#መለሲዝም ዕድለኛ ነው። ድምጡን አጥፍቶ ሥራውን ይሠራል። #ሌጋሲው ቀጥሏል። 2) ዝምታ #ከጩኽት ይከብዳል።
1) #መለሲዝም ዕድለኛ ነው። ድምጡን አጥፍቶ ሥራውን ይሠራል። #ሌጋሲው ቀጥሏል። 2) ዝምታ #ከጩኽት ይከብዳል። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አቶ አህመድ ሸዴ የፓርላማ አፈ ጉባኤ። ወሮ ሙፍያት ካሚል የፌድሬሽን ምቤት አፈጉባኤ #ምዕራፍ ፳። ሁለት እርዕሶችን በአንድ ላይ አጣምሬ እስቲ ልሂድበት። ከትናንት በፊት የሲዳማ የክልል ፕሬዚዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞን ወደ #ፌድሬሽን #ምክርቤት አፈጉባኤ ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ ጽፌ ነበር። የግምቴ አቅጣጫ ትክክል ነበር ማለት ነው። "የአዲስ መንግሥት ምሥረታ።" መንግሥት በሌላት አገር የተፈጠሩ የአገር መሪወች? የሚገርሙ እኮ ናቸው። ኢትዮጵያ እኮ ከቀደምት መንግሥት ከመሠረቱ አገራት ተርታ የተመደበች አገር ናት። አየር ላይ ተተክሎ፤ በቅሎ እንደ ጸደቀ፤ እንደ አፈራም ሰብል ኢትዮጵያን #አብይዝም ሠራሽ አድርገው ባያቀርቧት ጥሩ ነው። ለነገሩ ኢህአዴግ ነፍሱ እንዳለ የሚያሳይ የምደባ ኩነት ተስተውሏል። በሌላ በኩል #ስብጥሩንም በማስተዋል መመርመር ይገባል። ብልሁ ጉዳይ ያ ይመስለኛል። አዲስ ነገር ግን #አላየሁም ። ሳሎን የነበረውን ወደ ጓዳ፤ ጓዳ የነበረውን ወደ በረንዳ፤ ከበረንዳ የነበረውን መኜታ ክፍል ሽግሽግ ነው። ለውጥ ለዛውም " #አዲስ " የት ላይ ይሆን ያለው። ይልቅ በቃላት፤ በሞቶ፤ በሥንኝ ውበት ከመጽናናት የተረሳው ቢሮክራሲ፤ ከፖለቲካ #ውክልና #ውጭ የሆነችውን #ቅድስት #ኦርቶዶክስ #ተዋህዶን ማሰብ። ምንም አያደርግም ተብሎ የተናቀውን ዝምተኛውን የማህበረሰብ ክፍል ሊያሳምን የሚችል የቁም ነገር ትጋትን አቅዶ መተግበር በእጅጉ ይገባል። ...