አዲስዬ #የእግዚአብሄር እጅ ያለባት ከተማ ናት። አዲስና #ምሩቅ መንፈስም ናት።

 

አዲስዬ #የእግዚአብሄር እጅ ያለባት ከተማ ናት። አዲስና #ምሩቅ መንፈስም ናት።
 
"ጎለመስኩ አረጀሁም፤ ፃድቅ ሲጣል፤
ዘሩም እህል ሲለምን አላዬሁም።"
(መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፴፯ ቁጥር ፳፭።)
 
«በአዲስአበባ ጉዳይ አስደንጋጭ ጉድ ተሰማ! | የአዲስአበባ እጣፈንታ ተወሰነ? | ወይ አዲስአበባ! አፋጀቻቸው!| Ethiopia»
 
#ምዕራፍ ፲፱።
 
ሊንኩን መለጠፌ የተረጋጋ ውይይት ስለሆነ ነው። ቁጣ የለውም። ብስጭት የለውም። ገረጭራጫ መንፈስ የለውም። የእቴጌ #ጣዩቱ ከተማ መነሻዋ፤ ታዳጊነቷ፤ ወጣትነቷ፤ ጎልማሳነቷ፤ አዛውንትነቷን ገለጣው ይተነትናል ውይይቱ። 
 
ለምን እሷን የመሰለ ከተማ መፍጠር አልተቻለም ሲል ትንተናው ይጠይቃል። ከተፈላጊነቷ #ዝቅ የማድረግ ፕሮጀክት ሊኖር እንደሚችል ኢትዮጵያዊው ጉግል አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገልጠው ነበር። የሸገር ሲቲ እኮ ከዛ ጋር የተያያዘ ይመስለኛል። አዲሱ የአውሮፕላን ማረፊያ ጥንስስም ለዛ ይመስላል። ግን አሁንም ጉምጅቱ ተጧጡፏል። 
 
ግን ኦህዴድ ድሬን፤ ደብረዘይትን፤ ናዝሬትን፤ ጅማን የከፋን፤ ሚዛን ተፈሪንም፤ ኢሊባቡር መቱን፤ ባሌ ጎባን፤ ወለጋ ነቀምትን፤ አርሲ አሰላን፤ ሻሸመኔን ጠቅልሎ ተሰጥቶት ግን የአዲስ አበባ #አቻ ለመፍጠር ምን ተሳነው?።
 
ስንት ዓመት? ከ30 ዓመት በላይ። ጅማ እማ በሚያሳዝን ሁኔታ እንደ ነበር ሰምቻለሁኝ። ድሬም እንዲሁ። ከእጅ የገቡ የቀድሞ ስንት የክ/ ሃገራት ከተማ ለኦህዴድ ተሰጠው??? ግን ምንም …… በተሠራ ነገር ላይ ብቻ #የእኔን ገነባበት። በዚህ መፈተን ይቻላል። 
 
በሌላ በኩል አይደለም ከአዲስ አበባ ጋር የሚወዳደር፤ ከአዋሳ ጋርም የሚተካከል ከተማ ማድረግ የክፍለ አገራትን ዋና ከተማ ብቁ፤ ሳቢ እና አጓጊ ማድረግ አልቻለም በዘመነ - ህወሃት። 
 
ስምንት ዓመቱ የብልፄው ሲታከልበት ምን ያህል #የሚያረካ ከተማ ተፈጥሮ #ከምታስጎመጀው የአዲስ አበባ ከተማ ጋር መወዳደር እንደተቻለ አላውቅም። ሂጅ ስላላየሁኝ። ሻሸመኔንም በተደጋጋሚ መንደዷን እያዘንኩ አዳምጫለሁኝ።
 
የሆነ ሆነ ይህን ትንተና እያዳመጥኩኝ ተሞክሮ ተጠቃሚነቷን የመቀነስ ክፋ ሃሳብ፤ ያልተሳካበት ሁነትን ሳስበው አዲስ አበባ ስትመሠረት #የእግዚአብሄር እጅ እንዳለባት አመንኩኝ። በሌላ በኩል የኗሪወቿን የአስተሳሰብ አድማስ ሉላዊነት ከውስጤ ስመረምረው ደግሞ የፈጣሪ የአላህ #መባረክ እንዳላት ተረዳሁኝ።
 
ነዋሪው ሁሉም በተፈጠረበት ንጥረ ነገር መኖሩን የመራበት የአኗኗር ዘይቤ፤ የአፍሪካውያን ውስጣቸው ያደረጉበት አመክንዮ፤ ዓለም ለ፬ኛ ዲፕሎማሲያዊ ከተማ አጭቶ ብቁ አድርጎ የማብቃት ክህሎትን ያስዋበት ሁነት ሲጤን የአዲስዬ የሁለመናዋ ውስጣዊ ውበት የፈጣሪ #መሰጠት እንደሆነ ተረዳሁኝ። ባትታገሉት ጥሩ ነው። "ላም እረኛ ምን" አለ ቢደመጥ።
 
አዲስ ፈተናውን ሁሉ ተቋቁማ እስከዚች ቅጽበት ድረስ ቤታችን፤ ማዕዳችን፤ የሁላችን የመንፈስ ማረፊያነቷ በተለይ ለእኛ ለስደተኞች አገር አለኝ፤ ኢትዮጵያ የምትባል ፓን አፍሪካኒስት የነፃነት ጉልልላት፤ ዋና ከተማዋ #አዲስ አበባ ይባላል ማለት ችለናል። ስለነገ ደግሞ ባለቤቱ ይጎብኛት። አሜን። 
 
አዲስ አበባ በአንድ #ዞግ ሥር ከሆነች የአፍሪካ አንድነት ድርጅት #መቀመጫ #ሊቀየር ይችላል። ይህ ደግሞ የግብጽን የሙሉ ዕድሜ መሻት ይሁን የሌት ተቀን ህልም ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ማተም ይሆናል። በዚህ ውስጥ የፓን አፍሪካ መሪነታችንም #ይናዳል
በሌላ በኩል ከኒወርክ፤ ከቤይና፤ ከጄኔባ ቀጥሎ ያለችው አዲስዬ የዲፕሎማሲ ከተማነቷም ፈታኝ ዕጣ ፈንታ ይገጥመዋል። ይህ ሁነት ኢትዮጵያዊነት በራሱ ዜጎች አፋፍ ላይ እንዲገኝ #ገፊ ሁነት ይፈጥራል። 
 
አፍሪካውያን ብቻ ሳይሆን #ጠይም ዕንቁወች ግሎባሊ ተስፋቸው ይነጠቃል። በርካታ ትናንሽ የደሴት አገራት ውስጣቸው ከአዲስዬ፤ ከኢትዮጵያ ጋር ነው። አዲስ አበባን ያህል ርዕሰ መዲና ለአንድ ዞግ መሸለም፤ የጠይም ዕንቁወች ራዕያቸው #ይሸበሸባል። ናፍቆታቸው #ይሸሸጋል። መጠጊያቸው #ይለሞጣል። ይህ ግድፈት እንዳይፈጸም በእርጋታ እና በአትኩሮት እኛነትን ሳያገሉ እራስን መግራት የሚያስፈልግ ይመስለኛል። 
 
ኢትዮጵያ ርዕሰ መዲናዋን ማረጋገጥ ካልቻለች፤ በዕርሰ መዲናዋ ላይ እርግጠኛ መሆን ከተሳናት መንፈሷ #ይሰደዳል። ችግሩ ወደ ሉዓላዊነት ፈተና ሊያስገባት ይችላል። ዜጎቿም ለሥነ - ልቦና #ስውር ጥቃት ሊጋለጡ ይችላሉ። 
 
ኃላፊነት ያላቸው ዘመን ሰጥ የብልጽግና የኦሮሞ ባለሥልጣኖች በጥሞና አስበው፤ ጥርት ካለ አቋም እና ውሳኔ መድረስ ከተቻለ አሰፍስፈው ፍርሰቷን፤ ድቀቷን፤ #ስንፈቷን ላጩ ሁሉ የመንፈስ #ቆጣቸውን መናድ ይቻላል።
 
ካልሆነ ግን ኢትዮጵያ ከእጅ ላይ #ታመልጣለች። ወርቅ ከቀለጠ ይፈሳልና። ጉዳዩ የዋዛ አይደለም----ና። አንድ እሳር ሲመዘዝ ወዘተረፈ ችግር መፈናፈኛ ያሳጣል። ወቅትን አድምጦ በጊዜ መወሰን ይገባል። 
 
አዱኛወቼ የእኔ መምህሮች እንዴት አርፍዳችሁ፤ ዋላችሁልኝ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። 
 
አንድአፍታ ጥሩ ውይይት አድርጓል። አመሰግነዋለሁኝ።
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
12/08/026.
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።