"፭ #መቶወቹ።" #ትንሽዬ ዕይታ።
"፭ #መቶወቹ።"
"እግዚአብሄርም አለ ሰውን በመልካችን
እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር።"
(ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፳፮)
#ትንሽዬ ዕይታ።
እንዴት ነን? አንድ አገር ነው ያለን። አንድ ማዕድ ነው ያለን። አንድ እልፍኝ ነው ያለን። ስለሆነም #አግለን ይሁን #አቅርበን ልናየው የምንችል አመክንዮ ቢኖርም የእናት ጉዳይ ግን #አናት ነው። ልናደምጠው፤ ልንከታተለው፤ ሰሙን አልሰሙን ዕይታችን ማጋራቱ የቤታዊነት ልዕልና ጋር ያገናኛል እና ሁኔታውን መከታተሉ ይጠቅማል። የዜግነት #እኩሌታ ወይንም #እርቦ ይሁን #ሲሶ ስለለው።
#የኮሚሽኑ ዕለታዊ ማብራሪያ።
"አዳሪ አጀንዳወች ሊኖሩ ይችላሉ። ለቀጣዩ ትውልድ ም ሊሻገሩ የሚችሉ።"
የሁለንም ኢትዮጵያዊ ዜጋ #ሰብሳቢ የሚያደርገው #በክብነት ውስጥ #ማዕዳዊ የማድረግ አቅም ያለው፤ እኛን ኢትዮጵውያንን ብቻ ሳይሆን #አፍሪካውያንንም እንዲሁም ሉላዊ የዲፕሎማት ፬ኛ ግሎባል መዲናይቱን፤ ባለቤት ወይንም #ተጠማኝ ሊያደርግ የሚችል የምክር ሃሳብ ሊሆን ይችል ይሆን #አዳሪ ይሁን ተገፍቶ በቀጠሮ ለቀጣይ #የትውልድ #ቀጣይ የቤት ሥራ ሊሆን የሚችለው?
ፊት ለፊት ተገናኝቶ መነጋገሩ መልካም ነው እንጂ፤ በጠቅላይ ሚኒስተሩ በኦሮምያ ያደረጉት ንግግር ተስፋው የገዘፈ ፈተና ሥራ ላይ እያለ ሳይቀር እንዳለበት ይገልፃል። በትርጉም ነው የሰማሁት። የነበረን ለማስቀጠል ድካሙ ይሁን ወጪው ከፍ ያለ ነው።
የሆነ ሆኖ በርከት ያሉ ሃሳቦችን ኮሚሽኑ በማብራሪያው ገልፆል። ሃሳቦቹን ፕሮፌሰር አስታግሰው ቢያቀርቧቸውም፤ የሃሳብ ጦርነቱ #የጦፈ እንደ ነበር ትንሽ ፍንጭ ይሰጥ ይመስላል። የአቀራረቡ #ትህትና ግን የኢትዮጵያን #ኦርጋኒክ ተፈጥሮ ልክነት አይቸበታለሁኝ።
ኢትዮጵያ ከ፹ በላይ ብሄረሰብ አላት፤ ከ120 - 130 ሚሊዮን የሚገመት ህዝብ አላት ይባላል። በዚህ ልክ ወዘተረፈ ፍላጎት፤ ምኞት፤ ሃሳብ እና ጥያቄ ይኖራል። ያን በተቻለባቸው ቀዮወች አሰባስቦ በአንድ ብሄራዊ መንፈስ ለማስተዳደር የገዘፈ ኃላፊነት ነው። በዚህ ዘመን በአንድ ቤተሰብ ያለው ሁነት እንኳን አልተቻለም። #የእኔ ገዢ ሆኖ የወጣበት ዘመን ነውና። እንኳንስ ፬ሺ።
ክብረቶቼ እስቲ በሌላ የሙግት ሃሳብ ከች እስክል ድረስ ደህና ቆዩልኝ። አሜን። ነገረ የገበሬ ጸጋ ህወሃት ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ #የፖለቲካ #ውክልና ገበሬው የለውም።
ውስጤ በጣም ያዝን ነበር። ጠሚር አብይ ወደ ስልጣን ሲማጡም በጹሁፍ አሳስቤያቸው ነበር። የዋህነቱ፤ ንጽህናው፤ ታማኝነቱ፤ ትጋቱ ልዩ ነው። አገር ጠቀምም ነው። ስለሆነም ለምክክሩ #መወከል መልካም ነገር ነው። ገበሬ መሠረት ነው። በተጨማሪም ሰውኛ እና ተፈጥሮኛ ጸጋውም በተሰጠው ልክ ነው።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
10/08/026.
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው።
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ