የገቢዎች ቀን አዲስ ጥረት በኢትዮጵያ።
የገቢዎች ቀን አዲስ ጥረት በኢትዮጵያ። „ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን ? እናንተ ግን እኔን ሰርቃችኋል። እናንተም፦ የሰረቅንህ በምንድር ነው ? ብላችኋል። በአሥራትና በበኵራት ነው። ይህ ሕዝብ ሁሉ፥ እኔን ሰርቃችኋልና በእርግማን ርጉሞች ናችሁ።“ ትንቢተ ሚልክያስ ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ ዛሬ አንድ ዜና አዳምጥኩኝ የገቢዎች ሚ/ር የዘጋጀው ጉባኤ ነው። በጉባኤው ላይ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ተገኝተዋል። ጉባኤውን ያዘጋጀው የገቢዎች ሚ/ር ነው። ዛሬ በነበረው የጉባኤ ባህሬ ላይ አንድ ያስተዋልኩት ቁምነገር አለ። ዶር አብይ አህመድ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚ/ በነበሩበት ጊዜ ከእርምጃ ወደ ሩጭ በተዘጋጀው ጉባኤ ላይ የነበረው ሙሉ መንፈሳቸውን አይቻለሁኝ። ዘና ያለ ሁኔታ ብቻ ሳይሆን እርግጠኛ የመሆን አቅሙም ያን ያህል ጉልበታም ሆኖ ነው ያዬሁት፤ በግራ በቀኝ የሚወራጨውን የማህበረ ደራጎን የተስፋ ንጥቂያ ዘመቻ እና ትብትብ ሴራ ከመጤፍ አልቆጠሩትም። እንደ ዛን ጊዜው ሚ/ር እንደነበሩበት ወቅት ቅልል ብሏቸዋል። https://www.youtube.com/watch?v=vu-kkIUohRw&t=76s Ethiopia - Dr Abiy ኢትዮጵያን ማሸጋገር ይቻላል ! ከራዕያቸው ለመድርስ በሚያደርጉት ጉዞም አሸነፊ ሆኖ የመውጣት መንፈስ ልክ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ በነበረው አቅም ልክ ነው እኔ ያዬሁት -ዛሬ። ሁልጊዜም እኔ እንደምለው ንግግሩን ብቻ ሳይሆን የሰብዕን ውስጣዊ መንፈስ ለማግኘት ወደ ውስጥ ሰርስሬ ማዬትን ነው ምርጫዬ። ዛሬ የሰጠኝ ግብረ ምላሽ በጠ/ሚር አብይ አህመድ በኩል የመንፈስ ሙሉዑነት ...