#ለነውር ሌላ #ነውር መመከቻ ሊሆን አይችልም።
"ምድርን ሰንጥቀህ ፈሳሾችን አወጣህ።"
(ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፱።)
#ምዕራፍ ፲፱።
ለነውር ሌላ የነውር ዓይነት ለማነፃጸሪያ ሊቀርብ አይገባም።
ማነፃጸር መልካም ነገርን // ከመልካም ነገር ጋር ከሆነ የተገባ ነው።
ለነውር የሚሰጠው ጊዜ ዕድሜን ይዘርፋል። ከነውር
ጋር መኖር የዕድሜ ብክነት በብክለት ነውና።
የነውር ዓይነቱ ብዙ ነው። አንዱ ክህደት ነው። መካድ።
ክህደቱ አፈፃጸሙ፤ አድራጊው እና ተደራጊው ቢለያይም
የነውርነቱን ተፈጥሮ ግን አይቀይረውም።
የሁሉም የህግ ትልልፍ ሁነቶች በሙሉ #ነውር ናቸው።
ህግ ጣሽነት። ትዳር - ሲከዳ፤ ቤተሳባዊነት - ሲከዳ፤
ጓደኝነት - ሲከዳ፤ ልጅነት - ሲከዳ፤ እህት - ወንድምነት
ሲከዳ፤ እናት አባታዊነት - ሲከዳ፤ አገር ሲከዳ ይሁን ኃላፊነት
ሲጣስ የድርጊቱ ዓውራ #ክህደት ነው።
እናቱን የከዳ አባቱን ከከዳ ጋር ማነፃጸር አይገባም። ክህደቱንም
ማፎካከር አይገባም።
እንደ ወርቅ የነውር ደረጃ ሊያወጡ የሚሹ ሰብዕናወች ይገርሙኛል።
አይቻልም።
"እናንተ ነውርና ነቀፋ የሌላችሁና ቅዱሳን አድርጎ
በእርሱ ፊት ያቀረባችሁ ዘንድ በፊት የተለያችሁትን
ክፋ ሥራችሁንም በማድረግ፤ በአሳባችሁ ጠላቶች
የነበራችሁትን አሁን በሥጋው ሰውነት በሞቱ በኩል
አስታረቃችሁ።"
(ቆላስያስ ምዕራፍ ፩ ቁ ፳፩ - ፳፪)
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
03/08/026.
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ