ልጥፎች

የዓድዋ ድል ሆይ #ይቅርበለን።

ምስል
  #የዓድዋ ድል ሆይ #ይቅርበለን ።   እኛነታችን በግርማ፤ በሞገሥ ያላቀ፤ የእኛነታችን ንጥረ ነገር ለዓለም የገለጸ #ራዲዮሎጂያችን የዓድዋ ድላችን።    "አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁኝ።"      የዓድዋ ጥንካሬ፤ ብርታት፤ መንፈስ፤ ህይወት፤ አቅም እና ክህሎት #ዊዝደሙን አክሎ ከእኛ ጋር ይሁን። አሜን። አድዋ - ለእኔ፤ ዓድዋ - ለእኛ፤ ዓድዋ ለሁላችንም እኛነታችን የሰጠን፤ የማድረግ፤ የመሆን አቅማችን ለዓለም የገለጠ #ራዲዮሎጃችን ነው። እኛስ ለዓድዋ ድል ምን አደረግንለት?   እኛስ ምን ለዓድዋ #ዕውነት ምን ሆንለት? በጎሳ፤ በዞግ ተከፋፍለን የድሉን አልማዛዊ ብርኃን #አደበዘዝንበት ። የስላቅ መደርደሪያ ካንፓስ ሆንበት። እኛ ለዓድዋ ለተፈጥሯዊ አቅሙ #እንቅፋት ሆንበት። ይህ እርግጥ እና ዕውነት ነው። የአድዋን ክብር እና ልዕልና አብዝተን ተዳፈርነው። አንድነትን ዓድዋ ሰጠን። እኛ ግን ለመቆራረጥ ህግ አርቅቀን አጽድቀን #በአንቀጽ 39 ስንፎክር እንገናኛለን።    ጋዜጠኛ ሆኖ የአንቀጽ 39 ሞጋች ከመሆን በላይ ምን አሳፋሪስ፤ አንገት አስደፊ የታሪክ አሰርነት አለና? ኢትዮጵያ አጀንዳዬ አዬደለችም ማለትስ ከማን ከዬት የተወረሰ #ቋቁሻዊ ዕሳቤ ይሆን???? በውነቱ አውቀንም ይሁን ሳናውቅ፤ ልካችን ሳናውቅ በዓድዋ ድል #ክብር ዕውቀት የአመራር ክህሎት፤ ልቅና እና ልዕልና ልክ መሆን ላልቻልን የስንፍና #ግዞተኞች እግዚአብሄር አምላክ ማህሪ ነውና ምህረቱን ይላክልን። አሜን???    በውነት ተሳስተናል። በውነትም ከዊዝደማችን ጋር ፈቅደን #ተካክደናል ። ፈጣሪ መርቆ ከሰጠን ከብልህነታችን ጋር ወደን #ተላልፈናል እና የዓድዋ ድል ሆይ! ይ...

የዓለም አቀፍ ትኩረት በአቡ ዳቢ እና ዱባይ ጉርሻ page

ምስል
  "የዓለም አቀፍ ትኩረት በአቡ ዳቢ እና ዱባይ፡ ለታሪክ የሚቀመጥ ሰብዓዊ ውሳኔ የአየር ክልል መዘጋትን ተከትሎ በኤምሬትስ ተቀርቅረው ለነበሩ ከ20,000 በላይ ለሚሆኑ የውጭ አገር እንግዶች፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግሥት ላሳየው አርአያነት ያለው ተግባር ዓለም እያደነቀችው ነው።   "ማንም እንግዳ ከሆቴል አይውጣ!" የሚል ጥብቅ መመሪያ ለቱሪዝም ዘርፉ ተላልፏል። መንግሥት እንዳስታወቀው፣ የእንግዶቹ የሆቴል፣ የምግብ እና የሌሎች መሰረታዊ ፍላጎቶች ወጪ ሙሉ በሙሉ በመንግሥት ግምጃ ቤት ይሸፈናል።   መንግሥት ብቻ ሳይሆን፣ የግል ተቋማትም የድርሻቸውን ተወጥተዋል። በርካታ የቤት አከራይ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ቤቶቻቸውን ለተቸገሩ እንግዶች በነጻ ክፍት አድርገዋል።   ከምንም በላይ "መንግስት እንግዶቹን በሰላም እስኪሸኝ ድረስ ዋጋ መጨመርም ሆነ በራሳችሁ ተቻሉ የሚል አሰራር አይኖርም" መባሉ፣ አገሪቱ ለሰው ልጅ ክብር ቅድሚያ መስጠቷን ያሳያል።" Via the National ጉርሻ page

#በአረብ #አገራት በስደት የምትኖሩ ወገኖቻችን ሁሉ #ፈጣሪ አምላክ ይጠብቃችሁ። አሜን።

ምስል
  #በአረብ #አገራት በስደት የምትኖሩ ወገኖቻችን ሁሉ #ፈጣሪ አምላክ ይጠብቃችሁ። አሜን።    #ጦርነት #ጨካኝ ነው። ከዚህ እሳት አማኑኤል #ሁላችሁንም ይጠብቃችሁ። አሜን።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።     ሥርጉትሻ 02/03/2026 #ሰላምን #ያሰማን ። አሜን።

#እግዚአብሄር #አለቀሰ።

  #እግዚአብሄር #አለቀሰ ።   "አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።"   አርሲ ሆይ! ሁልጊዜ በተዋህዶ ልጆች ስለምን እንዲህ ጭካኔሽ አላባራም አለ። እኔ እማውቅሽ #ደጓ አርሲ ከቶ ምን እነ ማህበረ ኦነግ #አስነኩሽ ? የራስሽን ወገን? የራስሽን ህዝብ? የራስሽን ግብር ገባሪ፤ የራስሽን መንፈስ ምነው እንዲህ #በጭንቀት ታሳድጃለሽ? የነገው ትውልድሽ ምን እንደሚገጥመው ብታስቢበት ጥሩ ነው። ይህ መከራ ለልጅ ልጅ ተራፊ ነው። የፈጣሪ ቁጣ የመጣ ቀን ወዮ አርሲ???? ፈጣሪ ሆይ! ባለቤት የሌላቸውን #ንጹሃን አለሁላችሁ የሚል ድምጽ አሰማ። ማንም የላቸውም እና።    https://www.bbc.com/amharic/articles/c3v7elez0geo   በአርሲ ዞን ትናንትን ጨምሮ ባለፈው ሳምንት ውስጥ ከ30 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ምንጮች ተናገሩ   ሥርጉትሻ 02/03/2026 አቤቱ አባታችን እየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ምህረትህን #ለተጨነቁ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ላክ። አሜን።

ጥሩ መልክት ነው። #የተገባም።

ምስል
 

ዛሬ የምትሞግትለት ነገ አይገኝም። ጣሪያ ላይ ተንጠልጥሎ የራሱን #ኢንፓዬር ሲያንጽ ነው የሚገኜው።

 ፍቅር ሲጨንቀው ይጨንቃል። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 26/02/2022  ኢትዮጵያ ውስጥ ጭካኔ #ደልቧል ። #ፋፍቷልም ። ጨካኞች እንዲጨክኑ ኢትዮጵያ በጨካኝ መንፈስ እንድትታወክ ሊፈቀድ አይገባም። ፈጽሞ። የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያዊነት #መለያ #ዓርማ ጭካኔ እንዲሆን በፍጹም ሊፈቀድ አይገባም።  ኢትዮጵያን ከየትኛውም ጥቃት ተባብረን ልናድናት የምንችለው በኢትዮጵያ ውስጥ ተሰግስገው የሚገኙትን የጭካኔ ሃሳብ አራማጆችን #ሃግ ባይ ንጹህ ተቋም ሲኖር፤ በተጨማሪም፤ ጨካኞች እንዳይደላቸው ሰዋዊ ህጎችን ሥራ ላይ ለመዋል ሲወሰን፤ ለተግባራዊነቱ አብይዝም #ቁርጠኛ ሲሆን ነው።  በቃን! ጭካኔ። በቃ! መጨካከን። ሰው ከማትረፍ፤ ጓድን ከማዳን ይልቅ አሳልፎ መስጠት መንፈሱ ጲላጦሳዊ ነው። #ማዳን ቢያቅት የጭካኔ ማዳበሪያ መሆን #ይሰቀጥጣል ። የእኔ ክብሮች የኔወቹ ክፋ ሃሳብ እና ማህበርተኞቹን ቢያንስ #ሃግ እንበላቸው።  ሥርጉትሻ 27/02/2026    ከሥርጉትሻ ቤት የየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ደጋፊ መሪ ሊሆን ይችላል፤ ስድብ፤ ዘለፋ፤ ንቀት፤ በፎቶ ላይ ኤክስ ማድረግ፤ ፎቶ መዘቅዘቅ፤ የሰውን ልጅ እንሰሳዊ አድርጎ በፎቶ ሾፕ መስራት፤ ፆታዊ ያልተገቡ ቃላት፤ እያሉን ግን ነውረኛ የሆኑ ቃላት ልንጠቀምባቸው የማይገቡ ለምሳሌ "ጋለሞታ" ወዘተ አይፈቀድም። መራራ ስንብት ይሆናል። ይህ ትውልዱ በትክክለኛ የኢትዮጵያኒዝም ኦርጋኒክ ተፈጥሮ ልክ የሚበጅ ሃሳብ የሚያስተናግድ ፔጅ ነው። ወገንተኝነቱ ለመርህ እና ለፋክት ብቻ። #ሥርጉትሻ በነጣ አገልጋይ። መልካም ቀን። አሜን።  27/02/2026   ለኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ፖለቲከኞች ሰው ልጅ ብልህነት፤ ትጋት፤ ቅን ዕ...

ኢትዮጵያን ቁም ነገር የማድረግ ዓላማ በመሆን ውስጥ ይታያል።

ምስል
  ኢትዮጵያን ቁም ነገር የማድረግ ዓላማ በመሆን ውስጥ ይታያል።   ዕለተ አርብ ዕለተ ኢትዮጵያ! በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ።    „እግዚአብሄር የርስቴ እድል ፈንታና ጽዋዬ ነው።“ (መዝሙር ፲፭ ቁጥር ፭)     • መቅደመ ነገር። ቅኖቹ እኔ የምጽፈው ለቅኖቹ ብቻ ነው። የሰከኑ የረጉ መንፈሶች ብቻ ናቸው የመንፈስ ኃብታቴ ስኩን ታዳሚዎች። የቁጥር ተማሪ አይደለሁም። ለቁጥር ነዶ አይደለም እኔ እምተጋው። ለጥራት ፍሬ ዘር እንጅ።   በሌላ በኩል ጠማማ እቃናለሁ ካለ መብቱ ነው። ውሃ በቀጠነ ካለ አቅሙ እዬመጣ የአቲካራ አርኬቡ እክፍታለሁ ካለ ግን እልፍኜን ጥሎ ወለቅ ነው። የእኔ የህይወት ፍልስፍናም አይገባውምና። በመደዴ አይደፈርም። ስለዚህ ሜዳውም ፈረሱም …   … እልህ ፖለቲካ አይደለም። እልህ ምቹ ያልሆነ ገረጭራጫ የገረዘዘ ድወዬ በሽታ ነው። የእኔ ዕልፍኝ የጎንድ ተክለኃይማኖት ጠበል የለውም። ምን አልባት ለተደማሪ እና ለግንቦት 7 ቅሪተ አካል እዛ ኦዳ ቤተ -መንግሥት የተከፈተ የሥነ - ልቦና ማገገሚያ አለና ብቅ ይበል … ብራናዬን ለቀቅ።    • እፍታ።    አዎን ይታያል። አዎን የሚታይ ነው። አዎን መልክ ቅርጽ ገጽ አቋም አለው። አዎንታዊነት መነሻው ከአዎን ነው። አዎንታዊ ሰብዕናዎች ኢትዮጵያን ቁምነገር የማድረግ ዓላማ እና ግብ ያላቸው አሉ።   በአስተዳደግ መበደልም ይሁን በማላውቀው ሁኔታ ሙሉ ገጸ ባህሪያቸው አሉታዊ የሆኑ ደግሞ ይገጥማሉ። አዎን የሚሉት ጥፋትን ሊሆን ይችላል። ወይንም ክፋትን። ወይንም ጦርነትን። ወይንም ግጭትን። እንደዚህ ዓይነት ሰብዕናቸው ለአገር መድካማቸውም አይቀር...