#የአዋሳ #ጉዳይስ #ጊዜ #ጠብቆ #አይፈነዳምን?
"ልጄ ሆይ! ልብህን ስጠኝ
ዓይኖችህም መንገዴን ይውደዱ።"
(መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳፰ ቁጥር ፳፮።)
#ምዕራፍ ፲፱።
ሲዳማን በሚመለከት ስንት ህዝብ ተሰደደ?
ስንት ሰብዕስ በባዶ ስድስት ጆኖሳይድ ተፈጸመበት?
ስንት የብሄረሰቡ አባላት ለእስር ለእግር ብረት ለአካል ጉድለት ተዳረጉ?
የትኛው የሲዳማ ድርጅት ፊት ለፊት ወጥቶ በአደባባይ ጨቋኙን ሞገተ፤ በቋያው ተረገበገበ?
የሲዳማ ነፃ አውጪ የሚባል የጨመተ ኮሽታ የማያሰማ ድርጅት ከግንቦት 7 አገራዊ ንቅናቄ ጋር አብሮ እንደነበር አውቃለሁኝ። ህወሃትን መንበሩን ነቅንቆ፤ አጣድፎ፤ ዱብ ዕዳን ይፈቅድ ዘንድ ያደረገው ግን ገድለኛው #የሰቆቃው ወልቃይት ብረሳሽ ግሎባል ንቅናቄ ነበር። እራሱ ህወሃት ተደናግጦ ጎንደር ላይ ሙሉ አካሉን ይዞ ጉባኤም አካሂዶ ነበር።
አዲስ አበባም አቶ በረከት ስሞዖን እና ሌላ ፖለቲከኛ የሰበሰቡት ጉባኤም ተካሂዶ ነበር። ያሳካው ነገር ባይኖርም። "ኢትዮጵያ ሱሴ፤ ጣና ኬኛ" ሲመጣም #ጉዝጓዝ የሆነው ያ ቅን የአማራ ህዝብ ነበር። በውጭም በአገር ውስጥም። ዛሬ እጅግ የተንጠራሩ፤ ውጥርጥር ያሉ ጥያቄወች ከኦህዲድ ብልጽግና ሳደምጥ ይገርመኛል። የመታበይ መጨረሻ ምን እንደ ሆነ ባላውቅም።
ለነገሩ በአማራ ህዝብ ሙሉ #ይሁንታ የተገኜ ዕድል ተጠቃሚው 50+ ደቡብ ነው። ካቢኔውም ሆነ የጠቅላዩ ቢሮም በዚህው ልክ። #ሃራም አማራ ያለ ነው። የአማራ ህዝብ እጁ አመድ አፋሽ ነው። ፈጣሪ አላህ በቃ ይበለው አሜን።
"#አዬ ጅቦ ጅቦ ሳታመኃኝ ብላኝ።"
"የወልቃይት ጉዳይ ጊዜ ጠብቆ የሚፈነዳ ፈንጅ ነው።" አያ ጅቦ ጅቦ ሳታመኃኝ ብላኝ። ሌላው "እናንተ ናችሁ እንጂ የአማራ ልጆች ፈቅደውልናል" ተብለናል ብለዋል ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ። እንኳን ደስ አለወት። ስላተረፋበት።
መልሱን ያዘገዩት ፍሬ ነገሩ ከውስጠወት ነገረ አማራ #የተገለለ ስለሆነ ብቻ ነው። እርስወን ማን ወደ ስልጣን አመጣ እና ነው ያን ስንት መስዋዕትነት የተከፈለለት ትግል እንዲህ #ግዞት የላኩት? በበጀት ቀጡት። ሁለት ጊዜ በፓርላማ ውክልናም #አስገለሉት።
አካባቢው በኦሮምያ ወሰንተኛ ቢሆን ኖሮ እስከ አሁን በስንት የሙሽርነት ድባብ #ይፍነሸነሽ ነበር። ሲዳማ እኮ ገፍታችሁ ነው ክልል ያደረጋችሁት።
በቀጣይም ደቡብ የሚለው ማንነትን ፍርስርሱን አውጣችሁት። አቅሙን የደቡብን አከሳችሁት። ደቡብን የነበረውን የላዕላይነት ሁነት በፌድሬሽን ምክርቤት ያለውን የድምጽ አቅም #ብትንትኑን አውጥታቸሁ ዕድሉን እናንተው እራሳችሁ የወሰዳችሁት።
ከበሻሻ በስተቀር ለእርስወ ክብር ፈቃድ ያለው የወልቀይት ጠገዴ፤ ጠለምት፤ አዳርቃይ፤ ማይጠምሪ፤ አዲረመጥ ህዝብ የለም። የፓርላማ ውክልና አልቦሽ ይሆን ዘንድ ሲኔሪቲ ያለው የወልቃይት ጠገዴ የማንነት #አስመላሽ ኮሜት እያላ /// ሥምረት ፓርቲ ትናንት የተፈጠረ ተደማጭ ሆነ። ይህ ግፍ አንድ ቀን መልስ ይኖረዋል።
ቀጣዩ የህዝብ ድምጽ የምትሉት "ከነፃነት እና ባርነት" የሚል አሁን አዲስ አበባን እንዳደረጋችሁት፤ የምርጫ ሃሳብ ይዛችሁ #ትጠቀልሉታላችሁ። እንደ ኦሮሞ ፖለቲካ #ይሉኝታ የለሽ አይቼ አላውቅም።
ያ ሁሉ ሰማዕትነት፤ ያ ሁሉ መስዋዕትነት፤ ያ ሁሉ እንግልት፤ ያ ሁሉ እስር እና ድብደባ፤ ያ ሁሉ ስደት ለዚህ ነበርን? እንዲህ ለመገፋት፤ እንዲህ #አናውቃችሁም ለመባል፤ እንዲህ ለመገለል? እንዲህም ለመጣል???
ለነገሩ ለእርስወ ማን እንደሚቀርበወት ይታወቃል። የወልቃይት ጠገዴን የማንነት አስመላሽ ኮሜቴ #አንድ ቀን በአካል አግኝተው ለማነጋገር ፈቃደኛ አይደሉም። ጨርሶም ዓይናቸውን ማዬት አይፈልጉም። ዕውነቱ ይህ ነው።
ይህ በሚሊዮኖች ሞራል ጢባጢቦሽ ጨዋታ ጠቃሚ ከሆነ ይቀጥሉበት። ሰውማ ምን አቅም አለው። ፍርድ እና ዳኝነቱን ፈጣሪ ይስጥበት። እንደገና ማይካድራ፤ እንደ ገና ጭና ይደገም ዘንድ ነው ይህ ሁሉ ዘገምተኛ ትብስብስ ሂደት ተቀርፆ የቅጣት ዶፍ እየወረደበት ያለ ህዝብ። እፎይታው እንዲርቅ፤ የተረጋጋ ህይወት እንዳይኖር፤ #ድንገጣ ኑሮው እንዲሆን ተፈረደበት።
በአማራ የውስጥ ሳቅ፤
የአማራ ንጹህ ፍስሃ፤
የአማራ ሰናይ ብልፄው ሆነ ፕሬዚዳንቱ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ይሹታል ብዬ አላምንም። እንጂማ ለዚህ ሁሉ ክብር እና ልዕልና ህልም ለሚመስል ሂደት ያበቃው ቁልፍ የተጋድሎ ምዕራፍ በዚህ መልክ ተልፈስፍሶ #መፈራረጃ ይሆናል ብሎ ማን አስቦ?
ለነገሩ ሁላችነንም ይበለን። በሙሉ አቅም አንድም ሰው አንዲት ብጣቂ አቅም ማዋጣት በማይፈልግበት ጊዜ ተማግደን ነበር ከእርስወ ጎን ሆነን የተሟገትነው፤ የተፋለምነው። መጨረሻው እንዲህ #ከርቤ ሊሆን።
የደገፈ በቀና - ያቃና፤ ጎደሎን ያሟላ፤ መከፋትን #የጠገነ ከፊት ሆኖ በቅንነት ሁሉን የሰጠ ገራገር የአማራ ህዝብ መፍትሄው ከሰው ሳይሆን፤ ከፈጣሪ ስለሆነ ከእሱ ጋር ቢመክር ቢዘክር ይሻለዋል። የሰውኛው ጉድ እማ ታዬ። ተመዘነ። ተወደቀ።
የወልቃይት ጠገዴ የሰቲት የአዲረመጥ የአዳርቃይ የማይጠምሪ ጉዳይ የማንነት ጉዳይ ነው። የሰባዕዊነት ጉዳይ። የሞራል ጉዳይ ነው። የትንፊሽ ጉዳይ ነው እንጂ የቦሊቦል፤ የቅርጫት ኳስ ወይንም የከረንቡላ ጨዋታ አይደለም። አልነበረም።
#እርጋ።
"የወልቃይት ብረሳሽ ቀኜ ትርሳሽ።" በዘመነ አብይዝም ይህ ጥያቄ በአማራ ክንድ ብቻ እንደ ቆዬ አንድ ቃለ ምልልስ አዳምጫለሁኝ። የሚረሳ የማይደፈር #ሃቅ አለ። ይህም የኢትዮጵያ መከላከያ በሙሉ አቅሙ፤ ሙሉ ድጋፍ እያደረገለት፤ የተገበረበትም ነው። ይህ ዕውነት ሊደፈር እንጂ ሊሸሽ አይገባም።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ክብረቶቼ ኑሩልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
06/08/926.
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ለእውነት ወጌሻም ይሁን ጋራጅ አያስፈልግም።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ