19.11.2019 የሞት ጠረን ለሴራ ፖለቲካ ቀመር በኦዳ ኢንፓዬር።
የሞት ጠረን ለሴራ ፖለቲካ ቀመር በኦዳ ኢንፓዬር። እንዴት ናችሁ ጤና አዳሞቼ? ደህና ናችሁ ወይ? ኦዳና ጃራ ግብግባቸው በጉልህ እስኪወጣ ቀዳሚው የአህድዮሽ ጉዞ በፀረ ኢትዮጵያዊ መንፈስ ይቀጥላል። ከዚህ መከራ የሚድነው አሁን ባለው ሁኔታ የአድዋ ሥርዕዎ መንግሥት ብቻ ይሆናል። 18 ወራት የኢትዮጵያን መከራ ያልወቀጠው እሱ ብቻ ነው ማለት ይቻላል። የቀረበት የማህል አገር ዘመናይነት ብቻ ነው። እርግጥ ነው በራሱ መስመር አገርን አምሷል። ሰፊ ስለሆነ እሱን አቁሜ ወደ ዋናው እርእሴ ልሂድ። በዚህ 18 ወራት የበቀል ማወራረጃ፣ የጭካኔ የመሞከሪያ ጣቢያ የነፍስ ይማር ባዕት ያልሆነ አዬር ባዕት አልነበረም። ቁንጥንጡ፣ ዝርክርኩ፣ መሰሪው፣ ሸፍጠኛው የአብይወለማ ሌጋሲ ተጭኖ በያዘው የአማራ ህዝብ እና መንግሥት ከቀደሙው ዘመን ባላነሰ ፍላጎቱን ለማስፈፀም የመሞከሪያ ጥንቸል አድርጎት ባጅቷል። አሁን ግዙፋን ኦፕሬሽን በእንደልቡ አቶ ዮኋንስ ቧያለው እና በአቶ መላኩ ፈንታ የስሜን አሜሪካ እና የለንደን ጉዞ ሀ ብሎ ይጀምራል። ሲመለሱ የእራሱ እግር የእግሩ ራስ ሆኖ ይጠበቃቸዋል። በዚህ ማህል ሁለት አውራ ጉዳዮችን እንይ። ሃሳብን የማስተናገድ አቅም። ጥያቄ መጠዬቅ በህግ ያስቀጣል በዴሞክራሲ አሻጋሪው ጠቅላይ ሚኒስተር የህሊና አቅም። ሽብሽብ። የተገደሉት ሊሂቃን በሙሉ የሞገቱ ስለመሆናቸው እኔ በግሌ አልጠራጠርም። የታሠሩትም ቂሙ የሚመነጨው ሞገታችሁኝ ነው። ጠቅሚሩ ቶለራንሳቸው ዜሮ ነው። ፈሪም ናቸው። መናገር መናገር መናገር ጥሪያቸው ይህ ነው። ማድመጥ አቻችሎ መጓዝ አልተፈጠረባቸውም። ስለዚህ ዴሞክራሲ ሞቶ የተቀበረው እሳቸው በህይወት የተፈጠሩበት ዕለት ነበር። እኔ ዴሞክራሲን ...