ትውልድ የማይተካቸው ኮ/ ጎሹ ወልዴ ቃላቸውን አተሙ!
ትውልድ ማይተካቸው ኮ/ ጎሹ ወልዴ ዛሬ ለኢትዮጵያ ህዝብ ዓለም አቀፋዊ ጥሪ አቀሩቡ። ቃላቸውንም በኢትዮጵያዊነት አተሙ! ከሥርጉተ ሥላሴ 20.06.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።) "በመከራዬ ሳሉ ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሄር ጮኽሁ፤ እርሱም ሰማኝ፤" (ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ ፪ ቁጥር ፫) ትወልድ የማይተካቸው ኮ/ ጎሹ ውልዴ ዛሬ በውጬ እና በአገር ውስጥ ለሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያወያነ ሁሉ ለጠ/ ሚር አብይ አህመድ ሙሉ እግዛ እና ለቀናዊ ጉዟቸው ጥንካሬና ብርታት እንዲሆናቿው ለኢትዮጵውያን በሙሉ ታላቅ ዓለም ዓቀፋዊ ታሪካዊ ጥሪ አስተለላፉ። እኒህ ታላቅ ሙሁር እና የፖለቲካ ሊሂቅ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅዓላማ ናቸውም ማለት እችላለሁኝ። ከአገር ከወጡ በኋዋላ መድህን የሚባል የፖለቲካ ድርጅት መሥርተው ካደራጁ በኋዋላ በራሳቸው ፈቃድ ለተተኪ ወጣቶች ያደራጁትን መድህን ፓርቲ ...