#ጸጸትን ስለማስተናገድ።

 

#ጸጸትን ስለማስተናገድ። 
 
"የእግዚአብሄር ቃል ሁሉ ትፈትናለች፤
እርሱ ለሚታመኑት ጋሻ ነው።"
(መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፴ ቁጥር ፭)
 
#ምዕራፍ ፲፱።
 
የሰው ልጅ በሚያምንበት መስመር መሳተፍ መብት ነው። የሰው ልጅ #በማያምንበት መስመርም ቢሆን ጊዜው // ዘመኑ ካስገደደው መኖርን ለመምራት በሚያደርገው ተጋድሎ ውስጥ ስለመሆኑ አስተውሎ ሊመረምረው ይገባል።
 
130 ሚሊዮን ህዝብ ከአገሩ ውጭ የት ይሰደድ? ልሰደድ ቢልስ ይችላል ወይ? ይህንን ጽንሰ ሃሳብ በዘመነ ህወሃትም እጽፈው ነበር። የሚቻል ነገር ከገጠመ በህሊና ዳኝነት መወሰን ጥሩ ነው። #በማይቻል ሁኔታ ግን የአንዷን ቀን የለት ጉርስ መሸፈን ጋዳ ሆኖ፤ ተመችቶት በተቀመጠ ድሎተኛ ጫና በራስ ላይ ሌላ ፈተና ማከል አያስፈልግም። ህይወት ጥምልምል ነው። ያ በቂ ነው - ፈተናው።
 
ስለሆነም ወጣቶች ዕድል፤ ዘመን፤ ሁኔታ የሚፈቅድላችሁን ማድረግ ይገባችኋል። በዘመነ ህወሃት የውጭ የትምህርት ዕድል ያገኜ ወጣት አልሄድም፤ ሥርዓቱን ስለማልወደው አላለም። በዕድሉ ተጠቅሞ ለቤተሰቡም ተስፋ መሆን የቻለው ዕድሉን #ባለማፍሰሱ ነው።
 
በ6ኛው ይሁን በ7ኛው አገራዊ ምርጫ መሳተፍ፤ እጩ ሆኖ ለመቅረብ መፍቀድ፤ በድምጽ ሂደቱ ለመሳተፍ በአገኛችሁት ዕድል ሁሉ መሳተፋችሁ ወጣቶች ሆይ! #አይጸጽታችሁ። በኢትዮጵያ ውስጥ እየኖራችሁ መኖራችሁም እራሱ ፖለቲካ ነውና በሁነታዋ ሁሉ በንቃት መሳተፍ የተገባ ነው። ዕድሉ ከተገኜ።
 
በሌላ በኩልም በአገራዊ ምክክሩም መሳተፍ መልካም ነገር ነው። በተሳትፎው ውስጥ ትልቁ ቁምነገር በዕድሉ ከክፋ ሃሳብ ጋር አለመገናኘት ግን ይገባል። መሳተፍ ጸጸት #አይደለም
 
ታላቅ ተመክሮ፤ ጥሩ ሰወች ጋር የምትገናኙበትም አጋጣሚ ነው። ግን እናታችሁን ኢትዮጵያ አገራችነን ለዘላቂ የካንሰር #ህመም በሚዳርግ ውሳኔ ላይ ደግፋችሁ ድምጽ መስጠት መብት ቢሆንም፤ የውሳኔው ሁነት አብዛህኛውን ወገናችሁን የሚያስከፋ ከሆነ ጸጸቱ ሊነሳ የሚገባው ከዚህ አንፃር ብቻ ነው።
 
በፓርላማም በብልፄው ፈቃድ ምደባውን ያገኛችሁ ሁሉ፤ በአማራጭ ዕድሉ መጠቀም የሚያስከፋ አይደለም። ችግሩ በፓርላማ ቆይታ እናት አገር ኢትዮጵያን ከውስጥ #በሚያሳዝን ጉዳይ ላይ በድጋፍ ድምጽ ከተሳተፋችሁ ብቻ ነው ጸጸት ሊሆን የሚገባው።
 
አዱኛወቼ ሸበላ ቀን። አሜን።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
 
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
11/08/026.
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።