#ኑ #አብረን #እንፈር! በምን ቀመር? በምን ሁነት ህወሃትን ሞሽሩልን፤

 

"ልጄ ሆይ! በክፋ ሰወች አትቅና፤
ከእነርሱ ጋርም መሆንን አትውደድ፤
ልባቸው ግፍን ታስባለችና፤
ከንፈራቸውም ሽንገላን ትናገራለችና።"
 
(መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳፬ ቁጥር ከ፩ - ፪።)
 
#ምዕራፍ ፲፱።
 
እማይሰማ የለም። እግዚኦ ነው።
የማይደመጥም የለም። 
ከዚህ ምጣት አድነን ነው። 
 
ግፍን ማድመጥ ልዩ አቅል ይጠይቃል። ጥቃት ሲታከልበት #መቆም ይፈተናል።
ጭካኔን ተቀበሉ የሚል ግዳጅ ሲመጣም ልዩ #የግድያ ፍርድ ነው። 
 
በምን ቀመር?
በምን ሁነት ህወሃትን ሞሽሩልን፤ ከህወሃት ጋር ያለንን የግጥግጥ መርኃ ግብራችን አድምቁልን እንደሚባልም አይገባኝም። እንዲገባኝም #አልፈቅድም
ሲኦል እንዴት-------- ይናፈቃል?
መቃብር እንደምን ሽው ---------ይላል?
ገደላ ገደል እንደምን ---------ለምርጫ ይቀርባል?
አፋፍ ስለምን ----------ትዝ ይላል?
#ህወሃትቤርሙዳ ትርያንግልን ነው። እና እንዴት ቤርሙዳ ትርያንግልን አፍቅሩልኝ እንደምን ይባላል?
"ያልደረሰበት ግልግል ያውቃል ይላል" የጎንደር ባለ ቅኔ።
ይህም ሆኖ #ከ40 ሚሊዮን በላይ የሆነ ህዝብን እንደምን በህወሃት ሥር ተነጠፋ፤ ተጎዝጎዙ፤ ስገዱለት --- አደግድጉለት እንደምን ይባላል? ያ ትላልቅ ከአንገት ላይ የታሠረው መስቀሉ የት ገባ? ማተቡ የት ደረሰ?
የቅኑ የአማራ ህዝብ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ተጋድሎ፤ የዛ ገራገር ህዝብ በየዘመኑ ለካቴና መዳረግ፤ የዛ ሰው አማኝ የአማራ ህዝብ እንደ ወጣ መቅረት፤ የዛ ፈርኃ // እግዚአብሄር እና አላህ ያለው ህዝብ #ቅኔወች መሰወር፤ መታገት፤ ከፖለቲካ መገለል መገደልም እንደምን ለህውሃት በስጦታ ይቀርባል? እስር ቤት ያሉት ስለ ህወሃት ፈቃድ መሻት ሲሉ ነውን ካቴና ላይ ያሉትን? የእነሱን አደራ ማውጣት እንደምን ያቅታል????
ለዛውም መሮኛል ያለ እንድ እራሱን ለነፃነት ሲል ስቃይን ለመቀበል የፈቀደ፤ ዱር ቤቴም ያለም፤ ወንድም እና እህቶቹ ከፊቱ ንጥል እያሉ ሰማዕትነትን እየተቀበሉ ሲያልፋ በአካል አብሮ ሆኖ ያዬ ያን ሰማዕትነት #ድፍት አድርጎ፤ እንደ ገና እራሱን፤ ነፃነቱን፤ መሻቱን፤ ዓላማ እና ግቡን በህውሃት ሥር ለማድረግ እንደምን ሊፈቅድ ቻለ?????? #ኑ አብረን እናፈር።
እሱስ ይገዛ፤ እሱስ በአንድ የህወሃት አክቲቢስት ሥር ይውደቅ ሚሊዮኖች ይህን ጥቃት እንዴት ሊቀበሉት ይችላሉ ተብሎ ታሰበ? እንዴት? ኧረ እንዴት? እኮ እንዴት? አ ት ቡ ----- ት!
በህወሃት አክቲቢስት ሥር የፋኖ አቅም? የፋኖ ትንፋሽ ፈቃድ እንደገና ያን ሁሉ የከራ፤ ያን ሁሉ ስቃይ ካሳየው መንጦላይት ሥር #ለመጠቅጠቅ እንደምን ታሰበ? #አንደበትህ፤ መላ አካልህ መንፈስህም ከእኔ ቁጥጥር ሥር ነህ ሲባል የአማራ ህዝብ #ነገ ተቀብሯል ማለት ነው።
በዛ ጨካይ ሥርዓት ውስጥ አሳሩን ሲይ የኖረ ህዝብ ስንቅ፤ ትጥቅ መጠለያ የሆነው ለድርብርብ ባርነት፤ ለንብርብር የጭካኔ ጥንስስ ነውን? አብራ ቅድስት ቤተ- ክርስትያናችን፤ ቅዱሳን ገዳማት፤ የአብነት ተማሪወች፤ ንውዬ ቅድሳት #የሚከስሉት ለዳግም የህወሃት ሎሌነት ነውን? አበስኩ ገበርኩ? #ኑ ------ አብረን እንፈር።
ለነፃነት ዱር ቤቴ ያለ አርበኛ በአንድ ቀንጣ የህውሃት መንፈስ ሥር ለመማቀቅ እንዴት ተወሰነ? እንዴት? ኧረ እንዴት? ህወሃት እንደ አሻው ይጠቀጥቀው ዘንድ የአማራን #ተስፋ እንደምን ብሎ ከዚህ ውሳኔ ተደረሰ?
ያ ----- አቅም፤
ያ ----ብርታት፤
ያ ሙሉዑነት በቃ እንዲህ እና እንዲያ ……… አብረን በትግሉ ለቆዬን ሰወች ቀራንዮ እንደታወጀብን አስባለሁኝ። ደክመናል። ለፍተናል። እንደ እናንተ ጫካ ባንገባም ከእናንተ በቀደመ፤ በተደራጄ ብልህነት ስንታገል ቆይተናል። ስልታችን ነው የሚለያዬው። ሲነሪትም አለን። በህዝብ ጥያቄ ላይ ውሳኔ የጥቂቶች ሊሆን አይችልም። ቢሞከር #ይፈሳል
ይህ ሁሉ ያልተገደበ ማገዶነት ለህወሃት ---- ሎሌነት? ለህወሃት ---- ባርነት? #ኑ አብረን እንፈር?
ወሳኝ ጥያቄ ይነሳል። ይህን አውቃለሁኝ። ሃሳቡ ሲጠነሰሰ ነበር የዛሬው ጥያቄ መልስ ሰጥቶ መነሳት የነበረበት። መጀመሪያውኑ ብቻችን እንችላለን ወይ? ብቻችን መወጣት ካልቻልን የስትራቴጂ እና የታክቲክ አጋራችን ማን ሊሆን ይችላል? ምን ሰጥተን ምን እናተርፋለን በአደብ መመርመር የነበረበት ከመነሻው ነበር።
ለዚህም ነበር በጥዋቱ እኔ አበክሬ የፃፍኩት። መስዋዕትነት የሚቀንስ የትግል መስመር መምረጡ የተገባ ነበር። ያ ባይሆንም እራስን ችሎ መቆም፤ የማይደፈር አቅምን አጠንክሮ ማውጣት ይገባ ነበር። እንዲህ ከዛ ጨካኝ ሥርዓት ጋር በእኩልነት ሳይሆን #በበታችነት ለመስራት ሲታሰብ ጥቃቱን መሸከም በፍጹም አይቻልም።
እራሱ የህወሃት ላዕላይ እና ታህታይ መዋቅሩ እኮ መሠረቱ #ጸረ - አማራ ነው። አጥፋኝ --- ግደለኝ --- ዝረፈኝ --- ሰውረኝ ብሎ ፈቃድ አለ ወይ????? ውስጥን ገልጦ እንዳሻህ #ፈረሽበት ከጠላት ጋር ትርፋ #ጢስ ነው። ያ ሁሉ ልፋት እና ድካም ጨካኝን ሞሻሽሮ ለማቅረብ? መሃከነ።
ያ ሁሉ ወጣት ከትምህርት ገበታ የወጣበት፤ ያ ሁሉ በአማራ መንፈስ ብክንክን ያለበት? በየዓውዱ የሚያልቀው ህዝብ እና የሚወድየው ተቋም፤ ያ ሁሉ ሰማዕትነት እንዲህ ባለቤት አልባ??? ኦ! አምላኬ።
ህወሃት የመራው ማንኛውም ወታደራዊ ተግባር ብቅ ያላችሁትን የአማራ ሊቃናት እያደነ ማሰናበት ይሆናል። ይህንንም እሰቡት። ዘላቂ የአማራን ህዝብ ድል በትጥቃችን ትርሲቱን እናስገኝለታለን ያላችሁትን ትታችሁ ከእንግዲህ ለራሳችሁ #ህይወት እሰቡ። አሳሳቢው ነገር እሱ ነው።
ትግል አብሮ መነሳት ካልተቻለ በተጨማሪነት ከሆነ ይህን መሰል ክፍተት የግድ ነው። አብሮ ተኮትኩቶ ያደገ መንፈስ አይበገሬ የመሆን አቅም አለው። የትግሉን መንፈስ ተመግቦ ስለሚያድግ።
የማከብራችሁ የአገሬ ልጆች ነገ ነሃሴ አንድ ነው። የአማራ ልጆች በገፍ የተገበሩበት ሰማዕቱን ታስቡ ዘንድ በትህትና እጠይቃለሁ። ለተዋህዶ ልጆች መልካም የሱባኤ ጊዜ።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
07/08/026.
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።