በፓርላማ ምርጫ ፕሬዚዳንታዊ???? መንግሥታዊ አደረጃጀትን ፓርቲያዊ ዲስፕሊን ውስጥ ተዘፈቀን?

 

በፓርላማ ምርጫ ፕሬዚዳንታዊ???? 
 
እንዴት ሊሆን ይችላል? 
 
መንግሥታዊ አደረጃጀትን ፓርቲያዊ ዲስፕሊን ውስጥ ተዘፈቀን?
 
በስምንተኛው አገራዊ ምርጫ በያንዳንዱ የምርጫ ጣቢያ አቶ ሀ፤ አቶ ለ፤ አቶ መ ሴት አይታሰብም ይወዳደሩ እና ያን ጊዜ ፕሬዚዳንታዊ መሆን ይቻላል። እንጂ አንድ እንፍራንዝ ከምትባል ትንሽዬ ከተማ የምርጫ ጣቢያ፤ ወይንም ዲክሲስ ከሚባል የምርጫ ጣቢያ የተመረጠ አቶ ሀ አቶ ለ አቶ መ የአገር ፕሬዚዳንት ልክ እንደ ዲሞክራት፤ ሪፓብሊካን ወይንም ኢንዲፔንደት ልሆን ብሎ ማሰብ ብዙ የገዘፋ የመንግሥት አደረጃጀት መርሆችን የሚሰባብር፤ የሚያቆሳስል፤ የሚገርፍ መከራ ይሆናል።
 
ብዙ ዝንባሌው የመጫን መንፈስ ከኖረው መንፈስ፤ አየር ይወጠራል። የተወጠረ አየር መተንፈሻ ቧንቧ ሲያጣ ይፈነዳል። አሁን ባለው ግሎባል ይሁን አህጉራዊ፤ አህጉራዊ ይሁን ብሄራዊ ትብትብ ችግር አብዝቶ ማስተዋልን፤ አብዝቶ አርቆ አሳቢነትን፤ አብዝቶ ብልህነትን እንጂ ብልጥነትን አይጠይቅም። ብልጥነት ለእኔ አጭበርባሪነት ነው። ማጭበርበር ከገብያ ሂደት ጋርም መራራ ነው እንኳንስ በመንግሥት አደረጃጀት።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።