አጤ ዳዊት በራራን (የዛሬዋን አዲስ አበባ) በ1398 መሠረቱ፡፡ Mindaralew Zewdie

 

አጤ ዳዊት በራራን (የዛሬዋን አዲስ አበባ) በ1398 መሠረቱ፡፡ ከእንጠጣ (አሁን እንጦጦ) እስከኤረር ተራራ (አሁን የረር) የተዘናጠፈችው በራራ የዓለም መካነ ኃይማኖት ፣ መካነ ዲፕሎመሲ ፣ መካነ ንግድ ነበረች፡፡ በወቅቱ የዛሬዎቹ ለንደንና ፓሪስ የእዳሪ መውጫ ፣ የአውሬ መፈንጫ ነበሩ፡፡ በራራ ግን በወቅቱ እጅግ ገናን ከነበሩት ሶስት ( ቬኒሰ ፣ ሮምና በራራ) የዓለማችን የንግድ መናኸሪያዎች አንዷ ነበረች፡፡
በመዲናይቱ ዙሪያ የነበረው የአማራ አርሶአደር በመሸ ቁጥር ከእንጦጦ እስከየረር ሲያማትር በየየቤቱ ደጃፍ ላይ ተሰቅሎ የሚንተገተገውን ፋኖስ አይቶ ፣ የአጤው ከተማ እዚህም እዚያም በራ ፤ ሁሉም ጋ በራራ ፣ እያለ በመደመሙ ፣ የመዲናችን ስም በራራ ሆኖ ዘለቀ፡፡ አህመድ ግራኝ ቴረሪስቱ በኦቶማን ቱርክ አይዞህ ባይነትና የሎጂስቲክስ አቅራቢነት ተዘርፋና ተቃጥላ ባድማ ሆና ስትኖር እምዬ ምኒልክ በ1879 እንደገና መሠረቷት፡፡ ባለቤታቸው እቴጌ ጠሀይቱም ጠሀይ የመሠለ ስም አወጡላት፡፡ እነሆም በራራችን አዲስ አበባ ተሰኘች፡፡

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።