ግልብጥ ...
ግልብጥ የልብ አፍርጥ ልጥ። ከሥርጉተ ሥላሴ 14.06.2010 ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ። „በዚያም ቀን ይህ ቅኔ በይሁዳ ምድር ይዘመራል። ፣---- የጸናች ከተማ አለችን፣ ለቅጥርና ለምሽግ መዳህኒት ያኖርባታል። ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፳፮ ቁጥር ፩“ ሲንጠባጠብ - ሽርክት፤ ሲሸረከት - ግርድፍ። ስከረከም - ታሬ። ስመትር - ቅርጥምጣሚ። ሲረግፍ - ጤዛ። ሀገር ምድሩን አካልሎ … ካለ ልኩ ተንቧልሎ ----- ሲሰጠስጥ በድንክ አልጋ - ግልብጥ ሳይናጥጥ ናጥ------! ላጥ …. እንጦርጦስ፤ ጢባ - ጢቦ፤ ጠራጠሮ --- ተንትርትሮ - ግርድ ሲሆን። ተያይዞ በሆድ ሰንሰለት ጅዋጅዊት ሲጫወት፤ በነፍ...