(ለመንግስትና ለብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች)
ከአቶ ጀንበሩ አረጋ ፔጅ ነው ያገኜሁት። አላነበብኩትም። እንዳያመልጠኝ ነው ፖስት ያደረግኩት። ይድረስ ለመሪዎቻችን !! (ለመንግስትና ለብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች) ስለአገሬ ሰላምና ደህንነት አሁንም እጮሀለሁ !! በጀምበሩ አረጋ (ረ/ፕሮፌሰር) ጎንደር ዩኒቨርስቲ ስነ-ትምህርት ኮሌጅ ሀ) ታሳቢዎች (Assumptions) አገሬ ኢትዮጵያ አሁን ከገጠማት ውስጣዊ ፈተና በፍጥነት ትወጣ ዘንድ ይህንን የአጭር ጊዜ የመፍትሔ ሀሳብ በራሴ ተነሳሽነት ሳቀርብ የሚከተሉትን ጉዳዮች ታሳቢ አድርጌ ነው፡፡ የአገሬና ሕዝቧ ሰላምና ደህንነት እንደሚያስጨንቀው አንድ ተራ ዜጋ ለሰላምና ደህንነት መረጋገጥ ያለኝን ከመወርወርና ከቅንንነት በስተቀር ምንም አይነት ሌላ ፖለቲካል ፍላጎት (Other Political Interest) የሌለኝ መሆኑን ትረዱኛላችሁ በሚል የመንግስትና የገዢው ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ከተስተካከለ የአገራችን ችግር በወሳኝ መልኩ መፍታት እንችላለን የሚል ጠንካራ ዕምነት ስላለኝ ከመንግስትና ከገዢው ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች መካከልየችግሩ አሳሳቢነት የሚያስጨንቃቸው አንዳንድ አመራሮች ይኖራሉና ለመፍትሔውም ይተጋሉ የሚል ግምት ስላለኝ ከታሪካችን እንደምንረዳው መላ የአገራችን ሕዝብ መንግስት የሚለውን በቀላሉ የሚያምንና በጠንካራ መንግስት አስፋላጊነት የሚያምን እንደሆነ ስለምረዳ መሰሪ ፖለቲከኞቻችን በየመድረኩ እንደሚያስጮሁት የጨቋኝ-ተጨቋኝ ትርክት ሳይሆን አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ አብሮነትን የሚፈልግ ነው የሚል ጠንካራ እምነት ስላለኝ ነው፡: ለሕዝብ እብሮነትና የጋራ ተጠቃሚነት የሚተጉ ቅንና ቆራጥ መሪዎችን ወደፊት ካመጣናቸው የሕዝቧ ሰላምና ደህንነት የተረጋገጠማት ውጫዊ ጠላቶቻችን በርቀት የሚያከብሯትና በቀላሉ የማትደፈር ጠንካራ ኢትዮጵያን በ...