ልጥፎች

#አድሎ እና #አግላይነት ይቁም! "ከልጅልጅ ቢለዩ ዓመትም አይቆዩ።" ኮሚሽኑ የክት እና የእዳሪ ልጅ አለው። #የቀዝቃዛው ጦርነት ሂደት ቀጥሏል።

ምስል
  #አድሎ እና #አግላይነት ይቁም! "ከልጅልጅ ቢለዩ ዓመትም አይቆዩ።" ኮሚሽኑ የክት እና የእዳሪ ልጅ አለው። #የቀዝቃዛው ጦርነት ሂደት ቀጥሏል።   "ከክፋ ሸሽ፤ መልካሙን አድርግ፤ ለዘላዕለም ትኖራለህ።" (መዝሙር ፴፮ ቁጥር ፳፯)       ለምክክር ኮሚሽኑ የቤት ልጅ አቆላማጭ፤ አባባይ ልዩ ኮሚቴ አቋቋመመ።   የማይገባኝ የማህበረ ኦነግ ቤተኞች ኢትዮጵያዊነትን የሚያገሉበት፣ እነሱን ከኢትዮጵያዊነት መንፈስ አውጥተው የመንፈስ ውጊያ በየዘመኑ የሚያደርጉበት፣ እኛን ገፍተው ዶክትሬናቸው እኔ - እኔ - እኔ - የእኔ - የእኔ - የሚሉበት ጉዳይ ነው። እኛ እኮ በውስጣቸው ፈጽመን የለንም። ኧረ እኛ አማራነት አለ በዘር ሐረጋችን ሌሎችን ወገኖቻችን ቢያንስ የእኛ የማይሉበት ምክንያት አይገባኝም።   #የሆነ ሆኖ ………   "በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ኮሚሽኑን የሚያግዝ አዲስ ኮሚቴ ተዋቀረ " ሪፖርተር።" ይህ ጉዳይ በቅጡ ምላሽ ካላገኜ ከፋኝ ላሉት ታጣቂወች ንጥረ አመክንዮ ይሆናል። አቅማቸውን ይጨምራል። ተስፋቸውን #ያደረጃል ። የተበተነ መንፈስንም ይሰበስባል። በተለይ ሳይለንት ማጆሪቲውን የማቅረብ ሁነት ይፈጥራል።    አሰላ የአርሲ ፎለቄ ዋና ከተማ፤ በደምብ ነው የማውቃት። ጅማ ተወዳጁ የከፋ ክ/ አገር ዋና ከተማ፤ መቱ የደጋጎቹ የኢሊባቡር ዋና ከተማ፤ ነቀመት ተናፋቂው የወለጋ ዋና ከተማ፤ ድሬ እናታዊ የሁለመና ደማቅ ከተማ፤ ደብረዘይት ውዷ እታጌዋ ከተማ፤ ሻሸመኔ የህብራዊነት አብነት ከተማ፤   ናዝሬት ብቋዋ የደህንነታችን ዋስትና ከተማን አንድም ሳቢነት፤ አጓጊነት ሳያክል ጠቅልሎ የያዘው የአቶ አባዱላው #ኦህዴድ ፤ በጠቅላይ ሚ/ር አብይ አህመድ ...

#ሽኝት ሆድ ያረባብሻል። ይገባልም።

ምስል
  #ሽኝት ሆድ ያረባብሻል። ይገባልም።   ገዳይዚም ተመስጥሮ ሳይሆን ተገልጦ ነው የተጀመረው። መሪወቹ ነግረውናል እኮ። ስለዚህም ከገዳይዝም ከተፈጥሮው የሚመነጩ አስደንጋጭ ክስተቶች የግድ ይሆናሉ።    "እኔ ሰምቻለሁ፤ ልቤም ደነገጠብኝ፤ ከድምጹ የተነሳ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፤ መንቀጥቀጥ ወደ አጥንቶቼ ገባ በስፍራዬ ሁኜ ተናወጥሁ፤ በሚያስጨንቁን ህዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ፤ የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁኝ።" (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፮።)         መነሻዬ ከዋዜማ ራዲዮ አቶ ዳንኤል በቀለ ሼር ያደረጉት ቁምነገር ነው።   #ሽኝት ።   የፈለገ ነገር ይደርደር፤ የፈለገ ነገር ይቀመር፤ የፈለገ ነገር ይሽሞንሞን፤ የፈለገ ነገር ግጥግጥ ላይ ይሁን የአዲስ አበባ ሁነት እንዲህ በጎሼ፤ በአጎረፈ፤ በአጎፈረ ሁኔታ እልል ተብሎ አሸኛኜቱ ሊጸድቅ አይገባም። አንበሳው አብዲሳ አጋ፤ አርበኛ አብርኃም ደቦጭ፤ አርበኛ ሞገስ አስጎደም፤ አርበኛ ዘርዓይ ደረስ፤ ሰማዕቱ ብጹውወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ "ኃይለማርያም ማሞ የጦሩ ገበሬ፤ ፈረሱን እንደ ሰው አስታጠቀው ሱሪ" እንዲህ በለብ ለብ፤ በግብር ይውጣ ሁነቱ ስክነት አንሶት ብይን ሊሰጥበት አይገባም።    በባዶ እግር ቤቱን ትዳሩን ትቶ፤ ሞፈር ተፈቶ የፈሰሰው ደም እና አጥንት፤ ሰማዕትነት አጥንት ወጥቶ ሊጠቀጠቅ አይገባም።   ይቺ አገር የኩባ፤ የራሽያ፤ የየመን፤ የአርመኖች መንፈስ የተገበረላት የዘጠኙ ቅዱሳን የመንፈስ ማረፊያ፤ የነብዬ መሐመድ የነብይነት ልክ የተገለጠባት ጠይም ዕንቁ ናት።   በአንድ ዞግ ባህል እና ትውፊት፤ ፍላጎት እና ግብ ልትመራ አይገባም። ህብራዊ - ሥናዊ፤ ቅባዕዊ ጸጋዋ ይፈገፈጋ...

ጥልፍ የሥነ ቃል ጥልፍ።

  • ጥልፍ የሥነ ቃል ጥልፍ። ዕለተ ሰነበት ማዕዶተ ርትህ ወሰባዕዊነት በከበቡሽ የቁራሽ አንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። ጥልፍ የሥነ ቃል ጥልፍ። ጥልፍ „አቤቱ ታድነኝ ዘንድ ፍቀድ፤ አቤቱ እኔን ለመርዳት ፍጠን“ መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፴፱ ቁጥር ፲፫ ጠብታ! ዘለላ- የመንፈስ ወለላ መዳፈ-ጥልፍ ጠፈፍ! አልቦሽ ጠረፍ ብራና ላይ ሲንጠፈጠፍ ዛላው ሲርገፈገፍ ጊዜ አይሽረው አይነጥፍ አይሆን ጠፍ ጥልፍ! ብዕረ ምጥ-የቁርጥ የቀለም ሰርጥ ንጥር የምናብ መረቅ ነበልባላዊ መንፈስ አቅልጥ ጥልፍ! የቅመም ውቅጥ የተግባር ነቁጥ ወልጋዳን ቆንጥጥ፣ ተባደግን አፍርጥ-ደፍጥጥ ጥልፍ! ነው ጥልፍ የኮፒ እንፋሎት፣ ፍ ላ ሎ ----------- ት ሮ ኆ ቦ ------------ ት ጥልፍ! ዘይቢያዊ ንቅሳት ነቀል - ተከል፣ የሌለበት ቀድሞ የሚያልፍ፣ አይደለም ግርድፍ ማገሩ አለው ውብ ዘርፍ የሚያዘርፍ፤ ጥልፍ! ገለባን የሚቀርፍ ድቃቂን የሚያራግፍ፣ ባለ ጥርኙ ጥልፍ ፍቅርን የሚያሳቅፍ ጥልፍ! የአብረንታት ጥልፍ ደፋ...

እ። ምን ልል ነበር አያ? ኧረ አወን ልበለው። "የታስራችሁ #የተሰውታችሁ እንይ" ምኞት። "በሞኝ ክንድ ዘንዶ ይለካበታል።"

  እ። ምን ልል ነበር አያ? ኧረ አወን ልበለው። "የታስራችሁ #የተሰውታችሁ እንይ" ምኞት። "በሞኝ ክንድ ዘንዶ ይለካበታል።"   "እግዚአብሄር እዮብን ልቡ ከኃጢያት፤ እንደነፃች ባየው ጊዜ፤ በብዙ ክብር ተቀበለው።" (መቃብያን ም ፰ ቁ ፪)   ምዕራፍ ፲፱።   ጤና ይስጥልኝ ክብርት ኢትዮጵያ እናት አገሬ፤ ጤና ይስጥልኝ እምዬ ሲዊዝሻ ርህርህተ - አገር፤ ጤና ይስጥልኝ ኮሽ አይሏ ደጓ፤ እየኖርኩብሽ እማልጠግብሽ ቢንተርቱር ከተማ (Winti) ጤና ይስጥልኝ አዱኛወቼ ቤተ - ሥርጉትሻ እንዴት አድራችሁ? እንደምንስ አረፈዳችሁልኝ? "በአገራዊ" የምክክር ኮሜሽን ቅሬታ ያላቸው ተቋማት፤ የተከፋ ተሳታፊወች "ጉባኤውን ረግጣችሁ ውጡ፤ ምን ትጠብቃላችሁ፤ ሞትም እስራትም ቢመጣ ተጋፈጡት፤ የሚል ጨካኝ ሃሳብ አዳመጥኩኝ። "ያልተነካ ግልግል ያውቃል" እንዳልል ሃሳብ አራማጁ በዘመነ - ህወሃት፤ በዘመነ - ብልፄው ታስሮ የተንገላታ፤ የተሰደደም ነው።    በተለይ የአማራ ተወያዮች "በነውረኛ ቃል ዘለፋ፤ በክፋ ዓይን መገረፍ፤ በተሳትፎ ላይ ዕድል መነፈግ፤ ግልምጫ፤ ማሳደድ ተካሂዶብናል" ብለው ቅሬታቸውን ለምክክር ኮሚሽኑ አቅርበው አድማጭ ማጣታቸው ነው "ጥለው ይውጡ ምን ይሠራሉ? ይውጡ እና የሚመጣውን ይጋፈጡ" የሚል ሃሳብ ተሰጣቸው።    ወጣትነት ትዕግሥትን የሚፈትን ስለሚሆን ይሆናል። ወጥተው የት ይሂዱ እነኝህ ቅሬታ አቅራቢወች? ሰማዩም ምድሩም እኮ #በብልፄው መንግሥት ሥር ነው። ምንድን ነው ወጥተው የሚያተርፋት? ማንስ አላቸው???? መቼም ከ፵ ሚሊዮን ህዝብ በላይ ስደት ሊያስብ ይቻል ይሆን ሎጅኩ? ልሰደድ ቢልስ ይችላልን???   የአማራ ተሳታፊወች ጉባ...