የአብይን የቅንነት ሌጋሲ ለማሰቀጠል ብቻ እንትጋ።
የመረጋጋት ስንቅ። ከሥርጉተ ©ሥላሴ 11.-8.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። „እኔ ግን በምህረትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ፤ አንተን በመፍራት ወደ ቅደስናህ መቅደስ እሰግዳለሁ።“ መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፬ ቁጥር ፯ ከሥርጉተ ©ሥላሴ 11.-8.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። · መነሻዬ https://www.youtube.com/watch?v=QN9CQEMiLVE Ethiopia: [ ሰበር ዜና !] ከዶ / ር አብይ ስለ ሶማሌ ክልልና የአቡነ መርቆርዮስ ጉብኝት የተሰጠ መግለጫ ! የሆነው ሁሉ ባይሆን መልካም ነበር። ብቻ ይሄ ቪዲዮ አንፃራዊ ነፃነት ያለው ነው። መንፈሱም ጤነኛ ነው። ቀጣዮቹ ጊዘያቶች ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ባላውቅም ከሰነበትንባቸው ጭጋጋማ ማዕልተ ሌሊቶች የተሻለ ተስፋ ያለው ነው። መሆን ያለበት ዓለም አቀፍ ተጽዕኖው በተከታታይ ማስቀጠል ነው። የሆነው ሁሉ ለመልካም ቢሆንም አሁንም ሴራ እና ሼር ሊያርፉ ስለማይችሉ የቅኖች መንፈስ የአብይን ሌጋሲ የማስቀጠል ተግባር ላይ መታተር ያስፈልጋል። ይሄ ቁስል እዬቀራረፉ ግጭትን የሙጥን የማለትን ሂደትን አቆሞ መድንህን የሆነውን የአብይ መንፈስ በቀደመው ሃይሉ እና ብቃቱ ይቀጠል ዘንድ የላዩን ጉዞ ተግ አድርጎ ውስጣዊ የሆነ ድጋፉን በእውነተኝነት እና ስሜት መቀጠል ነው። የሆነው ሁሉ ለበጎ ...