ልጥፎች

"We just released our report in Amharic or testimony of numerous victims .. "Mr. Obang Metho

    #ኦባንግሻ እንዴት ነህ? አንተን የበላ ጅብ #አልጮኽ አለ? #ዘመናችን ይናገራል። #አድማጭ ካገኜ። ፈጣሪ አምላክ #በቃችሁ ይበለን። አሜን። Obang Metho     "We just released our report in Amharic or testimony of numerous victims, survivors and eye-witnesses of Ziway and Shashamane’s attacks that was based on identity factors of ethnicity and religion.   The English version of the report is to be released very soon.‬ Until then please read my short observation. We are deeply saddened by the violence, killing and destruction taking place in Ziway, Shashamane and other parts of the Oromia region of our country in the last month, most of which consisted of targeted attacks based on ethnicity, religion and/or economic status.    Recently, a team from the Solidarity Movement for a New Ethiopia (SMNE) visited the area so as to gain a better understanding of what happened.    After seeing the destruction first hand and personally interviewing numerous victims, survivors and eye-witnesses, w...

መቀመጫ ብሎ ነገር #ለመቀጣጫ? ለኢትዮጵያዊነት #መቅጫም። የእንብርት #እጥፋት። ጀግኖች የእምየዋ ልጆች ይነሱ እና ያድምጡ።

ምስል
  መቀመጫ ብሎ ነገር #ለመቀጣጫ ? ለኢትዮጵያዊነት #መቅጫም ። የእንብርት #እጥፋት ። ጀግኖች የእምየዋ ልጆች ይነሱ እና ያድምጡ።   "ያባት ምርቃት የልጅን ቤት ያጸናል፣ #የናት #ርግማን ግን ሥረ - መሰረት ይነቅላል" (መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲)       #ምዕራፍ ፲፱።   ኢትዮጵያን #ካለ ርዕሰ መዲና? አፍሪካን ካለ ርዕሰ መዲና? ፓን #አፍሪካኒዝምን ካለ ርዕሰ ከተማ?   የዓለም #ጠይማን የነፃነት ቀንዲልን ድል አድዋን ካለ ርዕሰ ከተማ? ያን ጥልቅ ምጥቅ ልቅና ኢትዮጵያዊ #ፍልስፍናን ካለ ርዕሰ መዲና? የኢትዮጵያን ታሪክ፣ ትውፊት፣ ወግ ልማድ፣ ባህል #ዊዝደም ያለ ርዕሰ ከተማ?   እግዚኦስ - አሁን ነው። ምህላስ አሁን - ነው። ማቅ ለብሶ ተንበርክኮ መጸለይ #ለዱዋ መትጋትስ አሁን። ኢትዮጵያ በልጆቿ ባሳደገቻቸው ውስጦቿ #ስትከዳ ። እጅግ አሳዛኝ ገጠመኝ።   በነፃነት አገር፣ በነፃነት የኢትዮጵያን ርዕሰ መዲና ለመወሰን ይህን ያክል #ልመና ? ይህን ያክል #መለማመጥ ? ውዶች ክብሮች ናፍቆቶች በጽሞና እሰቡት #እንብርት አልባ የእግዚአብሄር ፍጥረታትን? የሰውን ልጅ ብቻ ሳይሆን አንዲት ጊደር #እንብርት የሌላት ስትሆን። ጽንስ በምን ይጸነሳል?   የትውልድ መቀጠል በእንብርት #አልቦሽ ? የትውልድ #መቋረጥም በዕንብርት #እጥፋት ። ለዛውም ለአፍታ - ታይተን፣ ለአፍታ - ብን ትን ለምንለው የህይወት #መስመር ?   በኢትዮጵያ ላይ? በእናት ላይ? በአናት ላይ? በውስጥነት ላይ?    ይህን ያህል፣ በዚህን ያህል ጥልቀት #መከፋትን አደራጅቶ፣ መዋለ ዕድሜ መከፋት ስንቅህ ይሁን ብሎ ለ120- 130 ህዝብ ድልድይ መሆን? ...

የኢትዮጵያ መንግሥት፤ "ህገ መንግሥቱ #ጆኖሳይዳል ነው።" "በህገ መንግሥቱ ውስጥ የፖለቲካ ድርጅት #ማኒፌስቶ መንፈስ አለበት"

  የኢትዮጵያ መንግሥት፤ "ህገ መንግሥቱ #ጆኖሳይዳል ነው።" "በህገ መንግሥቱ ውስጥ የፖለቲካ ድርጅት #ማኒፌስቶ መንፈስ አለበት" ይላሉ። ብልፄው ይህን መንገድ ይከተል ይሆን፤ እንደ የኦህውኃት ህገ - መንግሥት። ብታደምጡት ጥሩ ነው። የፕሮፖኃንዳ ውይይት አይደለም። እኔ በዘመኔ ሁሉ ፕሮፖጋንዲስቶችን አዳምጬ አላውቅም። ቢመቸኝም // ባይመቸኝም ሃሳቡ ከፋክት፤ ከህግ ጋር የተያያዙትን ብቻ ነው ጊዜ የምሰጣቸው። ሥርጉትሻ መልካም ሰንበት።     CH ...

አድርሽኝ በጎንደር። ልዕልት ጎንደር ደንብ፤ ድንጋጌ፤ አንቀፃት የሚደመሙባት #ህግ ናት። ጎንደር ለእኔ መነኩሴ ናት። ጎንደር ከተማ የምትመስጥ ገዳምም ናት።

ምስል
  አድርሽኝ በጎንደር። ልዕልት ጎንደር ደንብ፤ ድንጋጌ፤ አንቀፃት የሚደመሙባት #ህግ ናት። ጎንደር ለእኔ መነኩሴ ናት። ጎንደር ከተማ የምትመስጥ ገዳምም ናት።     #ምዕራፍ ፲፱።   ሳይሽ እውላለሁ ከልቤ አስቀምጬ ሳይሽም አድራለሁ እቅፍ አንተርሼ አወሳሳሻለሁ አድርሽኝ ለብሼ አንችን እየሳሳሁ ናፍቆትን ደቁሼ መቼም አይሻለሁ ተፈጥሮን አቅስሼ እሳሳልሽ- አለሁ እቅፍ አንተርሼ እንደ ወጣሁ አይቀር አይቀር እንደ መሼ። #ለህትምት የበቃ።   "የሰው ልብ መንገድ ያዘጋጃል አካሄዱን እግዚአብሄር ያሳካለታል።" (ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱።)   የአብሮነት --- እመቤት የልቅና --- ማህሌት የመቻል ----- ተምሳሌት የጽናት ------ መሠረት የድንጋጌ --- #አናት የሥልጣኔ ------እናት ኦ! ጎንደርዬ ህይወት።   አድርሽኝ በጎንደር ልዩ ቃና፤ ልዩ ማዕዛ፤ ልዩ ጥርኝ፤ ልዩ ናፍቆት፤ ልዩ ቤተሰባዊነት፤ ልዩ የምህላ፤ የሱባኤ የአኃቲነት በማህተም የሚረጋገጥበት ወቅት ነው።   እቴጌ ጎንደር #የተሰጣት ባዕት ናት። እርግጥ ፈተናዋ ብዙ ነው። ፈተናዋ ምንጩም በርከት ያለ ነው።    ዕውነት ቦታውን ለቆ፤ ሌላውንም ተጋፍቶ የማያስለቅቅ በመሆኑ በጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ልዕልት ጎንደር ክብሯ፤ ሞገሷ፤ ደርባባነቷ፤ ውይዝርናዋ ሳይወዛወዝ፤ #ሳይብተከተክ ወይን ብል እንደበላው ጨርቅ #ብትንት ሳይል ቀጥሏል። ወደፊትም ይቀጥላል።    እመቤት ጎንደር #ማንጠግቦሽነቷ ከዕውነት፤ ስለዕውነት የጠራ፤ ስኩን የሆነው የአቨው፤ የእመው ምርቃቷ እቴጌዋን ፈጥሮ አጽድቆ #አስብሎም አስቀጥሏታል። የእቴጌዋ አድማጭነት፤ የልዕልቷ ስክነት የተፈጥሮዋ ድንግልናዋ የፈጠረው ረቂቅ መሰጠት ነው። እቴጌ ጎንደር ...