የመከራ ዚታ ተሸካሚዋ ስደተኛ እናት።
አላዛሯ ኢትዮጵያ እና ልጆቿ። „ምህረት እና ዕውነት ከአንተ አይራቁ“ ከሥርጉተ© ሥላሴ 09.10.2018 ከጭምቷ ሰዊዊዘርላንድ። · መነ ሻ። https://www.youtube.com/watch?v=_JOWxawk32U Ethiopia:" ከስደት መልስ የምስኪኗ የመኪና ውስጥ ጎጆ " ፡ሁለት ልጆችዋን ይዛ በመኪና ዉስጥ ኑሮዋን ካደረገችዉ ከወ / ሮ ዘሪቱ ጋር የተደረገ ቆይታ ስልክ ቁጥር 011-893-2975 ወይንም 0920 -0196 -34 የመከራ ቁልል የዕለት ኑራቸው ቤተኛ የሆነባቸው ሁለት ህፃናት እናት ናቸው ወ/ሮ ዘሪቱ። ኡጋንዳም ሱዳንም በስደት ቆይተዋል። ስደት ለሁሉ አይደላም ለሁሉም አይከፋም። ዕድል ለቀናቸው ይቀናል ዕድል ፊቱን ለነፈገችው ደግሞ መከራ ይቆልላል። ስደት በልክ ያልተሰፋ ሽብሽቦ ወይንም እጀ ጠባብ ነው። ስደት እና ህይወቱ የፈተና ማሰልጠኛ ተቋም ነው። እርግጥ ነው በሰላ ሁኔታ የሰላ ገጠምኝ ባለቤቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ግን የሰላውም የሚባለው የማትቀበሉትን ዕድል መቀበል ከተቻለ ነው። ያ ካልሆነ ዘላቂ መከራ መሸከም አይቀሬ ነው። ስደት ውስጥ ብዙ አቅጣጫ ያለው ተራራዊ ገጠመኞች ነው ያሉት። ይህን እንደ ተጠቀለለ ትቼ የእነዚህን ምንዱባን ህፃናት ዕጣ ፈንታ እና የነገ አገር ገንቢ ታሪካዊ ድርሻቸው በምን ሁኔታ ሊሰላ እንደሚችል ያለኝን ዕይታ መጥኜ ላንሳ። ለነገሩ በርዕሰ መዲናዋ በአዲስ አባባ ቀደም ባለው ጊዜ በሺሕ የሚቆጠሩ ወገኖች ኑሯቸውን ጎዳና ያደረጉ እንደ ነበሩ ይታዋቃል። አሁን በብዙ እጥፍ አድጓል። ከዚህም አልፎ ከትግራይ በስተቀር ሁሉም ክልል በዬቀኑ ኗሪው ይፈናቀላል በ...