ልጥፎች

መቼ ነው ወደ ጎልማሳነት የምትሸጋገሩት? ምን አለ #ከእጩ ወጣትነት እራሳችሁን ብትታደጉ?

  መቼ ነው ወደ ጎልማሳነት የምትሸጋገሩት? ምን አለ #ከእጩ ወጣትነት እራሳችሁን ብትታደጉ?   https://www.youtube.com/watch?v=gEEl31-g1zY «በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከአብረሃም በላይ (ዶ/ር) ጋር የተደረገ ቆይታ | ETV | EBC | EBCDOTSTREAM»   "ዋይታ ለማነው? ኀዘን ለማን ነው? ጠብ ለማን ነው? ጩኽት ለማን ነው? ያለምክንያት መቁሰል ለማን ነው? የዓይን ቅላት ለማን ነው?" (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳፫ ቁጥር ፳፱)   #ምዕራፍ ፳።   ጉዳዬ የዶር አብርኃም በላይ ቃለ ምልልስ አይደለም። ለነገሩ እሳቸውም የመለሲዝም ትውልድ ናቸው። ይህ × ይመቻቸዋል ብዬ አላስብም።    #ነገረ ሚዲያ እና የቲን ኤጀርነት ናፍቆት።   ሚዲያ መሠረቱም፤ ራዕዩም፤ ግቡም ህዝብ እና ትውልድ፤ ማግስት እና ተስፋ፤ ሞራል እና ኤቲክስ፤ ህግ እና ሥርዓት፤ ነፃነት እና "ፍትሃዊነት" ወዘተ በመሆኑ ትውልድን አስቦ መሥራት ቀዳሚ #ዶግማው ሊያደርገው ይገባል።   ወጣትነት፤ እጩ ወጣትነት በራሱ ጊዜ የሚኖር የባህሬ ዓይነት ቁጣ፤ ግንፍልነት፤ ብስጭት፤ ገረጭራጫነት፤ ችኩልነት፤ አኩራፊነት፤ ልቅ ነፃነትን መሻት፤ ፈጣንነት፤ #አቅማዊነት ፤ ብሩህነት ወዘተ ማነሳሳት ይቻላል። ሁላችንም ያለፍንበት ነው። እናውቀዋለን።    ልጆች ላለውም፤ የልጅ ልጅ ላለውም አብሮ ይኖራል። ሳይኮንበት ግን እያዩት ለመኖር ዕድል ይፈቅዳል እንደማለት። ግን የራስን ዘመን፤ የተቋምን ዘመን ለክቶ በልኩ መጥኖ መንቀሳቀስ የተገባ ነው። ወጣት ሆነው ወጣትነታቸውን ተላልፈው እንደ ጎልማሳ የሚያስቡ ርጉ ሰብዕናወች እኮ አሉ። በተለይ ህግ ያጠኑ ሰብዕናወች፤ በሃይማኖት ቀኖና እና ዶግማ የተመሰጡ ወጣ...

ይህ ዜና የዘር ሐረጌ #ከኢትዮጵያ ነው ለሚል ሁሉ #የምሥራች ዜና ነውን?

  ይህ ዜና የዘር ሐረጌ #ከኢትዮጵያ ነው ለሚል ሁሉ #የምሥራች ዜና ነውን?   https://www.bbc.com/amharic/articles/c6y934gv5l9jo «በግብፅ የተሰባሰቡት የኢትዮጵያ ጎረቤቶች በቀይ ባሕር እና በድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ላይ የጋራ መግለጫ አወጡ»   " ዕውቀትን ለማን ያስተምረዋል? ወይስ ወሬ ማስተዋልን ለማን ይሰጣል? ወተትን ለተወ ወይስ ጡትን ለጣሉ ነውን? ትእዛዝ በትእዛዝ፤ ሥርዓት በሥርዓት፤ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ ነው? " "ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፳፰ ከቁጥር - ፲፩።"   እንዴት አደርን ማህበረ ቅንነት ዛሬ ሁሉም በየፈርጁ ይሞገታል። ሃሳቡ ነው የሚሞገተው።    #ምዕራፍ ፳።   ለምን ተወቀሱ? ለምን ተነቀሱም አለበት? ኢትዮጵያ ሆይ! ስንት አሜኬላ፤ እሾህ፤ ኮሸሽሌ፤ ትሬኮላታ ሃሳብ አራማጅ በአንቺ ልጅነት ይጠራ?   ዘመን - ጊዜ - ራዲዮሎጂ ነው ማለቴ ትክክል ሆኖ አገኜሁት። ሥርዓት ይመጣል ይሄዳል። ይደምቃል // ይከስላል አገር ግን ከእኛ በፊትም፤ ከእኛም በኋላም ትቀጥላለች።   ለዚህም ነው #ኦርጋኒኳ ኢትዮጵያ #የከበደችን #ለሁላችንም ነው እኔ እምለው። ይሰቀጥጣል በውነት የምትሰሙት ትንታኔ ይቀጠቅጣል። እናትን በዚህ ያህል ከውስጥ አግልሎ በእሷ ሥም በተገኜ ተጨማሪ ዜግነት እየተኖረ??? ይገረምማል፤ ይኮሰኩሳል። ይገለማም።    የሚታገሉት በሚታገሉበት መሥመር፤ በብዕር እምንሞግተው የምንሞግተው ኢትዮጵያ አገረ - መንግሥት ስላላት ነው። ዛሬ እንዲያውም #ብልፄውን ልሞግት ነው የገባሁት። ቻል ብልፄው ብዬ መጥቻለሁኝ። ስንቅ ቋጥሮ የሚያስተዳድራቸውንም ሚዲያወች ጭምር። ዛሬ ርህራሄ የለም።   ግን ሁሉም ነገር ከፈጣ...

የእናትነት #የእናታዊነት ነገር ህብር።

  የእናትነት #የእናታዊነት ነገር ህብር። ፆመ ጽጌ ልዩ ፍጹም ልዩ ድንቅ ጊዜ። ዘለግ ያለ፤ ዝልቅ፤ ፍልቅ፤ ብርኃናማ ጊዜ። #ጎንደር ገጠር የጽጌ ፆምን አስመልክቶ መላው የገበሬ ማህበር የመታሰቢያ የመገናኛ ጊዜ በየሳምንቱ አላቸው። "አቤቱ አንተ አምላኬ ነህ ድንቅን ነገር የዱሮ ምክርን በታማኝነትና በዕውነት አድርገኃልና ከፍ ከፍ አደርግኃለሁ ስምህንም አመሰግንሃለሁ።" (ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፳፭ ቁጥር ፩- ፪።) ለፆመ ጽጌ ቤተኞች እንኳን አደረሳችሁ። ፆመ ጽጌ #የመሰባሰብ ይሁንልን። አሜን። ሥርጉትሻ 6/10/026.

የአቶ ደስታ ሌዳሞ ከሥልጣን መነሳት በሚመለከት

  #የብልፄው የመንግሥት አደረጃጀትን ምደባ አስመልክቶ ብዙም መወያያ ሆኖ አላየሁትም። ይህ በራሱ የሚሰጠው መረጃ ያለ ይመስለኛል። የአንድ ክልል የመስተዳድር ሹም ሽር ግን ትንሽ ዘለግ ብሎ የታዬ ይመስለኛል። የሲዳማ ክልል የቀድሞው ፕሬዚዳንት (ርዕሰ መስተዳድር) የአቶ ደስታ ሌዳሞ ከሥልጣን መነሳት በሚመለከት። እንደ እኔ ለበለጠ፤ ለተሻለ ኃላፊነት ይመስለኛል። የፌድርሼን ም/ቤት አፈ - ጉባኤነትን ለመስጠት ይሆናል። ከዚህ ደረጃ ያነሰ ዕድል ይገጥማቸዋል ብዬ እኔ አላስብም። ሹም ሽሩ ፖለቲካዊ ምደባ ነው። ለአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባነት አፈፃጸሙን እኮ አየን፤ ተመለከትን አስተዋልንም። " አንተ ሁሉን ታያለህ" (መቃብያ ሣልስ፱- ፳፮) ሥርጉትሻ 04/10/026.

#ለታደሉት #ብቻ።

  #ለታደሉት #ብቻ ። "ትህትናን እንደልብስ ታጠቁ፤ እግዚአብሄር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፤ ለትሁታን ግን ፀጋን ይሰጣል።" (የሐዋርያው የቅዱስ ጴጥሮስ መልዕክት ፩። ምዕራፍ ፭ ቁ፭) ሥርጉትሻ 05/10/026.

#ማሸነፍ #በሃሳብ #ልቅና #በድርጊት #ልዕልና።

  #ማሸነፍ #በሃሳብ #ልቅና #በድርጊት #ልዕልና ።   "ዳግመኛ አርበኞች ቢከቡኝ እኔ በሱ አመንሁ እግዚአብሄርን አንዲት ነገር ለመንሁት ያቺኑ እፈልጋለሁ ብሎ እንደ ተናገረ በሱ ያመኑ ሰወች ፍራት የለባቸውም በሱ ያመነ ሰው ለዘላለሙ በሕይወት ይኖራል ከክፋ ነገርም የተነሣ አይፈራም" (መቃብያ ፯ ቁጥር ፫)   #ምዕራፍ ፳።   አዱኛወቼ ቤተ - ሥርጉትሻ እንዴት ነን? ጤና ይስጥልኝ ኢትዮጵያ እንዴት አድረሽ - አረፈድሽ ይሆን?   #ዕፍታ ላፍታ።   ማሸነፍ ደስታ ይሰጣል። መሸነፍ ደግሞ ውስጥን ያጠነዝላል። ለብልህ ሰው ግን መሸነፍን የመቀበል አቅም ከኖረው ውስጡ ሳይጠነዝል ወይንም ሳይጠወልግ ለቀጣይ የህይወት መስመር ሁሉ ከእግዚአብሄር ነውና አቅሙን አበረታቶ፤ ከአቅሙ ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ መክሮ እንደ ገና አወን እንደገና የመነሳት ዕድል ሊኖር ይችላል።   #ማሸነፍ ። የሚያሸንፈው ጥራት ያለው ሃሳብ እና ድርጊቱ ነው። #መሸነፍ ። የሚሸነፈው እና የሚወድቀው ሃሳቡ እና አካሄዱ ነው። #መሸናነፍ ። ቅይጥ ነው ይሄ የኪሳራ እና የትርፍ ምንዛሬ። የታክቲክ እና የስትራቴጂ ክህሎትም።   በጦር ሜድ ብቻ አይደለም የለቱ የወግ ገበታዬ ሊያጋራችሁ ያሰበው። በማህበራዊ፤ በጥበባዊ፤ በሃይማኖታዊ፤ በፖለቲካ፤ በኢኮኖሚያዊ፤ በትዳራዊ ወዘተ ገጠመኞች ውስጥ ሰው በሁለት ቢከፍለውም የእኔ ፈንገጥ ያለው ዕይታ #መሸናነፍ የሚል አክዬ ወደ ሦስት ከፍ አድርጌዋለሁኝ። ተጋጣሚው ድህነት ቢሆን ብላችሁ እሰቡት ወይንም ጤና ማጣት ቢሆንስ ብላችሁ ዕድል ስጡት፤ ወይንም ትምህርታዊ ጉዳይስ ቢሆን ብላችሁም ማስላት ትችላላቸው። መኖር እና ጅረቱ ወዘተረፈ ነውና።    #ተዚህ ላይ ፈንገጥ ያሉ ዕይታወቼን ብ...