ልጥፎች

ህወሃት እና የአዝመራ #ዘረፋው በወርሃ የካቲት ትውፊቱ ነው። ህዋህታዊነትስ - ምን #ጠቀመ፤ ምን አከሰረ?

  ህወሃት እና የአዝመራ #ዘረፋው በወርሃ የካቲት ትውፊቱ ነው። ህዋህታዊነትስ - ምን #ጠቀመ ፤ ምን አከሰረ?   "ከአጋም የተጠጋ ቁልቋል ዘለዓለም ሲያለቅስ ይኖራል።" መጥኒ ላንች እቴጌ ጎንደር። ልብ በአቅል ግዢ ከአጤወችሽ።    "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   #ምዕራፍ ፲፰። ዘለግ ያለን ትዕግሥት እና ማስተዋል የናፈቀው የወግ ገበታ ነው ለማህበረ ቅንነት።    #መቅድመ ፍሬ ነገር።   ጤና ይስጥልኝ የአገሬ ልጆች እንዴት አደራችሁልኝ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። ከእኛ ቅዝቃዜውም ለክፋ አይሰጥም። ካናዳ እና አገረ አሜሪካ ያሉ ወገኖቻችን ከቶ እንደምን አድረው ይሆን?   በውነቱ ህወሃትን በሚመለከት ምንም ለማለት ፈጽሞ አልፈልግም ነበር። ከምል "ሙያ በልብን" ብከውን የተሻለ ቀና መንገድም ነው ብዬ አምናለሁኝ። ለዛውም እኔ የልቤ ደርሶ፤ መሻቴ ተሳክቶ #የጃርት ጉባኤው የህወሃት ተንጠራርቶ፤ ተወራኜቶ #አራጦ የመግዛት ዘመኑ #እርሾ አልባው ክትመቱን ከማዬት በላይ መታደል ስለለ ግራ ቀኙን በትዝብት፤ በዝምታ ማየቱ ምርጫያ ነው።   ነገር ግን ዘመኑን ሁሉ በድንጋጤ፤ በጭንቀት እና በስጋት እንዲኖር የተፈቀደበት፤ የተፈረደበትም ሁነትን አስመልክቶ ለአዲሱ ትውልድ ትንሽ መረጃ ብሰጠው አይከፋም በሚል ነው አመጣጤ። ህወሃትን መንገድ መሪነት የተቃጠለ፤ ኤክስፓየርድ ያደረገ የአስተሳሰብ ድህነት ነው። የህወሃት ጉዞ በየትኛውም ሁነት ሊገታ ይገባል።   " #ከአጋም የተጠጋ ቁልቋል፤ ዘለዓለም ሲያለቅስ ይውላል።"   ወርኃ የካቲት የስሜን ጎንደር ገራገር ንጹህ ገበሬ ዓመቱን ሙሉ የለፋበት አእዝርቶቹን ሳይዘራ፤ ሳያርም፤ ሳያጭድ፤ ሳይወቃ የኖረ #ሰ...

ዓለም እና #ዛሬወነገ። የዓለማችን ፖለቲካ #ኢንፍሌሽን (ግሽፈት) እንደገጠመው ይሰማኛል።

ምስል
  ዓለም እና #ዛሬወነገ ። የዓለማችን ፖለቲካ #ኢንፍሌሽን (ግሽፈት) እንደገጠመው ይሰማኛል።   ስለሆነም ዓለማችን በጠና ታማለች። አይዞሽ ባይ #አጽናኝ መንፈስ ትሻለች። #አናርኪዝምም ያስፈራኛል።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።       #ምዕራፍ ፲፰ በርከት ያሉ ዕርዕሰ ጉዳዮች በአንድ የወግ ገበታ።   ዓለም የመረጠችው ጎዳና በሁሉም ዘርፍ ጭንቅ ሆኗል። ጫናም በዝቶባታል። በሌላ በኩል የዓለማችን ፖለቲካ ኢንፍሌንሽን የገጠመው ይመስለኛል። በዘመኑ የፖለቲካ ባህሪ አንፃር ሳስተውለው ካፒታሊዝም እድገቱን ጨርሶ ወደ #ኢንፕሪያሊዝም እያማተረ ይመስለኛል። ስለሆነም የፖለቲካ ሊቃናት ሰራሽ ችግሮች የተሻለ ዕድል ያገኙ ይመስለኛል። የህዝብ የመወሰን አቅም ደግሞ ፈተና ላይ የወደቀ ይመስለኛል። ይመስለኛል እምለው ጥናታዊ መረጃዊ ሁነትን ስለአላካሄድኩ ነው።    በዚህ ዙሪያ የሁሉም የሃይማኖት ተቋማት አቨው የዓለማችን የመኖር ቀጣይነት በሚመለከት አጀንዳቸው አድርገው ስለ ዓለማችን የጸሎት ቀናትን ወስነው ሊተጉ የሚገባ ይመስለኛል። ዓለም ሃዘን ላይ ናት። አጽናኝ መንፈስ ትሻለች - ና።   በሁሉም ቦታ #ስጋት አለ። በሁሉም ቦታ የሰው ልጅን የሰው ልጅ ይገድለዋል። #ጭካኔ መለያ #ማልያ የመሆን ዝንባሌም አለ። በሁሉም ቦታ #የታመቀ ጭንቀት አለ። በሁሉም ቦታ አስፈሪው የጦርነት ሁነት አድማጭ አግኝቶ ገኖ ይታያል። ጦርነት ተፈጥሮ ሰራሽ አይደለም። ጦርነት ፖለቲካ ሰራሽ ቀመር ነው። ፖለቲካ ደግሞ የሰው ልጅ የሚፈላሰፍበት አንኳር የዕውቀት ዘርፍ ነው።   ስለሆነም ጦርነትን የሚያነሳሱ፤ የሚገፋፉ፤ የሚያበረታቱ ሁነቶችን መግታት ፖለቲከኞች ይችላሉ። ግን ፈቃዳቸው እንብ...

#የበረዶ #ወጀብ በአሜሪካ እና በካናዳ። ዘገባው የቢቢሲ BBC ነው።

ምስል
  #የበረዶ #ወጀብ በአሜሪካ እና በካናዳ። ዘገባው የቢቢሲ BBC ነው።    " አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   ለሰው ልጅ ሊቆጣጠረው የማይችል የተፈጥሮ አደጋ በቂ ነው። ይህን መሰል ችግር አሳሳቢ ነው። አሜሪካ እና ካናዳ ለሚኖሩ የዓለም ዜጎች ሁሉ ፈጣሪ አምላክ #ምህረቱን ይላክላቸው። አሜን። በየሰዓቱ የሚሰማው ዜና እጅግ አሳሳቢ ነው። በሁለቱም አገሮች ሰፊ ቁጥር ያላቸው ወገኖቻችን አሉን። የእኔ ድንግል ጥላ ከለላ ትሁናቸው። አሜን።   በበረዶው ምክንያት ህይወታቸውን ላጡ ሁሉ ነፍሳቸውን በገነት ያስቀምጥልን አምላካችን፤ አላሃችን። በሌላ በኩል መኖራቸው ለተጎሳቆለ፤ የዕለት መብራት ላጣ፤ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ፤ ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ሁሉ አምላካችን አብዝቶ መጽናናትን ይስጥ አሜን። ለዚህ መሰል ተፈጥሯዊ ያልተለመደ ክስተት ፈጣሪ ምህረት ይልክ ዘንድ ብሄራዊ የጸሎት ቀን አውጆ ጥሞና ማድረግ ይገባል።   ሥርጉትሻ 27/02/2026   አምላካችን ሆይ! ምህረትህና ቸረንተህ አይለዬን። አሜን።   • https://www.bbc.com/amharic/live/c62vk0jmnpzt "በአሜሪካ በተከሰተው ከባድ የአየር ሁኔታ ቢያንስ 21 ሰዎች ሞቱ" «በአየር ሁኔታ ምክንያት በአሜሪካ ከ10 ሺህ በላይ በረራዎች ተሰረዙ» https://www.bbc.com/amharic/live/c62vk0jmnpzt «ካለፈው ሳምንት ማብቂያ ጀምሮ በአብዛኛው የአሜሪካ ግዛቶች ውስጥ በተከሰተው ከባድ ቅዝቃዜ እና የበረዶ ወጀብ የተነሳ እስካሁን ድረስ ቢያንስ 21 ሰዎች መሞታቸው ተዘገበ።   የተለያዩ ግዛቶች ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት ከተከሰተው ከባድ የክረምት ቅዝቃዜ ጋር በተያያዘ በበርካታ ግዛቶች ውስጥ እስከ ሰኞ ሌሊት ድ...

የኢትዮጵያ ፖለቲካ #ሰው ማትረፍ ለምን #አጀንዳው አይሆንም?

ምስል
  የኢትዮጵያ ፖለቲካ #ሰው ማትረፍ ለምን #አጀንዳው አይሆንም?   «ሁሉ ተፈቅልኛል፤ ሁሉ ግን አይጠቅምም።»       #ምዕራፍ ፲፰።   እጅግ የማከብራችሁ የአገሬ ልጆች እንዴት ሰነበታችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? ጤና ይስጥልኝ አገሬ ፈላስፊት ኢትዮጵያ እንዴት ባጀሽ? እንደምንስ ትሆኛለሽ? ጤና ይስጥልኝ እየኖርኩብሽ ሁልጊዜም የምትናፍቂኝ እመዬ ሲዊዝሻ።    #መግቢያ ።   ይገርመኛል። በእጅጉም ያስደነግጠኛል። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ለሰው ተፈጥሮ ሰውን ለማዳን አይታትርም። እንዲያውም ጉልበት ላለው አካል ምን እዬሠራህ ነው? እንዲህ ተብለሃል? እንዲያ ተብለሃል በማለት የኢትዮጵያ እናቶች #ሰቀቀን ናፋቂ ሆኖ ነው እማዬው። እንዳላዩ ማለፍ፤ እንደ አላወቁ መተው ማንን ይገድላል? ተጨማሪ ስቀቀን ዕድሜ ዘመናቸው ዕንባቸው ለሚፈሰው የኢትዮጵያ እናቶች ስለምን አይታዘንም? ሁሉም #እናት አለው እና። አራት ነጥቦችን ልጅ ቴወድሮስ አስፋው ማብራሪያ ከሰጠበት ለናሙና ማንሳትን ፈለግሁኝ።   ያው የነገዋ ኢትዮጵያ ቀጣይ ታዳሚው እሱ ነውና። የእኛ ጊዜ እያበቃ ስለሆነ። ሚዲያው " #ሰላም " ነው። ቃሉ ይጣፍጣል። የሚጠይቀው ግን ሆኖ መገኜትን ነው። ልጅ ቴወድሮስ አስፋው በፋኖ ተስፋ ሊኖረው የሚችል እስኬው ሲኖርበት ብቻ ስለመሆኑ ጠቅሷል። ኢትዮጵያ እና ኤርትራንም የማን ደም ፈሰሰን እየተየኜ ነው?    ለነገሩ እስኪ #ዓይኑን አተኩራችሁ እዩት የልጅ ቴወድሮስ አስፋውን። የሚነግራችሁ ነገር ያለ አይመስላችሁም።    ፬ቱ #ነጥቦቼ ።   1) «ብልፅግናም #ተሽሎ አይደለም» «ብልፅግና ያልተረዳው የኮለኔሉ #ቅኔያዊ ንግግር : የእስክንድር "ይቅርታ" (ኢት...