#መቼ ይሆን - #የሰላም #መቼቱ #በጦቢት?
"ሃሌ ሉያ።
እግዚአብሄርን የሚፈራ፥
ትዕዛዙንም እጅግ የሚወድ
ሰው ምስጉን ነው።"
(መዝሙር ፻፲፩ ቁጥር ፩)
በነጋ ጠባ ጥቁር ዜና፤ በየለቱ መርዶ፤ በየማዕልቱ ዕንባ መፈጠርን ተፃሮ በቆመ
ክፋ ሃሳብ የአንድ እትብት ልጆች እንዲህ መሆን ያሳዝናል።
ማህበረ ሰብአዊነት እንዴት አደራችሁልኝ።
ሥርጉትሻ 13/08/026.
«በመተከል ዞን ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን እና መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ»
12 ነሐሴ 2026
የንባብ ጊዜ: 3 ደቂቃ
«በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን እና መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ።
ጥቃቱ የተፈፀመው ትናንት ማክሰኞ ነሐሴ 6/ 2018 ዓ. ም. ጠዋት 12 ሰዓት ላይ በዞኑ ዋና ከተማ ግልገል በለስ በሚገኙ ቤተ ክርስቲያናት እና መናኸሪያ ላይ መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የአካባቢው ነዋሪ "ሕይወቱ ያለፈም፣ ከባድም ቀላልም ጉዳት የደረሰበትም ሰው አለ" ያሉ አንድ ነዋሪ "11 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን" እንደሰሙ ጠቅሰዋል።
የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥር "በትክክል አለመታወቁንም" ተናግረዋል።
"በገብርኤል እና በማሪያም እበያተ ክርስቲያን፣ በመስቀል አደባባይ ላይም ሞርታር መሣሪያ ተጥሎ" በሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን ነዋሪው ተናግረዋል።
ወደ ከተማው በእግር የገቡ "አሸባሪዎች" ያሏቸው ታጣቂዎች በአድማ በታኝ እና በመከላከያ ኃይል "መመለስ መቻሉን" ተናግረዋል።
የመተከል ዞን አስተዳደር በፌስቡክ ገፁ ባወጣው መግለጫ አጥቂዎቹ "የጉሙዝ ታጣቂዎች እና የፋኖ ኃይሎች" መሆናቸውን ጠቁሞ ጥቃቱ ግን "መክሸፉን" ገልጿል።
ዞኑ፤ ታጣቂዎቹ ወደ ግልገል በለስ ከተማ ለመግባት እና በንጹኃን ዜጎች ላይ ጉዳት ለማድረስ "ሙከራ" ማድጋቸውን ባወጣው አጭር መግለጫ ጠቅሷል።»
«በደቡብ ወሎ ዞን ለጋምቦ ወረዳ በሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ በተፈጸመ ጥቃት አምስት ሰዎች ሞቱ»
«በራያ አላማጣ ወረዳ "የትግራይ ኃይሎችን ዒላማ ያደረገ" የድሮን ጥቃት መፈጸሙን ምንጮች ተናገሩ»
See less
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ