ልጥፎች

ኢትዮጵያዊነት ስክነት ነው።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ  ድልና ዲል። „ሳቅን እብድ ነህ፤ ደስታንም፤ --- ምን ታደርጋለህ? አልኩት።“ መጽሐፈ መክብብ ፪ ቁጥር ፪ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 17.04.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንዴት ናችሁ? ዛሬ ተዚህ ደመንመን ብሏለኝ።  ለነገሩ ሲዊዞች ሚያዚያ ወርን የፈለገውን የሚያደርግ እንደልቡ ነው  የሚሉት። ድልና ዲል። ዲልም ድልም። ድልም ዲልም። ባለፈው ዓመት ሁለቱንም ተንበርክኮ የዛቀው የትናንቱ ኦህዴድ የዛሬው ኦዴፓ ሌላ ድልና ዲል ያጋጥምው ወይንስ  ተስፋውን ይጋግጠው እንደሆን ብዬ አሰብኩኝ - ዛሬን ላስክነው ሳስብ ወይንም ስሻ። ከዚህ ቀደም አንድ ጊዜ ጥቅምት ወር በፈረንጆች  ኢ ትደፈር ይሆን ብዬ ጽፌ ነበር። https://sergute.blogspot.com/2018/10/blog-post_2.html የፈረደባት " ኢ " ትደፈር ይሆን ? 02.10.2018 ከዛ ደግሞ ድንገት ተነሰተው በአጭር ጊዜ እንዋሃዳለን ሲሉ የጤና?  ብዬም አንድ መጣጥፍ አቅርቤ ነበር። https://sergute.blogspot.com/2019/02/blog-post_33.html የኢዴፓ እጩነት / አዲስነት ትልሞሽ / 25.02.2018 መቼም ለጠ/ሚር አብይ አህመድ ሁሉ ነገር ቀላል ነው። ከራስ መተማመናቸው  የመነጨ ይመሰለኛል። ድርጅት የሰው መንፈስ ውህደት ስለመሆኑ እንዴት እንዳዩት አላውቅም። ብቻ እኔ ያን ጊዜ ያነሳሁት፤ በስፋትም የሄድኩበት ጉዳይ አሁን የሁሉም አጀንዳ የሆነ ይመስለኛል። ኦዴፓ ድሉን አስገኘሁት እኔ ብሎ አስረግጦ እዬነገረ ነው፤ ለሚመራው ህዝብ ...