የፃድቃኔ ማርያም #ሰማዕታት።
የፃድቃኔ ማርያም #ሰማዕታት።
ከእህት ሮዛ ሰለሞን ፔጅ የተገኜ #ደራሽ ዜና።
"አቤቱ የተቀደስህ አምላኬ ሆይ!
አንተ ከዘላዓለም ጀምሮ አልነበርህምን?"
ፈጣሪ አምላክ ምህረቱን ይላክ። በጠቅላላ ሁለመናችን #መረጋጋት ተስኖታል። እኛ ቢያንስ ውስጣችን #ንጹህ እናድርግ። #እግዚአብሄር #እየተናገረ ነው። መሬት መንሸራተቱም #ይናገራል፤ #ያናግራል። አድማጭ ከተገኜ።
የሆነ ሆኖ ለሰማዕታት ነፍስ ይማር የተገባ አይመስለኝም። ለቅኒት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ግን #መጽናናትን እመኛለሁኝ።።
ሥርጉትሻ 03/08/026
የሃዘን ዳርቻ ያድርግልን አምላካችን። አሜን።
*********////*************
"የጻድቃኔ ቅድስት ማርያም ገዳም ዋሻ በመንሸራተቱ ከ10 በላይ ምዕመናን ሕይወታቸው አለፈ፤
(ሐምሌ 27/11/2018) የደብረ ምጥማቅ ጻድቃኔ ማርያም ገዳም ሚዲያ
በጻድቃኔ ቅድስት ማርያም ገዳም ላይ በደረሰ ድንገተኛ የዋሻ መደርመስ አደጋ ዛሬ በከፍተኛ ሀዘን ላይ እንገኛለን። ገዳሙ ከእድሜው ብዛት የተነሳ ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን አስቀድሞ በመረዳት እና ለዕድሳት በመዘጋጀት ላይ በነበረበት ወቅት፣ በቀን 27/11/2018 ዓ.ም በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ከቤተመቅደሱ አጠገብ የሚገኘው የሰላም ለኪ ዋሻ የመደርመስ አደጋ ደርሶበታል።
በመቶ ለሚቆጠሩ አመታት ሲያገለግል የነበረው የምህላ ማድረሻ ዋሻ በድንገት በተከሰተ መሸርሸር ከ10 በላይ የሚሆኑ ንጹሐን ምዕመናን ሕይወታቸው ሊያርፍ ችሏል። በበርካታ ሰዎች ላይም የአካል ጉዳት ደርሷል ።
ይህ ድንገተኛ አደጋ ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን፣ ለአካባቢው ማኅበረሰብ፣ ለገዳማችን አባቶች እንዲሁም ለተወዳጅ ምእመናን ቤተሰቦች እጅግ ልብ ሰባሪና ታላቅ የሀዘን ጊዜ ነው።
"እግዚአብሔር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው፥ መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል"
(መዝሙር 34፥18)
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ