ልጥፎች

እስከ መቼ የአማራ እናት ማቅ ትልበስ? "በአማራ ክልል ሁለት ዞኖች በአንድ ቀን 20 የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸውን ቤተሰቦች እና የዓይን እማኞች ተናገሩ" BBC

ምስል
   https://www.bbc.com/amharic/articles/c05l75z6lnpo   "በአማራ ክልል ሁለት ዞኖች በአንድ ቀን 20 የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸውን ቤተሰቦች እና የዓይን እማኞች ተናገሩ"   የአለፋ ወረዳ ዋና ከተማ ሻሁራ፤ ጥቃት የተፈጸመበት አምቻሆ ቀበሌ 30 ሻሁራ 16 ኪ.ሜ ገደማ ይርቃል ከ 8 ሰአት በፊት "በአማራ ክልል ማዕከላዊ ጎንደር እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች "በመንግሥት ኃይሎች" በአንድ ቀን በተለያዩ ሰዓታት ውስጥ ተፈጸሙ በተባሉ ጥቃቶች 20 የሚሆኑ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን የተጎጂ ቤተሰቦች እና የዓይን እማኞች ለቢቢሲ ተናገሩ። የጥምቀት በዓል በተከበረ በማግስቱ ሰኞ በማዕከላዊ ጎንደር፣ አለፋ ወረዳ እንዲሁም በምዕራብ ጎጃም፣ ቋሪት ወረዳ በዓል በሚያከብሩ እና በእርሻ መስክ ላይ ለከብቶች መኖ ሲሰበስቡ ነበሩ በተባሉ ሰዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት ነው ግድያው የተፈጸመው። በሁለቱም ዞኖች ውስጥ በአንድ ቀን የተፈጸመውን ጥቃት በተመለከተ ቢቢሲ የየአካባቢዎቹን ነዋሪዎች፣ የዓይን እማኞችን እና የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ቤተሰቦችን ያነጋገረ ሲሆን፣ የአካባቢዎቹ አስተዳዳሪዎችን ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም። በክስተቱ ከተገደሉት ሰዎች መካከል አንድ ቄስ እና ታዳጊ ልጆች እንደሚገኙበት የተናገሩት የቢቢሲ ምንጮች ሁሉም ሰላማዊ ነዋሪዎች መሆናቸውን ተናግረዋል። ቢቢሲ ይህንን መረጃ ከገለልተኛ ወገኖች ማረጋገጥ አልቻለም። በእነዚህ ሁለት ክስተቶች ተገድለዋል ከተባሉት ሃያ ያህል ሰዎች በተጨማሪ ሌሎች በርካት ያሉ ሰዎች በጥይት እና በድብደባ አካላዊ ጉዳት እንደደረሰባቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል በተለያዩ የአማራ ክልል ክልል አካባቢዎች ከአንድ ዓመት በላይ በሆነው በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች...

#የጃዋሪዝም #ሞገድ #ዳጥ።

ምስል
  #የጃዋሪዝም #ሞገድ #ዳጥ ። "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   ማህበረ አወንታውያውያን እንዴት አደራችሁልን? አወንታውያን የትውልድ #አንበል ናችሁና ደህንነታችሁ በእጅጉ ያስፈልገናል።   #ጠብታ ።   ትናንት ከአዲስ ኮንፓስ ጋር ውይይት ያደረገ ወጣት ጋዜጠኛ ነበር። ብዙ ጊዜ ሳዳምጠው ለእናት አገራችን ለኢትዮጵያ ያለውን ንጹህ ቅንነት አይበታለሁኝ። ለዚህም ነው ጊዜ ሰጥቼ የማዳምጠው። በጋዜጠኝነትም ህይወት ውስጥ ዝልቅ ተመክሮ ያለው ወጣት ነው። በዬትኛም ሁኔታ፤ በማናቸውም ጊዜ #ቅንነት ካዬሁ ወይንም ካዳመጥኩ እሳባለሁኝ። መዳኛችም ቅንነት ነው። ውድቀታችንም የቅንነት ፍልሰት ነው። • https://www.youtube.com/watch?v=AC2qgGIlmbI «የትራምፕ መንገድ፣ ለውጡና ምክክሩ፣ "ጊዜያዊ የተኩስ አቁም"   ወጣቱ ጋዜጠኛ አንተነህ የብልጽግና ጉዞውን የሚደግፍ ይመስለኛል። በጠሚር አብይ አህመድ የአመራር አቅምም ላይ ተመስጦ እንዳአለው አስተውያለሁኝ። ይህ ሙሉ መብቱም ነው። እኛ እንቃወም የለምን? ጋዜጠኛ አንተነህ ሙግት ሲኖርም በቀጥታ ይሞግታል። በተለይ ፕሬስ ህግጋት ላይ።   ስለ አዲስ አበባ ትናንት ሲገልጥም የመከፋት ግን ጊዜን የመጠበቅ አስፈላጊነት ፍንጭ የሚሰጡ ዝንባሌወችን አዳምጫለሁኝ። ዕውነት ለዴሞክራሲ የምንታገል ከሆነ የሚመቸንም፤ የማይመቸንንም ሃሳብ እኩል አዳምጡ ሳያጋንኑ፤ ወይንም ሳያይሸበሽቡ በሃሳብ መሞገት የተገባ ይሆናል። ያ ሃሳብ በብዙኃኑ ድምጽ ከፀደቀ በዛ መገዛት ግድ ይላል። እኔ እንዲያውም እኔ የማራምደውን ሃሳብ ከሚያነሱት ይልቅ ከእኔ ለዬት ያለ ሃሳብ ያላቸውን ባደምጥ እመርጣለሁኝ።   በአዲስ አበባ የቤቶች ፍርሰት ሁኔታ ዴሞግራፊ አለ ስለሚባለው ተጠይቆ እንደዛ ...