ልጥፎች

በፓርላማ ምርጫ ፕሬዚዳንታዊ???? መንግሥታዊ አደረጃጀትን ፓርቲያዊ ዲስፕሊን ውስጥ ተዘፈቀን?

  በፓርላማ ምርጫ ፕሬዚዳንታዊ????    እንዴት ሊሆን ይችላል?    መንግሥታዊ አደረጃጀትን ፓርቲያዊ ዲስፕሊን ውስጥ ተዘፈቀን?   በስምንተኛው አገራዊ ምርጫ በያንዳንዱ የምርጫ ጣቢያ አቶ ሀ፤ አቶ ለ፤ አቶ መ ሴት አይታሰብም ይወዳደሩ እና ያን ጊዜ ፕሬዚዳንታዊ መሆን ይቻላል። እንጂ አንድ እንፍራንዝ ከምትባል ትንሽዬ ከተማ የምርጫ ጣቢያ፤ ወይንም ዲክሲስ ከሚባል የምርጫ ጣቢያ የተመረጠ አቶ ሀ አቶ ለ አቶ መ የአገር ፕሬዚዳንት ልክ እንደ ዲሞክራት፤ ሪፓብሊካን ወይንም ኢንዲፔንደት ልሆን ብሎ ማሰብ ብዙ የገዘፋ የመንግሥት አደረጃጀት መርሆችን የሚሰባብር፤ የሚያቆሳስል፤ የሚገርፍ መከራ ይሆናል።   ብዙ ዝንባሌው የመጫን መንፈስ ከኖረው መንፈስ፤ አየር ይወጠራል። የተወጠረ አየር መተንፈሻ ቧንቧ ሲያጣ ይፈነዳል። አሁን ባለው ግሎባል ይሁን አህጉራዊ፤ አህጉራዊ ይሁን ብሄራዊ ትብትብ ችግር አብዝቶ ማስተዋልን፤ አብዝቶ አርቆ አሳቢነትን፤ አብዝቶ ብልህነትን እንጂ ብልጥነትን አይጠይቅም። ብልጥነት ለእኔ አጭበርባሪነት ነው። ማጭበርበር ከገብያ ሂደት ጋርም መራራ ነው እንኳንስ በመንግሥት አደረጃጀት።

"፭ #መቶወቹ።" #ትንሽዬ ዕይታ።

  "፭ #መቶወቹ ።"   "እግዚአብሄርም አለ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር።"    (ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፳፮)   የሰው ጉዳይ፤ የተፈጥሮ ጉዳይ የራስ #እንደራሴነት ጉዳይ ነው። ለእኔ። ሥጦታ የአጋይሥት ዓለሙ ሥላሴም ነውና።   "እግዚአብሄርም አለ፤ #ሰውን በመልካችን እና #ምሳሌያችን እንፍጠር።"   #ትንሽዬ ዕይታ።    እንዴት ነን? አንድ አገር ነው ያለን። አንድ ማዕድ ነው ያለን። አንድ እልፍኝ ነው ያለን። ስለሆነም #አግለን ይሁን #አቅርበን ልናየው የምንችል አመክንዮ ቢኖርም የእናት ጉዳይ ግን #አናት ነው። ልናደምጠው፤ ልንከታተለው፤ ሰሙን አልሰሙን ዕይታችን ማጋራቱ የቤታዊነት ልዕልና ጋር ያገናኛል እና ሁኔታውን መከታተሉ ይጠቅማል። የዜግነት #እኩሌታ ወይንም #እርቦ ይሁን #ሲሶ ስለለው።    #የኮሚሽኑ ዕለታዊ ማብራሪያ።   "አዳሪ አጀንዳወች ሊኖሩ ይችላሉ። ለቀጣዩ ትውልድ ም ሊሻገሩ የሚችሉ።" የሁለንም ኢትዮጵያዊ ዜጋ #ሰብሳቢ የሚያደርገው #በክብነት ውስጥ #ማዕዳዊ የማድረግ አቅም ያለው፤ እኛን ኢትዮጵውያንን ብቻ ሳይሆን #አፍሪካውያንንም እንዲሁም ሉላዊ የዲፕሎማት ፬ኛ ግሎባል መዲናይቱን፤ ባለቤት ወይንም #ተጠማኝ ሊያደርግ የሚችል የምክር ሃሳብ ሊሆን ይችል ይሆን #አዳሪ ይሁን ተገፍቶ በቀጠሮ ለቀጣይ #የትውልድ #ቀጣይ የቤት ሥራ ሊሆን የሚችለው?    ፊት ለፊት ተገናኝቶ መነጋገሩ መልካም ነው እንጂ፤ በጠቅላይ ሚኒስተሩ በኦሮምያ ያደረጉት ንግግር ተስፋው የገዘፈ ፈተና ሥራ ላይ እያለ ሳይቀር እንዳለበት ይገልፃል። በትርጉም ነው የሰማሁት። የነበረን ለማስቀጠል ድካሙ ይሁን ወ...

"የሰይጣን ጆሮ ይደፈን።" አሜን። "#እንጨራረሳለን።" አንባሳደር ባጫ ደበሌ በኬኒያ የፈላስፊት ኢትዮጵያ ባለሙሉ አንባሳደር (ጄኒራል)

  "የሰይጣን ጆሮ ይደፈን።" አሜን። " #እንጨራረሳለን ።" አንባሳደር ባጫ ደበሌ በኬኒያ የፈላስፊት ኢትዮጵያ ባለሙሉ አንባሳደር (ጄኒራል)   "ስለዚህም ነገር ፆምን፥ ወደ እግዚአብሔርም" ለመንን፤ እርሱም ተለመነን።" (መጽሐፈ ዕዝራ ምዕራፍ ፰ ቁጥር ፳፫)   ምዕራፍ ፲፱።   • https://www.youtube.com/watch?v=f4ydQf__UDA “ጦርነት ከተጀመረ መንግሥታት ይለወጣሉ፤ ድንበሮች ይቀየራሉ”| BBC News አማርኛ (በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ)   «ቢቢሲ በኢትዮጵያ እና በቀጣናዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ ጋር ቃለ መጠይቅ አድርጓል። የኢትዮጵያ አሁናዊ ሁኔታ፣ ከህወሓት ጋር ያለው ውዝግብ፣ የባሕር በር ጥያቄ እና የቀጠናዊ የጦርነት ስጋቶች በቃለ መጠይቁ ተዳሰዋል።»   #ዕፍታ ።   ደንግጬ ነው ያዳመጥኩት። በሚሊተሪ፤ በባንክ፤ በመንበረ - መንግሥት፤ በአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካ እጅግ ቁጥብ ነኝ። በሰባዕዊ መብት ጉዳይ፤ ወይንም በፖለቲካ ፓርቲ አደረጃጀት እና አመራር ነው ገፋ ያለ ጊዜየን የምመግበው።    " #እንጨራረሳለን ።" አንባሳደር ባጫ ደበሌ (ጄኒራል።)   ማነው ጨራሹ?   ማንስ ይሆን ተጨራሹ? እጅግ አስጨናቂ አገላለጽ ነው። "የሚጨራረሰው" የሰው ልጅ ነው። ኢትዮጵያዊው ሰው። ሰሞኑን ብልፄው የግሪን ሌጋሲውን ሂደት የመራበት ሞቶ "ተስፋን #እንትከል ነው።" ለሞቶ #ቅሸራ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ A+ ናቸው።    ሳይንስ እና ቴክኖሎጂም ሚኒስተር በነበሩበት ጊዜም "ከእርምጃ ወደ ሩጫ" የሚል ሞቶ እና ኮንፍረንስ ነበራቸው። ለትውልድ የሚሆን ቋሚ የሥራ ባህል ...

#ኑ #አብረን #እንፈር! በምን ቀመር? በምን ሁነት ህወሃትን ሞሽሩልን፤

  #ኑ #አብረን #እንፈር !   "ልጄ ሆይ! በክፋ ሰወች አትቅና፤ ከእነርሱ ጋርም መሆንን አትውደድ፤ ልባቸው ግፍን ታስባለችና፤ ከንፈራቸውም ሽንገላን ትናገራለችና።"   (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳፬ ቁጥር ከ፩ - ፪።)   #ምዕራፍ ፲፱።   እማይሰማ የለም። እግዚኦ ነው። የማይደመጥም የለም።  ከዚህ ምጣት አድነን ነው።    ግፍን ማድመጥ ልዩ አቅል ይጠይቃል። ጥቃት ሲታከልበት #መቆም ይፈተናል። ጭካኔን ተቀበሉ የሚል ግዳጅ ሲመጣም ልዩ #የግድያ ፍርድ ነው።    በምን ቀመር? በምን ሁነት ህወሃትን ሞሽሩልን፤ ከህወሃት ጋር ያለንን የግጥግጥ መርኃ ግብራችን አድምቁልን እንደሚባልም አይገባኝም። እንዲገባኝም #አልፈቅድም ። ሲኦል እንዴት-------- ይናፈቃል? መቃብር እንደምን ሽው ---------ይላል? ገደላ ገደል እንደምን ---------ለምርጫ ይቀርባል? አፋፍ ስለምን ----------ትዝ ይላል? #ህወሃትቤርሙዳ ትርያንግልን ነው። እና እንዴት ቤርሙዳ ትርያንግልን አፍቅሩልኝ እንደምን ይባላል? "ያልደረሰበት ግልግል ያውቃል ይላል" የጎንደር ባለ ቅኔ። ይህም ሆኖ #ከ40 ሚሊዮን በላይ የሆነ ህዝብን እንደምን በህወሃት ሥር ተነጠፋ፤ ተጎዝጎዙ፤ ስገዱለት --- አደግድጉለት እንደምን ይባላል? ያ ትላልቅ ከአንገት ላይ የታሠረው መስቀሉ የት ገባ? ማተቡ የት ደረሰ? የቅኑ የአማራ ህዝብ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ተጋድሎ፤ የዛ ገራገር ህዝብ በየዘመኑ ለካቴና መዳረግ፤ የዛ ሰው አማኝ የአማራ ህዝብ እንደ ወጣ መቅረት፤ የዛ ፈርኃ // እግዚአብሄር እና አላህ ያለው ህዝብ #ቅኔወች መሰወር፤ መታገት፤ ከፖለቲካ መገለል መገደልም እንደምን ለህውሃት በስጦታ ይቀርባል? እስር ቤት ያሉት ስ...

#የአዋሳ #ጉዳይስ #ጊዜ #ጠብቆ #አይፈነዳምን?

  #የአዋሳ #ጉዳይስ #ጊዜ #ጠብቆ #አይፈነዳምን ?   ለዕውነት #ወጌሻም ይሁን #ጋራጅ አያስፈልገውም።   "ልጄ ሆይ! ልብህን ስጠኝ ዓይኖችህም መንገዴን ይውደዱ።"   (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳፰ ቁጥር ፳፮።)   #ምዕራፍ ፲፱።   ሲዳማን በሚመለከት ስንት ህዝብ ተሰደደ? ስንት ሰብዕስ በባዶ ስድስት ጆኖሳይድ ተፈጸመበት?   ስንት የብሄረሰቡ አባላት ለእስር ለእግር ብረት ለአካል ጉድለት ተዳረጉ? የትኛው የሲዳማ ድርጅት ፊት ለፊት ወጥቶ በአደባባይ ጨቋኙን ሞገተ፤ በቋያው ተረገበገበ?   የሲዳማ ነፃ አውጪ የሚባል የጨመተ ኮሽታ የማያሰማ ድርጅት ከግንቦት 7 አገራዊ ንቅናቄ ጋር አብሮ እንደነበር አውቃለሁኝ። ህወሃትን መንበሩን ነቅንቆ፤ አጣድፎ፤ ዱብ ዕዳን ይፈቅድ ዘንድ ያደረገው ግን ገድለኛው #የሰቆቃው ወልቃይት ብረሳሽ ግሎባል ንቅናቄ ነበር። እራሱ ህወሃት ተደናግጦ ጎንደር ላይ ሙሉ አካሉን ይዞ ጉባኤም አካሂዶ ነበር።    አዲስ አበባም አቶ በረከት ስሞዖን እና ሌላ ፖለቲከኛ የሰበሰቡት ጉባኤም ተካሂዶ ነበር። ያሳካው ነገር ባይኖርም። "ኢትዮጵያ ሱሴ፤ ጣና ኬኛ" ሲመጣም #ጉዝጓዝ የሆነው ያ ቅን የአማራ ህዝብ ነበር። በውጭም በአገር ውስጥም። ዛሬ እጅግ የተንጠራሩ፤ ውጥርጥር ያሉ ጥያቄወች ከኦህዲድ ብልጽግና ሳደምጥ ይገርመኛል። የመታበይ መጨረሻ ምን እንደ ሆነ ባላውቅም።   ለነገሩ በአማራ ህዝብ ሙሉ #ይሁንታ የተገኜ ዕድል ተጠቃሚው 50+ ደቡብ ነው። ካቢኔውም ሆነ የጠቅላዩ ቢሮም በዚህው ልክ። #ሃራም አማራ ያለ ነው። የአማራ ህዝብ እጁ አመድ አፋሽ ነው። ፈጣሪ አላህ በቃ ይበለው አሜን።    " #አዬ ጅቦ ጅቦ ሳታመኃኝ ብላኝ።"...