ኢትዮጵያ #የጭቃ ምርጊት ወይንም ልስን አይደለችም። ኢትዮጵያ አፈጣጠሯ ይሁን ጸጋዋ #miracle ነው። የኢትዮጵያ ተክለ ማንነት #ከአዕምሮ በላይ ነው። #በመሰጠት የተሰጣት አገር። የምትመስጥም።
ኢትዮጵያ #የጭቃ ምርጊት ወይንም ልስን አይደለችም። ኢትዮጵያ አፈጣጠሯ ይሁን ጸጋዋ #miracle ነው። የኢትዮጵያ ተክለ ማንነት #ከአዕምሮ በላይ ነው። #በመሰጠት የተሰጣት አገር። የምትመስጥም። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። #ምዕራፍ ፲፱። ኢትዮጵያን አለማወቅ ብዙ ዋጋ አስከፍሏል። ወደፊትም ያስከፍላል። ኢትዮጵያን አቅሎ ማየትም ፋንታዚው #ምራቅ ሆኖ እንዲቀር ትናንትም አድርጓል - ነገም። ኢትዮጵያን #መተንበይ ፤ #መገመት ፤ ማቀድ እና ግብ ማሳካት በእሷ ላይ እስተ ዛሬ አልተቻለም - ነገም። ይመኟታል ሊገዟት፤ ሊጨቁኗት የተመኟት ግን ተሳክቶላቸው ትናንትም አያውቅም - ነገም። ኢትዮጵያን ክዶም ይሁን በእሷ ላይ ደባ የሠራም አይበረክትም። #እርቃኑን ይቀራል። ኢትዮጵያን ቱርኮች፤ ፖርቹጊዞች፤ ጣሊያኖች፤ እንግሊዞች ወጣ ገባ ቢሆንም ሌሎችም ተመኟት ግን ምኞቷታቸው አልተሳካም። መጨረሻ የውስጥ ኃይሎችን በመቅረብ፤ በመርዳት በማደራጀት የዞግ ፖለቲካን ከብክበው ቤተ - መንግሥት አስገቡ። ሌላም ሌላም ሁነት ተፈጠረ። ኢትዮጵያ ግን የአፍሪካ #አንከር ሆና፤ የዓለም ፬ኛ #ርዕሰ መዲና ሁና አለች። ዛሬ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ነገም ትኖራለች። ፈላስፊት ኢትዮጵያ #የሚያኖራት ተመርቃ የተፈጠረችበት miracle ጸጋ አይደፈሬ አድርጓታል። ይህን የሚፈታ ቁልፍ ከማንም፤ ከየትም አይገኝም። ስለዚህም የየዘመኑ ሟርተኞች ያሰቡትን ትናንም አላሳኩም፤ ነገም አያሳኩም። ምንግዜም አይሳካም። "በፌድራሉ" እና በህወ...