ዓይን ያለው ጆሮ የተስፋ መንገድ ነው።
ዓይን ያለው ጆሮ የተስፋ መንገድ ነው። „መንገዳችሁን እና ሥራችሁን ፈጽማችሁ ብታሳምሩ፣ በሰው እና በጎረቤት መካከል ቅን ፍርድ ብትፈርዱ፣ መጻተኛውን እና ደሃ አደጉን መበለቲቱንም ባትገፉ፣ በዚህም ሥፍራ ንጹህ ደምን ባታፋሱ፤ ክፉም ሊሆንባችሁ፣ እንግዶችን አማልክትን ባትከተሉ፣ ከዘላለም አስከ ዘላለም ለአባቶቻችሁ በሰጠኋዋችሁ ምድር በዚህ ስፍራ አሳድራችኋአለሁ።“ ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፯ ከቁጥር ፭ እስከ ፯ ከሥርጉተ©ሥላሴ 27.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። · መነ ሻ። https://www.ethiopianregistrar.com/mustafa-builder-somali- ethiopian-identities-intertwined-sbs-amharic/ Mustafa the Builder: My Somali & Ethiopian Identities Are Intertwined – SBS Amharic በተለይም “ ለበርካታ ዓመታት በአማራው ላይ ስር የሰደደ አሉታዊ ስብከቶች ስለነበሩ፤ የመጀመሪያ ልዑካን ቡድናችንን በቅርቡ ወደ አማራ ክልል እንዲሄድ እናደርጋለን ” በማለት የአንድነትና ብሔራዊ ማንነት ግንባታ ውጥናቸውን አጋርተውናል። SBS እንዲህ ብሏል „ሩቅ አሳቢ፤ ቅርብ አዳሪ እንደ ማይሆኑ ተስፋችን ነው።“ እኔ ደግሞ የችግሩን መከራ ስለደፈሩ ይህን መድፈራቸው በራሱ የታሪክ ብራና ሊያሰኛቸው ከመቻሉ በላይ አቅም በማመንጨት ረገድም ፏፏቴያዊ...