#ምነው ጠፋሽ ከሩህሩኃን የቀረበልኝ ጥያቄ ነው። በስሱ እንሆ።
#ምነው ጠፋሽ ከሩህሩኃን የቀረበልኝ ጥያቄ ነው። በስሱ እንሆ። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ፣ ቀናውን መንፈስ በውስጤ አድስ።" አሜን። (መዝሙር ፶፩ ቁጥር ፲) የማከብራችሁ የአገሬ ልጆች፣ የምናፍቃችሁ ማህበረ - ቅንነት፣ የቤተ - ሥርጉትሻ #የልብ ክቡራን ቤተኞች፣ እንዴት ናችሁ? እኔ አምላኬ ክብረ ይስፋ ደህና ነኝ። #የምዕራፍ ፲፱ አጠናቅቄ፣ #ምዕራፍ ፳ን ለመጀመር አብዝቶ #ከማድመጥ ጋር ለመገናኜት፣ ለመዋህድም ጊዜ መውሰድ ነበረብኝ። ይህ ከምዕራፍ ፩ ጀምሮ የማደርገው የተለመደ ተግባር ነው። ጠቃሚም ጎዳና ነው። ፍላጎትን፣ ሃሳብን አደራጅቶ ለማቅረብ አጋዥ ነው። መልክ ይኖረዋል። #ቀለምም አለው። የእኔ የፌስቡክን ዕድል የምመራበት መስመር ነው። አግዞኛልም። ዛሬ ሁሉ #ተናጋሪ ነው። ሁሉንም ማድመጥ ባይቻልም፣ የዘመኑን ግሎባል፣ አህጉራዊ ይሁን ብሄራዊ የፖለቲካ ባህሪ ለማወቅ፣ ለመረዳት #ጥሞና ወስዶ፣ ለማድመጥ መፍቀድ ከበርካታ የግድፈት ማዕበል ይታደጋል። የፖለቲካ የኃይል አሰላለፍም ከዲጅታሉ ዓለም ጋር ተለዋዋጭነቱ ፈጣን ስለሆነ ጨምቶ የግል ገፊ ስሜትን ማስከን ይጠይቃል። ወጣትነት ተጠናቆ ወደ ጉልምስና ሲገባ የስሜት #ፍላትን ይሁን የፍላጎት ሱናሜን #ረብ ማድረግ፣ የአቋም ይሁን ውሳኔን ችኮላን #ተግ አድርጎ መመርመር፣ በእጁጉ ያስፈልጋል። ሙሉ #ዕድሜ በራሱ ከተደመጠም ያስገድዳል። ሁልጊዜ ወጣትነት የለምና። ሌላው በእናት አገር በፈላስፊት ኢትዮጵያ እና በህዝቧ #የውስጥ ጉዳይ መዋለ ዕድሜን ሙሉ እንደ እኔ የሸለመ ሰብዕና መኖርም አለና በስሱ ከመኖር ጋር ለመወያዬት፣ ለመነጋገር፣ ለመፈታተሽም በአደብ እራስን እና የመኖርን ፍላጎት ለማጣጣም #...