ልጥፎች

በእብለት ተበጥቶ!

ምስል
ማህበረ ናዳ በወናው ማሳ ቀርንቶ! „ቁጣዬ በእረኞች ላይ ነድዷአል፤ አውራ ፍዬሎችንም እቀታለሁ፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሄርም የይሁዳን ቤት ጎብኝቷል፤ በሰልፍም ውስጥ እንዳለ እንደ ክብሩ ፈረስ ያደርጋቸዋል።“ ትንቢተ ዘካርያስ ምዕራፍ ፲ ከቊጥር ፫ እስከ ፬ ከሥርጉተ© ሥላሴ 18.08.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።                          ምን አለው እና የብትክ ቀረርቶ ¡ የሰባራ ሰንጣራ የሞገድ ሠርግ ቀበቶ። የስርዝ ድልዝ ቋቶ በወናው ማሳ ቀርንቶ። የሥም እንካ ስላንትያ ድርጎ የወንፊት ግድፍት ብልጎ። የጡዘት እርቃን ተባዝቶ ዓመት እስከ ዓመት ተዋርጭቶ። ተፈራግጦ ሲነሳ ደንግጦ ተላልልጦ ተገምጦ አይዋ ልጦ! በደመምን ተውጦ በትካዜ ጎርብጦ ያ እፉኝት ሰላቢው ወረንጦ። በድጥ ማጥ ተፈናጦ በፈንጣጣ ተንጣጥቶ በምንም ቀርቶ! በጎርምጥ እባጭ ተሰልቆ መውጫያ ሲያጣ ተደብቆ በፍርስቱ ናዳ ለቆ። የእፉኝት ጢንዝዝ ተቋንጥቶ አለሁ ይላል ተዝካሩ ላይ ሞቶ። ይሄው ታዬ በእብለት ሙሽርነት ተበጥቶ የውርዴው ኪሳራ አቦካቶ በዬለም ተቦክቶ ታካቶ። ሰላም የማይሰጥ እንቶ ፈንቶ በግጭት ህውከት ተዳምቶ ቀበቶውማ መች መክቶ? ቀረ ፈሶ አንብቶ ... የእብለት ሳይበር ጎርንቶ። ·       ሥ ጦታ ለማህበረ ቅጥፈት። 19.04 ደቂቃ።      የኔዎቹ ኑሩልኝ።       ማለፊያ ጊዜ።

ቅርሻ!

ምስል
ቅርሻ! „አባቶቻችሁ ወዴት ናቸው? ነብያትስ ለዘላለም በሕይውት ይኖራሉን?“ ትንቢተ ዛካርያስ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፬ ከሥርጉተ©ሥላሴ 18.08.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ። የውሸት ቀዳዳ ዋሻ ሁልጊዜ በግምሻ የፖለቲካ ነጋዴው የዘመኑ የመዘላባድ ቅምሻ ምንግዜም እየሸቀጡ ለማምሻ የቀዳዳ ቅርሻ! ሁልጊዜ ማበሻ፤ የነዳላ አስሳ የጦስ ልምሻ! የተልባ ስፍር መስፈሪያው ፍርሻ አንዱን ሲያሸልክ ሲነፍስ ለመቆስቆሻ የወጀብ ስፍር የቀመኞች ድርሻ ያፍ ወለምታ የማይነጥፍ ዓመት ድገሙን መቆራቆሻ ቆሻሻ! የጭድ ክምር ድንኳን ጥቅርሻ የጎደሎ ቀን እጣ የፍስሽ አለሎ መዋቀሻ በሌለበት የአልሁ ባይ መደቆሻ። ያልተወለደ አንጀት የጭካኔ ማርከሻ፤ የዕብለት አንቱታዊ ማፈሰሻ የምናምንቴው አርቲ ቡርቲ ማሳሻ። የማያባራ የሞላጮች ትናጋ መቀየሻ ክምር የድርቆሽ የባዶ ሜዳው አያልቅ ጥቃሻ የለመደበት የናዳ ፍርሻ! ·       ሥ ጦታ ዘመን ተዘመን በውሸት ድርድር ለተከመሩ ገበርዲን እስተከራበቱ ይሁንልኝ። 18.20 ውሸታሞች የሚያልቁበትን ቀን ፈጣሪ ያምጣልን! አሜን ይሁንልን! ይደረግልን! የኔዎቹ ልባሞቹ ቅኖቹ ኑሩልኝ! ማለፊያ ጊዜ!

ነፃነት ለአብያዊ መንፈስ!

ምስል
ለአገር እንባ የነበርክ መፈወሻ ! ቅዱስ አባቴ ሆይ! የት ሄደ የብጹዕነተዎት አምላክ? ከቶ ከመንበሩ የለምን?!  "ልባችሁን በመንገዳችሁ ላይ አድርጉ"  ትቢተ ሐጌ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፭ ከሥርጉተ © ሥላሴ 18.08.2018  ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ነፍስ ሲጨንቃት ስለ አገር ስታነባ ማቆሚያ አጥቶ ሆዴ ሲባባ የነፃነት ልዩ አባባ ፍሬ አፍርቶ ከልብ ሲገባ ነፍስ ተገዘቶ ሁሉን አግባባ። ያ የነበረ ግን አሁን የሌለ የሰማይ ያህል የራቀን  ወስጣችን ገብቶ በሰናይ የነኘን እሱ ነበር ሥጦታ የመንፈስ ቅኔ ጌታ የመሆን አዝማራ የሁለመና ገበታ። ሳናስበው ብቅ ብሎ ነፍሳችን ገዝቶ ወጣ ገባውን አስማምቶ በህሊና ለምቶ ስለህሊና ለህሊና ቃል አስምቶ ቃል ገብቶ የውል አባት ያ ሁነኛ የዋቢነት ባላ የእኛ። የሁሉን ጓዳ ደባብሶ ለፍስሃ ተግቶ ጉድፍ ጠርጎ፤ ጎናጣውን ሊያቃና አቃንቶ ቅንነት ሊዋውል አስልቶ እድሜ ሙሉ ተሰናድቶ ነበር እሱማ ስለሁሉም ተግቶ። የለም አሁን ከቅርባችን ያ አውራው ንብ ደርባችን መንበራችን … እንደናፈቀነው እንደ አጓጓን እንደሳሳነው የባተለው፤ ያ ሳተና ብረቱ የሰጠን ለኛ ሳይሰት ስልቱ ጥሩነቱን ሳንጠግበው ሳንሰናበተው በክፉዎች ወጥመድ የተበላው ደጉ አብይ ከቶ የት ነው ያለው? ያ ቅን ደካሚ አገር አለኝ ብሎ ሲማስን ሲወድቅ ሲነሳ   እናቱን ከእንቅልፏ  ሊያስነሳ አያታክቴ አንደ ባከነ ላይወሳ ላይነሳ ነገ ቀድሞት እንዲህ ሊረሳ? እንዴትስ ይረሳ? ስለምንስ ይረሳ? ለእኛ የሆንክ የአብርሃም በግ አንተ ንጹህ የሆንክ ደግ። ያ ባተ...

"የምናወቀውን አብይ እንፈልጋለን" ከጸሐፊ መስፍን ማሞ።

ምስል
የምናውቀውን     አብይ እንፈልጋለን!                                                መስፍን ማሞ ተሰማ “ህልም በሥራ ብዛት ይታያል። እንዲሁም የሰነፍ ድምፅ በቃሉ ብዛት ይሰማል” “ብዙ ህልም ባለበት ዘንድ እንዲሁም ደግሞ ብዙ ቃል ባለበት ሥፍራ በዚያ ብዙ ከንቱ ነገር አለ።” መፅሀፈ መክብብ ምዕ 5 ቁጥር 3 እና 7 አስቀድሞ ቃል ተነገረ፤ ቃሉም የአብይ ነበረ፤ ቃሉም ኢትዮጵያዊነትን ከወደቀበት ማንሳት ነበረ፤ ቃሉም በእኛ ዘንድ ህያው ሆነ፤ እነሆ ኢትዮጵያዊነትን ከመሪዋ ጎን ቆመን ከፍ አደረግን፤ ከአፅናፍ አፅናፍ ሆ! ብለን ተነሳን፤ በያደባባዩ ተመምን፤ መሪያችንን አብይን እንደ ጨው በተበተንባት ምድር ሁሉ ስሙን ጠራን፤ እነሆ ኢትዮጵያ መሪዋን ሙሴን አገኘች ስንል ብሥራት ተናገርን፤ እርሱም አላሳፈረንም፤ ሙሴነቱን እጃችንን ይዞን አቅፎንና ስሞን እንባችንንም አብሶና ደሙንም ለግሶን አልቅሶና አንሰቅስቆን ከሰቆቃና ከግርፋት ከእስርና ከስደት ነፃ አውጥቶን ወደ ነገይቷ ኢትዮጵያ መንገድ በመደመር ጉዞ መጋቢት 24 ቀን 2010 አስጀምሮን እስከ ሐምሌ መገባደጃው ከጎናችን ለቅፅበት ሳይጠፋ፤ ስንጀግን እየተደሰተ፤ ስናጠፋ እየወቀሰ፤ ስናኮርፍ እየመከረ፤ ስንበድል ይቅር እያለ፤ ወደ ሁዋላ ስናፈገፍግ እያበረታን፤ ስንቃወመውም እያዳመጠን ማዕበ...

ፐ!

ምስል
የመርህ ሰው እንሁን። „በንጉሡ ውስጥ የነበረው ጃንደረባው ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ       ኤርምያስን በጉድጓዱ ውስጥ እንዳኖሩት ሰማ።“  ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፴ ቁጥር ፰፯ ከሥርጉተ© ሥላሴ 18.08.2018 ትናንት አንድ ዜና አደምጥኩኝ የአማራ ክልል መስተዳድር የኤርትራን መንግስት ፕሬዚዳንት ፕ/ ኢሳአስ አፈወርቂን ወደ ክልሉ እንደ ጋበዘ። ቀኑ አልታወቀም ግን ይሁንታ እንዳገኜ አዳምጫለሁኝ። https://www.satenaw.com/amharic/archives/62628 “ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ የሚመሩት የልዑካን ቡድን ወደ አማራ ብሔራዊ ክልል እንዲሚመጣ ተስማምተናል ” ንጉሱ ጥላሁን አላውቅም እኔ ይህን ያህል ከውጪ መንግሥታት ጋር ክልሎች ሥልጣን እንዳላቸው፤ ህጋቸውንም አለነብኩኝም። መቼም ይሄ ሥልጣን ከተሰጣቸው ለእኔ ሥርዓተ አልበኝነት ነው። ወይንም ኢትዮጵያ የምትባል ማዕካለዊ መንግሥት ያላት አገር አለመኖሯን የሚያውጅልን ነው። በመንፈስ እንዳልነበረች ባውቅም ይህን ያክል ግን ገሃድ የወጣ ጉድ ይኖራል ብዬ አላስብም።  እርግጥ ነው የአባይ ኬኛ ግንኙት የሰጠን ግብረ ምላሽ ነበር በዬክሎች የነበረው የተካተረ ግንኙት ከውጭ መንግሥት ጋር የሚመስል ነበር። ልክ አልባንያ፤ ከአዘርባጃን፤ አዘርበጃን ከቦስንያ፤ ቦስንያ ኮከራዚ ወዘተ ...  ይሄ የአሁን ደግሞ ግርም የሚያደርግ ነገር ነው። ፉክክር ነው ወይ የተያዘው ወይንስ አገር እዬተመራ ነው ያሰኛል ። ወይንስ የ አብይን ጥረት ማክስም እና ማክሰል? ነገሩን ሁሉ እኮ የልጆች ጨዋታ አድርገውት አረፉ። የውሃ ላይ ኩበት … አንዱን መሰረት ሳያስዙት በዬደረሱበት ጉብ እያሉ እራሳቸውንም ...

ነፃነት ለአብይ እና ለቤተሰቡ!

ምስል
ዛሬም ዝምታ ነፃነት ለዶር አብይ አህመድ! „ኤርምያሰ ወደ ጉድጓድ ቤት ወደ ጓዳዎቹ ገባ፤ ኤርምያስ በዚያ ቀን ከተቀመጠ በኋዋላ ንጉሡ ሴዴቅያስ ልክ አስመጣው፤ ንጉሡም በቤቱ፤ በውን ከእግዚአብሄር ዘንድ የሆነ ቃል አለን ብሎ በቆይታ ጠዬቀው።“  ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ  ፴፯ ከቁጥር ፲፮ እስከ ፲፯ ከሥርጉተ© ሥላሴ 18.08.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንዴት ናችሁ? አሁንም ድህረ ገፆችን ጎበኘሁኝ ምንም ነገር የለም ዝምታ ሰፍኖበታል፤ እንዲያውም ሌላ የማጠናከሪያ ጹሁፍ ባ ኢንግሊዘኛ አነበብኩኝ። በዝምታ እንድንዘልቅ ያን የሚያጠናከር ነው። አሁን አጀንዳችን ሊሆን የሚገባው ዶር አብይ አህመድ ሆነው ሳለ እኛ በአርቲ ቡርቲው ስንፋለጥ እንገኛለን። እርግጥ ዛሬ የተሻለ ህልም አይቻለሁኝ። ነገር ግን እኛም ከተኛን ቀጣይ ነው ጨለማው። የአሜሪካ ኢንባሲ  በኢትዮጵያ ቃላ አቀባይ የኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነት ሲገኝ የአጠቃቀሙ ሁኔታ ነበር የገለጸው፤ አቶ አህመድ ሽኔ ደግሞ ለውጡ ሊቀለበስ አይችልም የሚል መግለጫ ሰጥተዋል። ይህ ሁሉ አድበስብሶ ለማለፍ ነው። ዶር አብይ አህመድ እገታ ላይ ናቸው። እባካችሁ መላ ፈልጉ። እባካችሁን ለነፃናታቸው ታገሉ፤ እባካችሁ እንቅልፍ አንተኛ ኢትዮጵያ በታሪኳ ይህን መሰል ዕድል አግኝታ አታውቅም። በዚህ የሚከፉ፤ የሚጨነቁ፤ በዚህ የሚጠበቡ ቅኖች ናቸው።  ትናንትም ቅኖች ነን አብረን ከጎናቸው የቆምነው። ዛሬም ማድረግ ያለብን ይሄውን ነው። ቢያንስ ወያኔ ሃርነትን ያህል ጠላት አስቀምጠን ይህ ሁሉ ቀን ከሰው እንዳልተፈጠረ ያ ሩህሩህ ፍጡር እንዴት ዝም ይባላል? እባካችሁ እንድረስለት። ነፃነት ነፃነት ነፃነት ነፃነት ለዶር አብይ አ...