ልጥፎች

‹‹ጠቅላዩ 1 ሺህ አመት መዋጋት አይችሉም›› | ‹‹ብልጽግና ከጦርነቶች መማር አልቻለም..›› | Ethiopia ብቁ ገለፃ።

ምስል

ዓለማችን የመደራጀት ውጤት ናት። Unsere Welt ist das Ergebnis von Organisation. ስለ መደራጀት ጽንሰ ሃሳብ ለመነሻ የሚሆን ጭብጥ። ጠቃሚ ማብራሪያ። ሸበላ ሰንበት። አሜን። አክባሪያችሁ ሥርጉትሻ025.01.24

ምስል

የአማራ እናት ተስፋ በዬዘመኑ ለቃጠሎ።

  የአማራ እናት ተስፋ በዬዘመኑ ለቃጠሎ።   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   ማህበረ አወንታውያን እንዴት አደራችሁልኝ??? ዛሬ የረባ እንቅልፍ አልወሰደኝም። እስከ መቼ የአማራ እናት ማህጸን ተስፋ #በቃጠሎ ይንደድ - ይገረፍ - ይንደድ? ይህ ጉዳይ በበቂ የዓለም ህዝብምሆነ የየክልሎ መስተዳድራትም በተለይ የአማራን ስቃይ በአስተዳደራቸው ለማይፈቅዱት፤ #ለአፋር ፤ #ለሱማሌ ፤ #ለሲዳማ ክልል መስተዳደር ፕሬዚዳንቶች በትህትና እና አክብሮት ላሳስባቸው እወዳለሁኝ። የአማራ እናት ኢትዮጵያዊ አይደለችምን? የአማራ እናት ልጇን ልዑላዊነትህን አስከብር ብላ መርቃ፤ #ሰንቃ አላበረከተችምን? ነበረ በሚባለው የአገር ጉዳይ በግንባር ቀደምትነት ባትላ ያሳደገቻቸውን ልጆች ፈቅዳ አልሰጠችንም? የአድዋ፤ የጉንዲት፤ የመተማ፤ የካራማራ፤ የባድመ ጦርነቶች ላይ ማህፀኗን እማ ቅንዬ የአማራ እናት አልገበረችንም???   ስለምንድን ነው የአማራ እናት በዬዘመኑ መጣ ለሚባል ሥርዓት ሁሉ ተስፋዋ #ማገዶ የሚሆነው? ለምን? ትናንት ቢቢሲ የአማርኛው ዜና ባወጣው ዘገባ ጥምቀት ሙሽሪት ሲባልላት በመንግሥት ሚዲያ ሲሸበሸብላት የሰነበተችው ጎንደር እና በቅኔው ጎጃም በመንግሥት ታጣቂወች ከፍ ያለ ጉዳት ደርሷል ይላል ዘገባው። "አጥንት ውስጥ፤ ደም ውስጥ አለች" ለምትባል ኢትዮጵያ መጠኑ ያለፈ ግፍ እና መበደል ሰርክ የሚደርስበት የአማራ ልጅ የዳር ልጅ ስለሆኑ ይሆን የአማራ ልጆች እንዲህ በመታገት፤ በመሰወር፤ በባሩድ፤ በካቴና፤ በመገለል፤ በስጋት፤ በጭንቀት፤ በበቀል፤ በጥላቻ የአማራ እናት ማህፀን የሚቀጠቀጠው ስለምን ይሆን።    የማነሳው እጅግ መራራ ነገር ነው። ሂደቱ ጎምዛዛ እና ድቅድቅ በመሆኑ የእኔ ማህፀንም እርር ኩምትር እያለ ነው። ...

#የገለበጠም #የተገለበጠም #የለም! #በሞቴ መንግስት መገልበጥ #አይሰልችህና #ሞካክረው። እኛም እንይ ………

  #የገለበጠም #የተገለበጠም #የለም ! #በሞቴ መንግስት መገልበጥ #አይሰልችህና #ሞካክረው ። እኛም እንይ ………   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   እንዴት ሰነበታችሁ ማህበረ ቅንነት? እንዴት አላችሁልኝ። ውጭ የምትኖሩ ወገኖቼ ዓውደ- ዓመቱ እንዴት ይዟችኋል? ጥሞና መልካም ነገር ነው። ከቅንነት፤ ለመልካምነት ከታሰበ። መታደልም ነው።   ዛሬ ዕለቱን በአቶ (በሃጂ) ጃዋር መሃመድ ዙሪያ የግል ዕይታዬን ላጋራ ወደድኩኝ። ፁሁፋ ሊረዝም ይችላል። ለብሎጌም ጭምር ስለምሰራም። በተጨማሪም የምዕራፍ ፲፬ መከወኛ ፁሁፌም ስለሆነ።   የአቶ (የሃጂ) ጃዋር ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ማቀዱ ከምን አንፃር ነው? 1) የማህበረ ኦነግ የቤተ - መንግሥት ቆይታ እንዳያጥር ከመስጋት። 2) የማህበረ ኦነግ በትረ ሥልጣን ከተናደ አማራጭ ሆኖ ለመቅረብ። #ሁለቱ ሃሳቦች መነሻወች መንታ ፍላጎት አላቸው። 1) አገር እናድን ጥሪ። ይህ ለውጥ #ፈላጊነትን ያሳያል። ለውጡ ግን ወደ አመራር ሽግሽግ ዝንባሌ ያለው ሆኖ አግኝቸዋለሁኝ። 2) ምንም ቢሆን በኦሮሞ ሊቃናት የበላይነት የምትመራ ኢትዮጵያ ለመሪው አካል #ጥገናዊ አጥሚት አዘጋጅተን እናድነውም ዓይነት ነው።    #ፖለቲከኛ ።   …… ለዛውም ፕሮፌሽናል ፖለቲከኛ የፍላጎቱን አቅጣጫ መንታ መንገድ ላይ ሊገትር አይገባም ባይ ነኝ። A. B. C. D ፈተና ላይ እራስን አስቀምጦ የፍላጎት አቅጣጫን ጥርት ባለ አቋም፤ ጥርት ባለ ውሳኔ ላይ መነሳት ያስፈልጋል። አገር እንደ ጥንቸል የመሞከሪያ ጣብያ አይደለችም እና። ኤንም፦ ቢንም፥ ሲንም፥ ዲንም፥ ልሁን በትውልድ ላይ መፍረድ ይሆናል።    #አቶ (ሃጂ) ጃዋር መሐመድ።   በቅጽበት ከተከሰቱ...