ኢንጂኔር ወ/ ሮ አይሻ መሃመድ - የወ/ሮ ዓለምጸሐይ ጳውሎስን ኃላፊነት ይረከቡ ይሆን?
#ኢንጂኔር ወ/ ሮ አይሻ መሃመድ - የወ/ሮ ዓለምጸሐይ ጳውሎስን ኃላፊነት ይረከቡ ይሆን? "አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።" #ምዕራፍ ፳። ሹምሽሩን አዳመጥኩኝ። #እመለስበታለሁኝ ። በካቢኔ ውስጥ ኢንጂነሯ የሉም። ከምከታተላቸው ሴት የፖለቲካ ሊቃናት አንዷ ናቸው። ከነበሩበት ደረጃ ጋር የሚመጥን ቦታ ሳስብ፤ የኢትዮጵያ የፖለቲካ መዕከል የጠቅላዩ ጽህፈት ቤት ስለሆነ የወሮ አለምጸሐይ ጳውሎስን ቦታ አሰብኩት። ለምን? 1) ከሙያቸው፤ ከልምዳቸው አንፃር፤ 2) የጠቅላይ ሚር አብይ #ውስጠት ተመስጥሮ ያለ መሻት ታክሎ ይህ ቦታ ለሳቸው ይሆን ይሆን አልኩኝ? ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ የማይደብቁት፤ በአገኙት አጋጣሚ የሚናገሯቸው አመክንዮወች አሉ። በአዲሱ የሥራ ዘመናቸው መግቢያ መቅድመ ጊዜ ባይደጋግሙት ይሻል ነበር። የሆነ ሆኖ ሌላም የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የነበሩትም ወሮ ሎሚ በዶም አልተመደቡም። #ነገረ " #አይመለከተነም " -- በጓዳ ምነው ሥርጉትሻ በብልጽግና ስብሰባ ታተኩሪያለሽ የሚሉ ወዳጆች አሉኝ። ይህ እኛን አይመለከተንም የሚሉ የቤታችን ቤተሰቦች አሉ። ህዝቤ የእኔ፤ ህዝባችን የሁላችን #ኑሮው የሚመራው በገኃዱ ዓለም #በኢሊት ነው። ስለዚህ ይህንን አስኳል አላየሁምም፤ አልሰማህም ልለው አልፈቅድም። የአገሬ ጉዳይ ቀዳሚው #አጀንዳዬ ነው። እከታተላለሁ፤ አደምጣለሁ። ዕይታዬንም አጋራለሁኝ። አይመለከተነም የሚሉትም እኮ ሌላ ሥራ የላቸውም፤ ይህንኑ ሂደቴ ያሳሱታል፤ ያባዝቱታል፤ ዛሬ ሁሉንም እዩ አጀንዳው የብልፄ ሹም ሽር፤ ሽግሽግ ይሆናል። በአወንታዊም በአሉታዊም። የዓለም ...