የኢትዮጵያን ፖለቲካ ሊመራ የሚገባው #ሰብዓዊነት እና #ተፈጥሯዊነት ሊሆን ይገባል።
"ልቤ ጽኑ ነው፥
አቤቱ ልቤ ጽኑ ነው፤
እቀኛለሁ፤ በክብሬም እዘምራለሁኝ።"
(መዝሙር ፻፯ ቁጥር ፩።)
ትናንት የአማራ ፖለቲከኞች እስር እና የፍትህ ውሳኔ ሃሳቡን ሙሉውን፤ የእኔ ሃሳብ ሳይታከልበት ከBBC ያገኜሁትን መረጃ ሼር አድርጌ ነበር። #ሳስበው ነው ያደርኩት።
የተጠየቀውን ቅድመ ሁኔታ ያልተቀበሉ ፖለቲከኞችን ሊስቱን ትናንት አላገኜሁም ነበር። አሁን ከአቶ ዳንኤል በቀለ ፔጅ የተገኜ። አመሰግናቸዋለሁኝ።
#ምዕራፍ ፲፱።
ጉዳዩን ከህግ አንፃር የመፍትሄ አቅጣጫው ከድንጋጌወች ጋር አዛምደው ቁልፋን የሚፈቱት የህግ #ባለሙያወች ናቸው። ለዚህም ነው ከአስተያዬት የተቆጠብኩት።
በሌላ በኩል ውሳኔው የእኛ ዕይታ ሳይሆን #እንግልት ላይ የሚገኙት የፖለቲካ እስረኞችን ውሳኔ ብቻ ነው ሊጠብቅ የሚገባው። እስረኞች ከጠበቆቻቸው ጋር፤ ከቤተሰቦቻቸው ጋር መክረው፤ ጉዳዩን አስበውበት የሚፈጽሙት ቢሆን የተሻለ ነው። ሃሳባቸውን የሚያባትል ዕይታ ከማንኛውም ወገን መቅረቡ ጥሩ አይደለም። ከእኛ ምንም ተጨማሪ #ጫና አያስፈልጋቸውም።
ጠቃሚውን እና ጎጁን መስመር የመወሰን አቅም የባለ ጉዳዮቹ ጉዳይ ነው። እንደ እኔ ያለ ፍትህ ፍለጋ በቋሚነት #መባተል ነው። እስረኞች #እንዳይዘነጉ #አዌርነስ መፍጠር ነው። በመሪው በብልፄው ላይ #ጫና መፍጠር ነው በብዕር እና በብራና አጋዥነት።
የእኔ ንጹህ ፍላጎት የሃሳብ አፍላቂ ሞጋቾችን መመከት እንጂ ህሊናን ማሰር አያስፈልግም ባይ ነኝ። በኢትዮጵያ #አንድም የፖለቲካ #እስረኛ እንዳይኖር ነው እምተጋው። ሙሉ ዕድሜዬ አቋሜ ይህ ነው። ከህወሃት ጋርም ሙግቱ ያ ነበር።
የመጀመሪያው ትልቁ ጉዳይ የኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች ጉዳይ ቅድሚያ እንዲሰጠው ነበር። ተሳክቶም ነበር። መሪ የፖለቲካ ድርጅት ተሁኖ ሃሳብ ከተፈራ የኢትዮጵያ ፖለቲካ #ይጫጫል። ክርክር፤ ሙግት ጤናማ መስመር ነው።
የሆነ ሆኖ እግዚአብሄር አምላክ ሁሎችንም የፖለቲከኛ እስረኞች ለቤታቸው ከቤተሰባቸው ጋር ለመገናኜት አምላካችን፤ አላኃችን ያብቃቸው። አሜን።
ብልፄው የዘረዘረው ቅድመ ሁኔታ #የዕድሜ #ይፍታህ ዓይነት ነው። #ግዞትም ይመስለኛል። አንድ አውራ የፖለቲካ ድርጅት የሃሳብ አቅም ሲያንሰው ነው ሞጋቾቹን የሚያስረው። ይህ የተገባ አይደለም።
አገር እየመሩ የተለዬ ሃሳብ ይህን ያህል #ተፈርቶ፤ ካለውሳኔ ይህን ያክል የአማራም ይሁን የሌላ ብሄረሰብ ፖለቲከኞች ሊታሰሩ፤ ሊንገላቱ፤ የፍትህ ያለህ ብለው ሊጨነቁ፤ ሊጠበቡ አይገባም።
ለልጆች ህሊና ማሰብ ይገባል። ይህን እያዩ ያደጉ ልጆች ነገ #ዕድሉን ሲያገኙ ይህን ጠቃሚ ያልሆነ መስመር ይከተላሉ። ማቆሚያ የለውም። የእኔ ፍራቻ ከዚህም አንፃር ነው።
ለነገሩ ቀና ሃሳብ፤ ተመክሮው ዝልቅ የሆነ ሃሳብ ከዕድሜም ይገኛል። የማዕረግ ተመራቂዋ የፍትህ ሚኒስተሯ በጣም ወጣት ናቸው። ዳኝነትን ይፈትናል ወጣትነት።
የወጣትነት ተፈጥሯዊ ባህሬ ፈታኝ ነው። #ያስገድዳልም። ስለዚህ ምራቁን የዋጠ፤ በተመክሮውም ዝልቅ ክህሎት ያለው በተለይ ለዚህ የኃላፊነት ቦታ በእጅጉ ያስፈልጋል። ለጠጣዩ የካቢኔ አደረጃጀት ቢታሰብበት ጥሩ ነው። የፍትህ ሚኒስተር #በጣምራ በውጭ ጉዳይ ሚር የሚታገዝ መሆኑ ቢገባኝም።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
13/08/026.
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
"መንግስት ያቀረበውን የይቅርታ ሰነድ አንፈርምም ያሉ ተከሳሾች እነማን እንደሆኑ የሚያመላክት የስም ዝርዝር አዲስ ማለዳ ደርሷታል
አዲስ ማለዳ
August 12, 2026
ረቡዕ፣ ነሐሴ 06 ቀን 2018 ዓ.ም
መንግስት ያቀረበውን የይቅርታ ሰነድ አንፈርምም ያሉ ተከሳሾች እነማን እንደሆኑ የሚያመላክት የስም ዝርዝር አዲስ ማለዳ የደረሳት ሲሆን በዚህ መዘርዝር ውስጥ በዋናነት የቀድሞው የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል ዮሐንስ ቧያለው፣ ዶ/ር ወንደወሰን አሰፋ፣ ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው፣ መምህርት መስከረም አበራ፣ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፣ ጎበዜ ሲሳይ፣ ገነት አስማማው ይገኙበታል፡፡
ሙሉ ዝርዝራቸው ተከታዩ ነው፡-
1. አቶ ዮሐንስ ቧያለው
2. ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃ/ማርያም
3. ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው
4. ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ
5. ዶ/ር መሠረት ቀለመወርቅ
6. ዶ/ር ዘሪሁን ባህሪው
7. ጋዜጠኛ መስከረም አበራ
8. ጋዜጠኛ ገነት አስማማው
9. ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው
10. ጋዜጠኛ ዓባይ ዘውዱ
11. ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ
12. አቶ አለልኝ ምህረት
13. አቶ መንበር አለሙ
14. አቶ ማይክ መላክ
15. አቶ አሳምነው ታደሠ
16. አቶ ደሳለኝ እጅጉ
17. አቶ እሱባለው በለጠ
18. አቶ እስክንድር ሽፈራው
19. አቶ መሰለ ቸሩ
20. ኢ/ር ፍርዱ ተፈራ
21. አቶ ጫኔ ዘየደ
22. ወ/ት ሃሊማ አህመድ
23. ወ/ት ህይወት አለማየሁ
24. አቶ ሲሳይ መልካሙ
25. አቶ ታደሰ ወዳይነው
26. አቶ በላይ ሲሳይ
27. አቶ ያሬድ ግርማ
28. አቶ ማረው ስለሺ
29. አቶ ሠለሞን ተፈሪ
30. አቶ ሙሉቀን ተስፋዬ"
"ለአዲስ ማለዳ የደረሳት ደብዳቤ እንደሚያመላክተው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን(ኢሰመኮ) ከመንግስት ጋር በጀመረው ውይይት በመጨረሻ ፈርሙ የተባሉት ተከታዮቹን ጉዳዮች ያካትታል፡-
“በአማራ ክልል ለተፈጠረው ቀውስ ኃላፊነት ውሰዱ፤ በአማራ ክልል በተፈጠረው ቀውስ ለሞቱ ሰዎች፣ ለቆሰሉ ሰዎች (በየመዝገብ ቁጥሩ ይለያያል) ፈጽመናል ብላችሁ እመኑ፤ ለወደመው በበሊዮን የሚገመት ንብረት
ፈጽመናል ብላችሁ እመኑ፤ ሀገሪቱ በአማራ ትውፊቶችና እና እሳቤ ካልተመራች ማለታችሁን ወንጀል ነው በሉ፤ ያለ አግባብ የተወሰዱ የአማራ ርስቶች መመለስ አለባቸው ስለማለታቸው እና ይህም ወንጀል መሆኑን እንዲያምኑ” በቅድመ ሁኔታ እንደቀረበላቸው አዲስ ማለዳ የተመለከተችው ያመላክታል፡፡
ይህንን ተከትሎ ተከሳሾቹ በሰጡት ምላሽ “እኛ ወንጀለኛ ነን ብለን አንፈርምም፤ በህግም፣ በሞራልም፣ በታሪክም ተቀባይነት የለውም ብለን አንፈርምም” ብለዋል፡፡
አክለውም፤ “የአማራ ህዝብ ጥያቄዎችም ህጋዊ ናቸው ብለው እንደሚያምኑ በመግለጽ የ60 ሚሊዮን ህዝብን መልካም እሴት ወንጀል ነው ብለን አውቀን አንሰጥም ወንጀልም አይደለም፤ በህገመንግስት እና በዓለምአቀፍ ህጎች ነፃ ሆኖ የመኖር መብታችንን ፈቅደን አንተውም፤ በህግ የተከለከለውን ራስን መከላከል እና ራሳችንን ወንጀለኛ አናደርግም” ሲሉ ምላሽ መስጠታቸውን መመልከት ተችሏል፡፡
ዋናው ጉዳይ ፍቺው አለመሳካቱ ሳይሆን ሂደቱ መጀመሩ ነው።
በሰምምነትና በይቅርታ እሰረኞቹ የሚፈቱበተን ሁኔታ ለማሳካትና ለማፋጠን ኢሰመኮናለሎችም ተቁዋሞች ጥረተቸውን ቢቀጥሉ መልካም ነው።"
See less
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ