ እየተባሉ መሳተፋቸው በራሱ እኮ ሰማዕትነት ነው።
በምርጫው ጊዜ ይሁን፤ በምክክሩ ሁነት "#አትሳተፋ!" እየተባለ ነው፤ ሞታቸውን መርጠው የተሳተፋት
ውጥንቅጥ ችግር ውስጥ ሆኖ፤ ተጨማሪ ችግር ይድረስብኝ ብሎ እራሱን ለማገዶነት ማሰናዳት
የተገባ ነው ብዬ አላምንም።
መስዋዕትነትን - መቀነስ፤ ወጀብን ዝቅ ብሎ ማሳለፍ ይገባል። "የሚያልፍ ዝናብ አይምታህ።" ይላሉ
ባለቅኔ ጎንደሮች። ቅሬታ ማቅረባቸው እኮ ደፋር እርምጃ ነው። ይህ በቂ ነው። ከዚህ በላይ ለመሄድ
ማሰብ ግን እራስን፤ ቤተሰብን ማሰቃዬት ነው። አቅዶ መሰቃዬት ሊፈቀድለት አይገባም።
#ተግ ብሎ በአደብ፤ በጥሞና ማሰብ ይገባል። በነገራችን ላይ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን
ሲመጡ በፆመ ፍልሰቲት ብሄራዊ ምርጫ ታቅዶ ነበር። በጠንካራ ሙግት፤ ተደምጦም ነበር የተዛወረው፤
ያን ሂሳብ ለማወራረድ የአገራዊ ምክክሩ በተናፋቂዋ ሱባኤ ወቅት እየተካሄደ ነው። ፍልሰቲት የቤተሰብ
የሱባኤ ጊዜ ነው ለተዋህዶውያን።
የተሳታፊ ቤተሰቦች በተለይ ልጆች ካላቸው ይህ የሱባኤን ጊዜ ከተሳትፎ ውጪ ያደርጋል። ብልፄው የክልል
ጉባኤወችን ገናን ይዞ ይከውናል። "በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ" እንዲሉ። መሪነት ይህን ይትብኃል አክብሮ
ሊነሳም ይገባ ነበር።
#ሌላው ግን ……
ከእስር ሲፈታ አንድ ሰው፤ #ጫካ እያለ፤ ዱር ቤቴ ሳይል ሌላ አገር የሚሰደድበት እራስን ለማዳን ነው።
እራሱን እንዲህ ያዳነ፤ እራሱን ከሞት ያተረፈ መንፈስ "እስከ መጨረሻው ተጋፍጠህ ሞትህን ይሁን እስራትህን
ተጎንጭ" ኃላፊነት የጎደለው ንግግር ነው። ርህርህና የነጠፈበትም ነው። ዕንባ እንዲበቃ፤ ክፋ ሃሳብ ተሸናፊ
እንዲሆን መትጋት እንጂ ክፋ ሃሳብን ያነገቡ ለበሰጨኞች ተመቻች? #እ!
ተሳታፊወች የተዘለፋበት፤ የተጎንጠጡበት፤ የተገለሉበት፤ መብታቸው ጭፍልቅልቅ ያለበት ህመም
እኮ የ40 - 60/70 ሚሊዮን የሚጠጋው የአማራ ህዝብ እና ወዳጆቹን ሁሉ ያማል። ያቆስላል።
ይቆጫል። ይጎረብጣል። በተለይ "በኢትዮጵያዊነት መሪነት ኢትዮጵያዊነት ሱሴ፤ ስንኖር ኢትዮጵያዊ፤
ስንሞት ኢትዮጵያን" ዕውቅና ሰጥቶ ዓለም ዓቀፍ ተቀባይነት እንዲያገኝ ለተጉ የቅንነት ማህበርተኞች
ጥቃቱ እስከ ውስጣቸው ዘልቆ #ለህመም ሊዳርጋቸው ይችላል። እንጥፍጣፊ ምን ይሉኝ የለለበት፤
ዛሬን የማያሳድር፤ ነገን የሚቀናቀን።
በኢትዮጵያዊነት ተስፋ፤ ተስፋቸው ሲሰወር እነሱም - ታመው፤ የፊት ለፊት ተጠቂወችም ጉባኤ ረግጠው
ወጥተው ቢታሰሩ፤ ቢሰው ንብርብር ኪሳራ ይሆናል። ለአንዱም ቤተሰብ የአንድ ቀን ስንቅ የማቀበል ድፍረት
አልባ ሁነት፤ ጉባኤ "ረግጣችሁ ውጡ እና ታሰሩ፤ ከፍ ሲልም ሙቱ፤ ምን ትሰራላችሁ? #ጨካኝ እይታ ነው።
ሁልጊዜ ተመራጭ የሚሆነው ቁም ነገር፤ ጥበብም በማስተዋል መራመድ ነው። መስዋዕትነትን
የሚቀንሱ ጎዳናወችን መከተል ነው - አትራፊው።
ህወሃት መንበረ ስልጣኑን በአፈሙዝ፤ በግዳጅ፤ አላስረከበም። ብልህነት፤ ማስተዋል፤ እግዚአብሄርን // አላህን
ያስቀደመ ሂደት ዊዝደምን ፈጥሮ ኮሽ ሳይል ሽግግሩ ተከወነ። ተመራጩ መንገድ ይህ ብቻ ነው።
ህወሃት ለዳግም ሥልጣን ሲያኮበኩብም ጉዞውን የገታው የጦር ሜዳ ጀብዱ ብቻ አልነበረም። እእ። ከእልህ
ፃዕዳ - የሆነ፤ ያስተዋለ - መስመር ሁሉንም ጩሆት አስክኖታል።
በዬትኛውም የግፍ ወጀብ ግብታዊነት #አያስፈልግም። ተግ ብሎ ማሰብን፤ በማስተዋል መቀመር ያስፈልጋል።
የአማራ ህዝብ ሁለመናውን አጥቷል። ተጨማሪ መከራ የመሸከም አቅሙ ከእንግዲህ ቢበቃው፤ ለዛ ቢተጋ
መስዋዕትነቱን ሊቀንሱ በሚችሉ በኽረ ጉዳዮች ላይ አትኩሮት ቢኖረው መልካም ነው።
"እስር ቤቱን ሰብረህ እስረኛ አስለቅቅ፤ ያገኜኽውን ድፋ" ና እና "አዲስ አበባን ቀውጠህ እትብትህ የተቀበረበትን
ህዝብ አስነሳ፤ ዛሬ አሁንኑ እንደርስልሃለን" ወዘተ …… የወጣት ናሆሰናይ ዝክረ ታሪክን ማንበብ በቂ ነው።
እያንዳንዱ ተሳታፊ ከእናት ነው የተፈጠረው፤ ትዳር፤ ልጅ፤ ወላጅ ቤተ - ዘመድ ይኖራል። ያ የምክክሩ ተሳታፊ
የቤተሰብ ኃላፊ ሊሆን ይችላል። ያ ሁሉ ቢበተን የማን #ያለህ ሊባል ነው። እራሱን ከወጀብ ያዳነ ማንኛውም ሰብ
የሰው ልጅ ማገዶ ራህብተኛ ሊሆን አይገባም። ፈጽሞ።
የማከብራችሁ የአገሬ ልጆች ዘመን ያቀረበላችሁን ሁነት መርምራችሁ፤ ከፈጣሪያችሁ፤ ከአምላካችሁ ጋር መክራችሁ
የምታደርጉት፤ የምትወስዱት እርምጃ ወሳኙ እናንተው እንጂ እኛ በስደት የምንኖር ወገኖቻችሁ አይደለነም።
መኖራችሁ የሚፈቅድላችሁን አድርጋችሁ፤ መኖራችሁ በሰጣችሁ ወሰን ልክ ሆናችሁ፤ የራሳችሁ ዘበኛ፤ እንደራሴ
በመሆን የራሳችሁ ውሳኔ ጌታ ሁኑ። አድምጡት ግን መርምሩት። እልህ፤ ችኮላ፤ አደብን መሸሽ የሚጎዳው ባለቤቱን
ነው። የሚበልጠው፤ የሚጠቅመውም ከፈጣሪ እና ከቤተሰብ ጋር መምከር ነው። ጠብታ የለት ውኃ፤ እራፊ የለት
ከፈን የማናሟላ እኛ እናንተን ማዘዝ አይገባንም። የኑሯችሁ ካፒቴን እናንተው ናችሁ።
በኢትዮጵያ ህዝብ ጨዋነት እተማመናለሁኝ። ይህን ያህል አማራውያን ከሌሎች ቅን ወገኖቻቸው ጋር ባቀኗት አገር
ኢትዮጵያ ተጋብዘው ግን "እንዳያማም ጥራው፤ እንዳይበላም ግፋው" በይፋ ሲታወጅ፤ ሲገፋ፤ ሲዘለፋ፤ መቆሚያ
መቀመጫ በአንድ ማዕድ ላይ ሲያጡ ዝምታችሁ ለምን? በውነት የደቡብ፤ የሱማሌ፤ የአፋር ወገኖቻችን ዝምታ
አስፈራኝ። በጣም ፈራሁት።
ውህድ ማንነት፤ ህብራዊነት፤ አብሮነት በዚህ ልክ ጫና ሲያስተናግድ ዝምታችሁ ያስፈራል!
#ግፋዓን ሆይ!
ለተጨማሪ መገበር ጥድፊያ አያስፈልግም። መቻላችሁን አስችላችሁ እስከ መጨረሻው ድምዳሜ ዕለት ዛሬ እሮቡ ነው፤
መድረሳችሁ አደብ እና አማራ፤ አቅል እና አማራ፤ የመቻል ጥበብ እና አማራን ፊደል ዘርግታችሁ ለዘመንም፤ ለህዝብም፤
ለትውልድም የፊደል ገበታ ሆናችኋል። መምህር ናችሁ።
"በመከራ በስተጀርባ ሁልጊዜ ክብር አለ" ይላል የእግዚአብሄር ቃል። ለኢትዮጵያ፤ ለኢትዮጵያዊነት ሳታጓድሉ፤ ከዛም
ሳትጎድሎ አክብሮትን ሰንቃችሁ ለተጋፈጣችሁት ከ30 ቀን በላይ ተጋድሎ ክብር አለኝ። #አይዟችሁ!
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
19/08/926.
"አማራነት #ይከበር!"
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ