ኩርፍርፍ።
እንኳን ደህና መጡልኝ ኩርፍርፍ። „ ሳቅን እብድ ነህ፤ ደስታንም፤ --- ምን ታደርጋለህ ? አልኩት። “ መጽሐፈ መክብብ ፪ ቁጥር ፪ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 27.04.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ · እ ፍታ። እንዴት ናችሁ የአገሬ ልጆች? ደህና ናችሁ ወይ? ለክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለባዕለ ስቅለት፤ ለቅዳምሱር ለትንሳኤ ዋዜማም አደረሳችሁ አደረሰን። ትናንት ስቅለት ነበር በህይወቴ የምውዳቸው ባዕላት የቅዱስ ዮሖንስ ዋዜማ በጎንደርኛ ምሽት እና የስቀለት በዓልን ነው። ጎንደር የተለያዬ ትውፊት አላት ስቅለትን ልጆች ሰብሰብ ብለው ሆምሻምሾ እየዘመሩ በዬቤቱ ዱቄት፤ ዘይት፤ ድልህ ይለምናሉ። ከዛ ከሙሴዋ ቤት ይቦካል፤ የተቦካው ጸሐይ ላይ ይቀመጣል ተነሳ አልተናሳ በዬሰዓቱ እዬሄድን እናዬዋለን። የሚገርማችሁ እጃቸው ቶሎ የሚያቦካም የሚባልላቸው ባለመክሊት አንስትም አሉ። የእኔ የእናቴ እናት ለዚህ ተፈላጊ ነበረች። እሷ ነው የምታቦካልን ለደብረብርሃን ልጆች … ሊጡ በቅጡ ሳይቦካ በለቱ ነው የሚጋገረው። የአንድ ቀን ሊጥ እንጀራ፤ ዓይኑ ቦግ ቦግ ያለው ማር ማር በሚለው እንጀራ ወጥ ተስርቶ በጋራ ይበላል። ትናንት ኤቢ አድበርታይዝመንት ቅምሻውን ልኮልን አይቻለሁኝ፤ በስንት ዓመቴ ማለት ነው። ሴቶችን ግን አላዬሁም። ለምን ማለቴ አልቀረም? ሴቶች የማይሳተፉበት የመስቀል ሆያ ሆዬን ምሽት ብቻ ነው። ያም ለወግ አጥባቂው የጎንደር ማህበረሰብ ሴቶችን በምሽት መፍቀድ ታሳቢ በማድረግ ይመስለ...