#ዘመነ #ሰማዕትነት በየለቱ #በየባዕቱ። #በዚህ መሰል ሂደት መሬትም --- ታዝናለች። አየሩ --- ያዝናል። ተፈጥሮ --- ያዝናል። ዘመንም --- ያለቅሳል። ፈጣሪም ይከፋል።
"አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።"
#ምዕራፍ ፲፱።
ፈውስ፤ መፍትሄ፤ መዳን፤ ርህርህና፤ ዕውቀት ሁሉም ነገር እንዳልነበረ
የሆነበት የሃኪሞች ጉዳይ የኢትዮጵያ የተስፋዋ #ውጋት የሆነ ገጠመኝ ነበር፤
የሁሎችም ሰማዕትነት በአማራ ክልል የተከወነ ነው።
በሱር ኮንስትራክሽን በማዕከላዊ ጎንደር ለመጀመሪያ ጊዜ 80ሺህ ተፈናቃይ እስከ ስሜን ፓርክ ቃጠሎ
ድረስ የተከወኑት አሰቃቂ፤ ሰላም ነሽ ጉዳዮች ባለቤቱን በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም #የተቀየጠ ስለሆነ።
የሆነ ሆኖ በሁሉም ሂደት የሰው ልጅ እንዲህ በየለቱ ተስፋውን ማጣቱ እጅግ …… እጅግ
ያሳዝናል። ዕድሜው እንዲህ መቀጨቱ። ትናንት በጉራጌ ዞን ነዋሪ የሆኑ አማራወችም
እንዲሁ #ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።
ብሄራዊ - አገራዊ - ኢትዮጵያዊ ምምክር እየተደረገ ባለበት በአሁኑ ወቅት፤
ፈፃሚው "በየመንግሥት ወታደሮች" ናቸው የሚል አንብቤያለሁኝ።
ይህን መሰል ሂደት በጥንቃቄ ሊታይ ይገባዋል። ምክንያቱም ለራሱ
ለኢትዮጵያ መንግሥት ስለማይጠቅም።
በህወሃት የማብቂያ ዘመን የጸጥታ ሠራተኞች ሰብአዊነትን ይማሩ ዘንድ
ውጭ አገር የሆነ ዕድል ተመቻችቶ ነበር።
መጨረሻም የህወሃት ዘመን #ተጠናቀቀ። ከዚህ ትምህርት መውሰድ ይገባል።
አሁን ቅርብ ጊዜ ምርጫ ያካሄደ መንግሥት ብዙ ችግሮችን ይሁን
ፈተናወችን አስታግሶ መያዝ ይገባዋል። ይህን ሲያደርግ ተጠቃሚው
እሱ እራሱ መንግሥት ነው።
የተዋህዶ ልጆች ጥብቅ ሱባኤ ላይ ናቸው። ይህንንም እንደ አገር ማሰብ ይገባል። ፆም
ላይ ጭካኔ????
#በዚህ መሰል ሂደት
መሬትም --- ታዝናለች።
አየሩ --- ያዝናል።
ተፈጥሮ --- ያዝናል።
ዘመንም --- ያለቅሳል።
ፈጣሪም ይከፋል።
አንድ ሰውን ደግሞ ማግኜት አይቻልም። ሞት መራራ ብቻ ሳይሆን ለቤተሰብ
እንደ ገል መንፈስን ወደ ስብርባሪ የሚቀይር ጨካኝ ክስተት ነው።
ለወላጆቻቸው መጽናናትን እመኛለሁኝ።
የሃዘን ዳርቻ ፈጣሪ ያድርግልን። አሜን።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
12/08 /026.
በቃችሁ ይበለን አምላካችን አላሃችን። አሜን
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ